Get Mystery Box with random crypto!

ጠሪቁል ጀና መድረሳ ማዕከል

የቴሌግራም ቻናል አርማ tarikuljenah — ጠሪቁል ጀና መድረሳ ማዕከል
የቴሌግራም ቻናል አርማ tarikuljenah — ጠሪቁል ጀና መድረሳ ማዕከል
የሰርጥ አድራሻ: @tarikuljenah
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 907
የሰርጥ መግለጫ

📩የጠሪቁል ጀና የዲን እዉቀት ማስፋኣፍያ & http://t.me/tarikuljenah የቻናሉ አላማ የተለያዮ የዲነል ኢስላም እዉቅት የሚያገኙበት ቻናላችን ነው! https://t.me/joinchat/AAAAAErB1tU4HaJolm_uGg

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-05 16:24:32
الحمدالله على نعمة الاسلام
አልሀምዱሊላህ ዲነል ኢሰላምን ላደልከኝ ተደራራቢ ምሰጋና ይገባህ ጌታየ ያረቢ የክሰረት ሁሉ ክሰረት ከአላህ ዉጭ ማምለክ
https://t.me/TARIKULJANAH2
48 views13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 15:51:17 የአለም ፍፃሜ ሲቃረብ ዝሙት በገሀድ ይፈፀማል፣ አስካሪ መጠጥም በገሀድ ይጠጣል።

ነብዩ ሙሀመድ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም
https://t.me/TARIKULJANAH2
215 views12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 12:14:28 ጓደኛህ ማነው!?
በዕለተ ትንሳዔ ሰዎች ከባድ የሆነን ፀፀት ከሚፀፀቱባቸው ነገሮች አንዱ በዱንያ ሳሉ መጥፎ ጓደኞችን ይዘው የነበሩ በመሆናቸው ነው። ያን ለት (ዋ ጥፋቴ ! አከሌን ወዳጅ አድርጌ ባለያዝኩ ኖሮ) ሲሉም ይመኛሉ።
https://t.me/TARIKULJANAH2
234 views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 17:26:05
''ከእውቀት በፊት ስነ ምግባርን ተማር! ''
ሼይኽ ኤልያስ አህመድ
https://t.me/TARIKULJANAH2
Joine
243 views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 06:15:13 ቀኑን በመልካም ከጭንቅ ነፃ አድርጎ ቀልቡን አረጋግቶ የሚውል ብልጥ ስው ማለት የጥዋት ዚክር (ውዳሴን የሚያደርግ ስው ነው::

ለዛም ነው ጌታችን አላህ ለቀልባችን ምድሀኒት እቺን የሚያስታውስን
الا بذكر الله تطمإن القلوب

https://t.me/TARIKULJANAH2
joine
231 views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 00:20:09 ሸይኽ ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-

ቁርኣንን መቅራት ከምርጥ ትዝታዎች አንዱ ሲሆን የታላቁን አላህ ሲሳይ መመልከት ከመልካሞች መልካም ስራ ነው።
جامع المسائل (٣٨٥/٣)

https://t.me/AlQuranbyword1
ቻናላችንን ለመቀላቀል joine
277 views21:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 02:47:08
ለሚያስተነትን ሰው! ቀብር ውስጥ ማለት ቢያቅተንስ!?
https://t.me/TARIKULJANAH2
Joine
251 views23:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 19:31:13 በመቀጠል አዲሱ አመራሮች በሸሪዐ ፍርድቤቱ ዋና ፕሬዝደንት አማካኝነትየሚከተለውን ቃለ መሀላ ፈፅመዋል:-
" أقسم بالله العظيم أن أكون موثوقا لديني ووطني ، وأن أحافظ على وحدة المسلمين، وإنه لقسم لوتعلمون عظيم، والله العظيم، والله العظيم،والله العظيم،والله العظيم!!"
" የሃይማኖቴንና የሀገሬን አደራ በአግባቡ ለመወጣት እንዲሁም የሙስሊሙን አንድነት ለማስጠበቅ እንደምሰራ ዝግጁ መሆኔን በአላህ ስም ቃል እገባለሁ። "

በመጨረሻም መርሃ ግብሩ በሸ/ጣሀ የሚቀጠሉት አንቀፆች ተነበው በዱዐ ተቋጭቷል።
" وتلك الآيام نداولها بين الناس.."

والحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات!

#አዲስአመራር
#ሁሉንአቀፍመጅሊስ
#ለውጥ
https://t.me/TARIKULJANAH2
Nesru Khedir/ነስሩ ኸድር
277 viewsedited  16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 19:31:13 የዛሬው ሀምሌ11/2014 "የኢትዩጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥ እና አንድነት 2ኛ ጉባኤ" ውሎ አጭር ጥንቅር

ፕሮግራሙ በሽ/ዐብዱልሐሚድ አሕመድ (ከጅማ) መድረክ መሪነት ከረፋዱ 4:30 ላይ ጀምሯል።

የታላቁ አንዋር መስጅድ ሸ/ጧሀ ሀሩን የሚከተሉትን የቁርአን አንቀፆች አንብበዋል:-

" لا يكلف الله نفسا إلا وسعها لها ما كسبت وعليها ما اكتسبت ربنا لا تؤاخذنا إن نسينا أو أخطأنا ربنا ولا تحمل علينا إصرا كما حملته على الذين من قبلنا ربنا ولا تحملنا ما لا طاقة لنا به واعف عنا واغفر لنا وارحمنا أنت مولانا فانصرنا على القوم الكافرين "

" الله الذي خلق سبع سموات ومن الأرض مثلهن يتنزل الأمر بينهن لتعلموا أن الله على كل شيء قدير وأن الله قد أحاط بكل شيء علما "

በመቀጠል ዶ/ር ጀይላን ኸድር እና ሸ/ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ እንዲሁም ሸ/ዐብድልከሪም ሸ/በድረዲን በየተራ የጉባኤውን መርሃ ግብር አንደሚከተለው አስረድተዋል:-

1ኛ/የዶ/ር ጀይላን ኸድር መልዕክት:-
የሚከተሉትን አንቀፆች አስታውሰዋል
" واعتصموا بحبل الله جميعا.."
" إن الذين فرقوا دينهم وكانوا شيعا لست منهم في
شيء إنما أمرهم إلى الله ثم ينبئهم بما كانوا يفعلون "
" ዛሬ እዚህ የታደማችሁ ሚያዚያ 23/2011 ያስረከባችሁንን ስልጣን መሠረት አድርገን መንግሥታችን ባደረግልን ድጋፍም ጭምር ኢስላማዊ ባንክን ማቋቋም ችለናል፣ ሕዝበ ሙስሊሙን የሚመጥን መሀል መዲናዋ ላይ ሰፊ መሬትም ተቀብለናል..
ሆኖም ከዚህ በላይ ብዙ ስራዎችን መስራት ሲገባን የተመረጥነው ለ6 ወራት ሳይሆን እስከመጨረሻው አንድንቀጥል ነው በሚል ንትርክ እየተስተጎጎልን ለዛሬዋ እለት በቅተናል።
ዛሬ የተገኘነው ጉዳዩን ወደናንተው ለመመለስ ነው። ምክንያቱም የኢትዩጵያን ሙስሊም የምትወክሉት እናንተ እንጂ መስማማት ያልቻልነው እኛ ጥቂት ዑለሞች ስላልሆንን።"

2ኛ/የሸ/ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ መልዕክት:-
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አሕመድ በሰጡን ምክር መሠረት እሰከ ዛሬ ሀምሌ 11/2014 ድረስ ብቻ እኔና ሙፍቲ መጅሊሱን በጊዜያዉነት እየመራን ነበር ፣ የዛሬውም ፕሮግራም የዘገየው ሙፍቲን እየጠበቅን ስለነበር ነው።
እሳቸው ባለመገኘታቸው የእሳቸው ምክትል የነበሩት ዶ/ር ጀይላን ኸድር መድረክ ላይ እንዲመጡ ሆኗል።
የዛሬው አብይ አጀንዳችንም ለ3 ዓመታት መጅሊስን የሚመሩ አዲስ አባላትን መምረጥ ይሆናል።
ይህንን ለማድረግ በሚያስችል መጠን እስከ አሁኑ ሰዓት ከ 300 አባላት 250 በመገኛተችውና ምልአተ ጉባኤው በመሟላቱ ወደ ምርጫችን እናመራለን (እስከ ፕሮግራሙ ፍጻሜ ድረስ የጉባኤተኛው ቁጥር ወደ 261 ከፍ ማለቱን ልብ ይሏል) ።
ይሀንን የሚመሩ የአስመራጭ ኮሚቴ አባላትም ይኖሩናል።

3ኛ/የሸ/ዐብድልከሪም በድረዲን መልዕክት:- https://t.me/TARIKULJANAH2

ዛሬ እዚህ የተገኘነው አማናውን ለሚገባው አካል ለማስተላለፍና፣የሰላም አጋር መሆናችንን በተጨባጭ ለማስመስከር ነው።
ይህን የምናደርገው እንኳን ደም ይቅርና አንባም ሳይፈስ ነው።
የሰላም ጉዳይ የዑለሞች ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነው።
በሰላም ጉዳይ ከማንም ጋር አንደራደርም።
በመቀጠል የሚከተሉት አስመራጭ ኮሚቴ አባላት መድረኩን ተረክበዋል:-
1_ ሐጂ/ሙሐመድኑር ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ (የሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሐቢብ ልጅ)
2_ ሐጂ/ ዐብዱልቃድር
3_ ኡ/ዐብዱልዐዚዝ ኢብራሂም
4_ አቶ/ባሕረዲን አወል
5_ ሐጂ/ኻልድ ሙሐመድ

በመቀጠልም አስመራጭ ኮሚቴው የምርጫ ሂደቱን አፈጻጸም እንደሚከተለው አብራርቷል:-

የሁሉም ክልል ተወካዩች በተሰጣቸውና እንደሚከተለው በተዘረዘረው ኮታ መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት የሚሆኑ በድምሩ 30 የሚሆኑ ተወካዩቻቸውን ይመርጣሉ።
* ኦሮሚያ 5
* አማራ 3
* አ/አ 3
* ደቡብ 3
* ሶማሌ 3
* ዐፋር 3
* ድሬዳዋ 2
* ትግራይ 2
* ሀረሪ 1
* ቤኒሻንጉል 2
*ጋምቤላ 1
* ሲዳማ 1
* ደቡብ ምእራብ 1

የሚመረጡ አመራሮች መስፈርት:-
1_ ዕድሜው ከ30 በላይ የሆነ፤
2_ ኢትዩጵያዊ የሆነ፤
3_ በሚመረጥበት ክልል ነዋሪ የሆነ፤
4_ ሕዝበ ሙስሊሙን ለማገልገል ቅን ፍላጎት ያለው፤
5_ ለእምነቱ ተማኝ የሆነ ተቅዋ ያለው፤
6_ ለቦታው የሚመጥን ብቃትና ክህሎት ያለው፤
7_በመልካም ሥነ ምግባር የሚታወቅ፤
8_ የተላያዩ ማህበራዊ ተሳትፎዎችን ያደረገ፤
9_ መሠረታዊ የሃይማኖቱን መርሆች አክብሮ የሚተገብር፤
10_ የየትኛወም ፖለቲካ ፖርቲ አባል ያልሆነ።

በመቀጠል የእያንዳንዱ ክልል ተወካዩች የተለያዩ ቦታዎች ላይ በመሆን ከተጠቆሙት እጩዎች መካከል የሚከተሉትን የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በድምጽ ብልጫ መርጠዋል:-

ከኦሮሚያ
1_ሸ/ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ
2_ሸ/ዐብዱልሐሚድ አሕመድ
3_ ኡ/ጋሊ አባቦር
4_ ኡ/ዚያድ ዐሊ
5_ ሸ/ሙሐመድ ዐሊ ኸድር

ከአ/አበባ:-
1_ ሸ/ጧሀ ሀሩን
2_ ሸ/ኑረዲን ደሊል
3_ ሸ/ሐሚድ ሙሳ

ከአማራ:-
1_ ሸ/ኡድሪስ ደጋን
2_ ኡ/ዐብዱረሕማን ሱልጣን
3_ ሸ/ሙሐመድ ኢብራሂም

ከደቡብ:-
1_ ሸ/ዐብዱልከሪም ሸ/በድረዲን
2_ሸ/ሙሐመድ ሙስጠፋ
3_ ሸ/ዐብዱልሀዲ

ከሶማሌ:-
1_ሸ/ዐብዱልዐዚዝ ሸ/ዐብዱልወሌ
2_ሸ/አሕመድ ሙሐመድ
3_
ከድሬዳዋ:-
1_ሸ/አሚን ኢብሮ
2_ሸ/ሙሐመድ ዑመር

ከትግራይ:-
1_ ሸ/ዐብዱልመናን ማሕሙድ
2_ ኢንጂነር/አንዋር ሙስጠፋ

ከቤኒሻንጉል:-
1_ ሸ/ዐለሙዲን
2_ሸ/አልመርዲ

ከጋምቤላ:-
1_ ሸ/ዛኪር ኢብራሂም

ከዐፋር:-
1_ ዶ/ር ሙሐመድ ሑሴን
2_ ሸ/መሐመድ አሕመድ ያሲን
3_
ከሲዳማ:-
1_ሸ/ሙስጠፋ ናስር

ከደቡብ ምእራብ:-
1_ሸ/ሑሴን ሐሰን

ከሀረሪ:-
1/ሸ/ሙሐመድ አሚን ዐያሽ

በመቀጠል ከእነዚህ 30 የጠቅላላ ጉባኤ አዲስ አባላት 14 የስራ አስፈጻሚ አመራሮችን አንደሚከተለው መርጠዋል:-
1_ ሸ/ ሐጂ ኢብራሂም (ፕሬዚዳንት)
2_ ሸ/ ዐብዱልከሪም ሸ/በድረዲን (ተ/ም/ፕሬዚደንት )
3_ ሸ/ ዐብዱልዐዚዝ ዐብዱልወሌ (ም/ፕሬዚደንት)
4_ሸ/ ሐሚድ ሙሳ (ዋና ፀሃፊ)
5_ሸ/ ዐብዱልሐሚድ አሕመድ (አባል)
6_ሸ/ እድሪስ ዐሊ (አባል)
7_ ሸ/መሐመድ አሕመድ ያሲን (አባል)
8_ሐጂ/ሙስጠፋ ናስር (አባል)
9_ሸ/ አልመርዲ ዐብዱላሂ (አባል)
10_ ሸ/ ሑሴን ሐሰን (አባል)
11_ ሸ/ ዛኪር ኢብራሂም (አባል)
12_ ሸ/ ሙሐመድ አሚን ዐያሽ (አባል)
13_ ሸ/ አሚን ኢብሮ (አባል)
14_ኢንጂነር/ አንዋር ሙስጠፋ (አባል)
250 views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 19:30:36
179 views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ