ከዓሹራእ ቀን ጋር ተያያዥነት ያላቸው ቁም ነገሮች የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:- "የዓሹራእ ቀንን መጾም ያለፈውን አመት ወንጀል ያሳብሳል ብዬ አላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ::" (ሙስሊም ዘግበውታል) የዓሹራእ ቀን ከሙሐረም ወር አስረኛው ቀን ነው:: በዚህ እለት ነበር አላህ ነብዩ ሙሳ እና ህዝባቸውን ከፊርዓውን ያዳናቸው:: የዓሹራእን ቀን መጾም የተወደደ ስለመሆኑ ዑለማዎች ስምምነት ኢጅማዕ ያላቸው መሆኑን ነወዊ እና ኢብኑ-ሐጀር እንዲሁም ሌሎችም ዘግበዋል:: የረመዳን ወርን መጾም ግዴታ ከመሆኑ በፊት ይህን ቀን መጾም ግዴታ የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን ግዴታነቱ ተሽሮ በፍላጎት የሚጾም የሱና ጾም ሆኗል:: በአራቱም መዝሀብ ዑለማዎች አቋም መሰረት ከዓሹራእ ቀን በተጨማሪ ዘጠነኛውንም ቀን መጾምም ይወደዳል:: ይህም መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ይህንን ቀን እንደሚያክብሩት በሰሙ ግዜ እንዲህ በማለታቸው ነው:- "በአላህ ፍቃድ እስከ ሚቀጥለው አመት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም ቀን አብረን እንጾማለን::" (ሙስሊም ዘግበውታል) ከዓሹራእ ቀን ጾም ጋር በተያያዘ ዑለማዎች የተለያዩ መረጃዎችን በመመርኮዝ በዚህ መልኩ ቢሆን የተሻለ ነው ሲሉ የሚሰነዝሮቸው ሀሳቦች አሏቸው ከነዛም መካከል የተወሰኑትን ለመጠቆም ያህል:- ዘጠነኛውን ቀን ከአስረኛው ቀን ጋር መጾም አስረኛውን ቀን ብቻ ከመጾም የተሻለ ነው:: ከላይ ያሳለፍነው "በአላህ ፍቃድ እስከ ሚቀጥለው አመት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም ቀን አብረን እንጾማለን::" የሚለው ሀዲስ ይህንን ሀሳብ ያጠናክራል:: ይቀጥላል… https://t.me/tahaahmed9 330 views20:26