Get Mystery Box with random crypto!

በዒድ እለት የመልካም ምኞትን መግለጽን በተመለከተ «የመልእክተኛው ባልደረቦች የዒድ ቀን በሚገናኙ | 🗞 ጣሀ አህመድ – Taha Ahmed 🗞

በዒድ እለት የመልካም ምኞትን መግለጽን በተመለከተ

«የመልእክተኛው ባልደረቦች የዒድ ቀን በሚገናኙበት ወቅት አንዳቸው ለሌኛው "ተቀበለ አላሁ ሚና ወሚንከ" ይባባሉ ነበር።» (ኢብኑ ሀጀር ፈትሁልባሪ ላይ ዘግበውታል አልባኒም ሰነዱ ትክክለኛ ነው ብለዋል)
ትርጉሙም: ‐ "አላህ ከእኛም ከአንተም መልካም ስራችንን ይቀበልን" ማለት ነው።

እንኳን አደረሳችሁ በመባባል የመልካም ምኞትን መግለጽ እና ዱዓእ መደራረግ በሸሪዓ መሰረት ያለው ለመሆኑ ይህ ግልፅ መረጃ ነው።

ጣሀ አህመድ

https://t.me/tahaahmed9