Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዓመት✿❀✿❀ ከጎረቤት ረብሻ ከባለትዳር ጥቅሻ ከተናካሽ ውሻ ከገቢዎች ፈለጣ ከአለቃ ቁጣ ከመ | 𝕡𝕒𝕤𝕤𝕔𝕠𝕕𝕖 🤟

አዲስ ዓመት✿❀✿❀
ከጎረቤት ረብሻ
ከባለትዳር ጥቅሻ
ከተናካሽ ውሻ
ከገቢዎች ፈለጣ
ከአለቃ ቁጣ
ከመንግስት ለበጣ
ከሞራል ስብራት
ከገንዘብ ብድራት
ከቀፋዮች ብልጠት
ባዶ ቤት ከመግባት
ከጅል ጋ ከመዋል
ቪዛ ከመከልከል
ጨጓራ ከሚልጥ
የመብራት መቆራረጥ
ከሰራዊት ማስጠንቀቂያ
ከኢቲቪ ማስታወቂያ
ከሰይፉ ፉገራ
ከፈሪ ፉከራ
የፀዳ ይሁንላችሁ፡፡❀✿❀✿
ላላገባችሁ ትዳር
ላገባችሁ ፍቅር
ያድላችሁ፡፡
ባዲሱ ዓመት
ከኪሳችሁ ፍራንክ
ከጥርሳችሁ ሳቅ
አይጥፋ፡፡
ቤታችሁ ቄጠማ ጎዝጉዙ
ላንድ ልጅ አንድ ደብተር ግዙ
በጎ ሰሪዎችን አግዙ
ወለሸዶ ለመሳም
ዘርቶ ለመቃም
ያብቃችሁ፡፡
መርቅኖ ከማቀድ
አፍቅሮ ከማበድ
በግፍ ከመሰደድ
ካልተከደነ ጉድጓድ
ውሃ ካቆረ መንገድ
እጅ እጅ ከሚል ቀልድ
ጦምሮ ከመታሰር
ከባለጌ ወንበር
ከአሽሟጣጭ ከንፈር
ከንፁህ ሰው ደም
ከስኳር ወረፋ
ከስልክ ጠለፋ
ቀጥሮ ከሚቀር
ከአካውንት ሀከር
ከውሃ ሙላት
ከወዳጅ ክህደት
ከFacebook ጅንጀና
ከውሸታም ዜና
ብሎክ ከመደረግ
like ከሐነፈግ
ይሰውራችሁ፡፡ አሜንንን


★★★★


Happy New Year
2014 2014
የኔ ውድ ጓደኛ
የኔ ሁሉ ነገር
አንተን/ቺን/በመተዋወቄ በጣም ደስተኛ ነኝ

አዲሱ 2014