2022-07-03 17:42:27
ፅናት
ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ (የሸዋ ልጅ)
ክፍል
.
፨ ፅናት በዛ ሰአት እራሷን አልነበችም ውስጧ ዝብርቅርቁ ወጥቶ ነበር። ደረቃ
ቀረች በቆመችበት የያዘችውን ትኩሱ ቡና እግሯ ላይ ቢደፍም አልተሰማትም።
በፀሎት ቡና ወደወደቀበት እጆቿን በመዳበስ አይኖቿን ወደ ጣሪያ
ወረወረቻቸው። በፀሎት ለስለስ ባለ ድምፅ "ምንድነው ምን ተፈጠረ?" አለች።
ፅናት አይሆንንንምም ብላ ጫከች።
፨ ያኔ ሊባኖስ በፍጥነት በሩን በርግዳ ገባች። ሁሉም ፅናትን ለማረጋጋት
ቢሞክርም አልቻሉም ፅናት አንዴ ነቃ ብላ "አይ አይ ሊሆን አይችል" ትላለች
ከዛም ፍዝዝ ብላ ትቆያየች። ሊባኖስ ፅናትን ደግፋ ፍራሽ ላይ ጋደም አደረገቻት።
ፅናት ግን በጭራሽ ውስጧ አላረፈም ። መንቀጥቀጥ ጀመረች። ሊባኖስ በጣም
ደነገጠች አቶ ኪዳኔም እንደዛው በፀሎት ምን እንደተፉጠረ ብትጠይቅም ምላሽ
አላገኘችም። ከዛም ቀዝቀዝ ባለ ድምጿ "ፅናቴ ፅናቴ ደና ነሽ እህቴ"አለች።
መልስ አልተሰጣትም ከዛም "ሊባኖስ እህቴ ደና ነች?" አለች አሁንም ዝም
ከዛም ጮክ ብላ መልሱልኝ ብላ ጮከች።
፨ሊባኖስ ፈጠን ብላ ወደ በፀሎት ቀረባ "ደና ናት አትስቢ እንዲ ሆነሽ ማየት
ከብዷት ነው የሚወዱት ሰው በእዚህ መልኩ ተጎድቶ ማየት ያማል" አለቻት።
በፀሎትም የሊባኖስ ንግግር የገባት ትመስላለች "ልክ ነሽ"ብላ ኡፍፍፍ አለች።
ሊባኖስ ፅናትን ለማረጋጋት ወደ ፅናት ሄደች። ፅናት አሁንም አልተረጋጋችም ይህ
ነገሯ ለቀናት ዘለቀባት ከዛም በሂደት እየለመደችው መጥታ እህቷን መንከባከብ
እና ማገዝ ጀመረች።
፨በጊዜ ሂደት በፀሎት ማየት ባለመቻልዋ ተስፍ ቆረጠች። ፅናት ግን ተስፍ
እንዳትቆረጥ የሚቻላትን ሁሉ ታረጋለች ለእሷ ብላ ማየት መስማትም የማይችሉ
ስዎችን ታሪክ አፈላልጋ ታነብላታለች ለምሳሌ ስለ ሄለን ኪለር። ሄለን ኪለር
ለበፀሎት ብረታትን ለፅናት ደሞ ድልን ሰጥታቸዋለች። ፅናት ትምርቷን
አላቋረጠችም ምክንያቱም ሊባኖስ ታግዛታለች። የፅናት የቀን ተቀን ድረጊቷ
ሌሊት ተነስታ ለእሷ እና ለእህቷ ሊባኖስ ቤታቸው ካደረችም ለእሷ ቁርስ ሰረታ
ቤትም አፅድታ ትምህረት ቤት ትሄዳለች ሄዳ 6:30 ትመጣለች። ከትምህርት
ስትመለስ 30ደቂቃ ያክል ተኝታ በድጋሚ ተነስታ ታጠናለች። አጥናታ ስጨረስ
9:30 ይሆናል። ከዛም ማታ ማታ የምትሸጠውን ምግብ በሊባኖስ እርዳታ
ትስራለች። በራቸው ላይ በዳቦ የሚበሉ ቀለል ያሉ ምግቦችን እንሸጣለን ብለው
እሷና ሊባኖስ ካርቶን ላይ ፅፈው ነው የለጠፉት። ፅናት የቤቱን ስራ ስትስራ
ሊባኖስ እና በፀሎት ከ ሊባኖስ መኖሪያ ያመጣሉ ሊባኖስም የደረሰችበትን
ታግዛታለች። አቶ ኪዳኔ በፀሎት ለህክምና የተጠየቀችውን ብር መክፍል
ስላቃታቸው በሶስተኛው ወር ነበር ከነ ቤተሰቧቻቸው ድርሻቻው
የጠፋው።ገፍታሪው ልጅም ያን ቀን ነበር የተሰውረው። የሰፈሩ ሰው የቡና ቁርስ
መሆናቸውም ቀጥሏል እና ደሞ ፅናት በክፍል ከፍ ባለች ቁጥር በውበቷ
ያልተማረከ እና ያልጠየቃት እኩያ ወንድ የለም ውበቷ በጣም ሲጨምር ቤቷ
ድረስ ዱረየውም ጨዋውም እየመጣ የአብረሽኝ ሁኒ ማመልከቻውን ያስገባል።
በሊላ በኩልም ቆንጆ ቡዳ ነው ቡዳ ቆንጆ ነው እያሉ የተቀሩት የሰፈሩ ኑዋሪዎች
ያበሽቆት ጀመር።
፨ፅናት ሁሌም ይህ ነገር ስሚ ሰለቻት ታለቅስ ነበር ገና ሳታድግ በቅጡ እንዲ
መባልዋ ምቾት ነስቷታል በየ መንገዱ የሚስሟት አሮጊቶችም ጭምር ስለቿት።
ከዛም ሊባኖስ አንድ ሀሳብ አመጣች ቤት መቀየር በእዚህ ተስማምተው ሊባኖስ
ቤት መፈለግ በጀመረች በሳምንቱ አገኘች። ይህን ዜና ለእነ ትግስት እንዲ ስትል
ነገረቻቸው "ቤት አግኝቼላችዋለው ያው ሰፈሩ ከእዚህ የባሱ ስዎች ነው ያሉበት
ነው ግን ይሁን አለቻቸው ስትነግራቸው ፅናት ቡና እያፈላች ነበረ ከቡናው ተነስታ
ፍራሹ ላይ የተቀመጠችውን ሊባኖስን እና ዌልቸር ላይ የተቀመጠችውን
በፀሎትን ሳመቻቸው።
በነጋታው ሊባኖስ የነገረቻቸውን ሁሉ አድረገው ወደ አዲሱ ሰፈር ወደ አዲሱ ቤት
ተቀላቀሉ ይህ ሲሆን ፅናት 10 ክፍል ደረሳ ነበር።
፨ እነ ፅናት ያን ጊዜ ኑሮም በጣም ከበደባቸው ከቤታቸው ሽያጭ የተረፈውን
አንድ በአንድ ለትግስት መታከሚያ እና ለኪራይ ካደረጉት ወራት ተቆጠሩ እንኳን
ብር የሰው ልጅም አካል አልቆ እና እረግፎ መንምኖ ያልቃልና እጃቸው ላይ
ያለው ብር አንድ በአንድ ለቤት ኪራይ እና ለበፀሎት ህክምና ወጥቶ አለቀ።
አሁን ከድሮ በበለጠ ህይወት ከበደች ፊቷንም አዞረች በይበልጥ እና ደሞ
በእጥፉ ችግራቸው ልክ እንደተቦካ እና ኩፍ እንደሚል ሊጥ ወደላይ ወጥቶ
ተስፋቸው ደሞ ሊጡ ሲመለስ ያለው አይነት መመለስ በቀስታ እንደመተንፍስ
በቀስታ እንደመቀነስ በቃ ኑሮም እንዳልቦካ ሊጥ እንደመቆምጠጥ ሆነ።
፨ታዲያ ይህንን ኑሮ መኖር ለማነው ቀላል ለትንሿ ፅናት ነው ወይስ የአይን
ብረሀኗን እና የመራመድ ፀጋዋን ለተገፈፈችው በፀሎት እ እህ መልስ የለም።
ፅናት ከትምህርቷ ስትመለስ እንፖቴቶ እና ፓስቲ በመስራት እና በመሽጥ ከዛም
ብር በማጠራቀም ለሆዳቸው ተርፍለች። ሊባኖስ አትረዳቸው ነገር ግን እሷም
እረጋፊ ሳንቲም የሊላት ደሀ ነች።
፨ ፅናት መጀመሪያ ሰሞን ለአንድ ቀን የሊባኖስን ስፈር አይታውዋለች
በመጀመሪያ ቀን ግን ሊባኖስ ፅናት እንድትገባ አልፈቀደችላትም። ሁሌም ቢሆን
የሊባኖስን ቃልን መቼም አትረሳም። ሊባኖስ ለፅናት ብረታት ሆናታለች።
፨ሊባኖስ አሁን የት እንዳለች ሳትናገር ድራሿ ጠፈቶል።ይህ ነገር ፅናት እና
በፀሎትን ቢያሳስባቸውም መፍትሄ አላገኑም ፅናት ትኖራለች ብላ የምታስብበት
ቦታ ሁሉ ፈለገቻት ነገር ግን ሁሉም ሊባኖስ ቋሚ መኖሪያ እንደሌላት እና
ባገኘችበት እንደምታድር ከመንገር ውጪ ማንም ምንም አላለም። እንደውም ስለ
ሊባኖስ ስትጠይቃቸው ፍረሀት እና ድንጋጤ ከፊታቸው ይነበባል። ፅናት ለምን
ስለ ሊባኖስ ሲነሳ እንዲህ እንደሚሆኑ ግራ ገባት።
፨ ሊባኖስ ከጠፋች ወራት ተቆጥሯል በእነዚህ ወራት ውስጥ ግን አንድ ስው
አግኝታ ነበር። ሰውየው ሊባኖስን በደንምብ እንደሚያውቃት እና ሊባኖስ ማለት
የመስቀል ወፈ እንደሆነች ማንም እሷን ፈልጎ ማግኘት እንደማይችል እና ተመልሳ
ብትመጣ እንኳን ከእሷ እንድትረቅ ሊባኖስን በደንብ እንደሚያውቃት እና
መጀመሪያ ሰውን መላክ ሆና ቀረባ ከዛም በአይኗ ሀይል ደም ግባት ውስጥ
ገብታ ሞትን የሚያስመኝ ስቃይ እንደምታሰቃይ ፤ ውሎዋ የመቃብር ቦታ ላይ
እንደሆነ የሞቱ ሰዎችን እንደምትወድ በቁም ያለውን ሰውም ገድላ ወደ እሪሳነት
መቀየር ለእሷ በቁም ላለው ሰው ውለታ እንደሰራች አንደምትቆጥረ ነገራት።
ፅናት አማተበች በጣምም ፈራች ሰውየው የሚነግራት ፊልም ይሁን እውነት
ቀልድ ይሁን ውሸት ግራ ገብቷታል ግን ደሞ ጨንቋታል።
፨ ሊላው ፅናትን ሰላም የነሳት ከድሮ ሰፈራቸው አንዲት ሴት መጥታለች ሴቲቶ
የእነሱ ሰፈር ባለ ጫት ቤት ሰውዬ አያት ናት ድሮ ሰፈራቸው የሚያወሩትን ሁሉ
ለባለ ጫት ቤቱ ስትነግረው ጫት ቤቱ ለደንበኖቹ ደንበኞቹ ለሴተኛ አዳሪዎች እና
ለሚስቶቻቸው ተናግረው ወሬውን ነዙት።
፨አንድ ቀን ፅናት በአንድ ጀንበር እራስዋን ጠንካራ ውስጧንም ጠንካራ አድርጋ ተነሳች። ጊዜው የ10ረኛ ክፍልን ፍተና ተፈትና በጥሩ ውጤት አልፋ ክረምት ላይ
297 views14:42