2022-01-19 23:00:12
ምርጥ ትውልዶች
============
በዑመር (ረድየሏሁ አንሁ) ዘመን ሶስት ወጣቶች አንድ ስውዬን ጎትተው
በማምጣት ያዐሚረል ሙእሚኒን ይህ ሰው አባታችንን ገድሏል ሀድ/
ቅጣት/ እንደትወስንበት እንሻለን በማለት ተናገሩ።
ለምን ገደልክ ? ሲሉ ዑመር ጠየቀ
‹‹ እኔ የግመል እረኛ ነኝ አንደኛው ግመሌ የአባታቸው መሬት ላይ ካለ
ዛፍቅጠል ቀንጥሶ ሲበላ አባታቸው ድነጋይ ወርውሮ ሲመታው ግመሌ
ሞተ እኔም እሱ የወረወረውን ድንጋይ አነስቼ ስወረውር መታሁትና ሞተ…
ሲል ተናገረ።
‹‹እንደዛ ከሆነ ቅጣት እወስንብሃለሁ! አሉ ዑመር ።
‹‹እሺ ሦስት ቀናትን አቆየኝ …… አባቴ ሲሞት ለኔና ለወንድሞቼ የተወው
ከንዝ/የተደበቀ ሃብት/አለ እኔ አሁን እዚሁ ከሞትኩ ከንዙም ይጠፋል
ወንድሞቼም ይጠፋሉ (ይቸገራሉ) ስለዚህ
ፍቀድልኝና ሄጄ ልምጣ አለ።
ታዲያ እሰክትመለስ ዋስ የሚሆንሀ ማነው? በማለት ዑመር (ረድየሏሁ
አንሁ) ጠየቁ።
ሰውዬው የተሰበሰቡትን ሰዎች ተመለከተ የሚያውቀው የለም……
የእያንዳንዱን ፊት ተመለከተ እና ያ ሰውዬ ሲል ጠቆመ።
ያ አባ ዘር ለዚህ ሰው ዋስ ትሆናለህ? በማለት ዑመር (ረድየሏሁ አንሁ)
ጠየቁ
አዎን ያ አሚረል ሙእሚኒን በማለት መለሰ።
ይህ ሰው ካመለጠ ቅጣቱ አንተ ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን አታውቅም
እንዴ? ሲል ዑመር ተገርሞ ጠየቁ ግድ የለም ያአሚረል ሙእሚኒን እኔ
ዋስ እሆነዋለሁ …. ሲል አቡዘር መለሰ። ሰውየው ሄደ።
አንድ ቀን አለፈ….ሁለተኛው ቀን ተከተለ…በሦስተኛው ቀን ሰውየው
ካልመጣ ቅጣቱ አቡዘር ላይ ስለሚፈፀም ሰዎች ተጨነቁ ……… ሆኖም
የዛን ቀን ከመግሪብ በፊት ያሰው እያለከለከ መጣ እንደደከመው
ገፅታው መስካሪ ነበር። ከዑመር (ረድየሏሁ አንሁ) ፊት ለፊት መጥቶ
በመቆም
‹‹ከንዙን ለወንድሞቼ እና ለእናቴ ወንድሞች አስረክቤ መጣሁ አሁን
በቁጥጥርህ ስር ሆኛለሁ ቅጣቱን ፈፅምብኝ በማለት ተናገረ።
ዑመር (ረድየሏሁ አንሁ) ተገረመ በዚያው ማምለጥ የምትችል ሆነህ
እንዴት ተመለስክ? ሲል ጠየቀው።
‹‹ ሰዎች ዘንድ ቃል አክባሪነት/ጠባቂነት/ጠፋ እንዳይባል ፈርቼ ነው››
በማለት መለሰ።
ዑመር ወደ አቡዘር ዞሮ ይህን ሰው እንዴት ዋስ ሆነከው? በማለት ጠየቀ
‹‹እኔማ ዋስ የሆነኩት በሰዎች ዘንድ ኸይር (መልካም ስራ) ጠፋ
እንዳይባል ፈርቼ ነው›› ሲል አቡ ዘር መለሰ። በሁኔታው
የሟች ልጆች ልብ ተነካ በቃ አፉ ብለነዋል ቅጣቱ እንዳይፈፀምበት ሲሉ
ተናገሩ
ዑመር (ረድየሏሁ አንሁ) ለምን? ሲል ጠየቃቸው…..‹‹እኛ ደግሞ
በሰዎች መሃል ይቅር መባባል ጠፋ እንዳይባል እንፈራለን›› አሉ
ሱብሃነላህ
እኔ ደግሞ ሰዎች የሰሙትን አያደርሱም እንዳይባል ሰጋሁ እና
ነገርኳችሁ፡፡ @subhanela1
1.2K viewsሚ , 20:00