Get Mystery Box with random crypto!

የእግር ሽታ የእግር ሽታ ያስቸግሮታል? አንግዲያዉስ የሚከተሉትን ይተግብሩ! ሁሌም እግሮችዎና የእ | St. Urael Internal Medicine Clinic

የእግር ሽታ

የእግር ሽታ ያስቸግሮታል? አንግዲያዉስ የሚከተሉትን ይተግብሩ!
ሁሌም እግሮችዎና የእግሮችዎ ጣቶች ዉስጥ ንፁህና ደረቅ ይሁኑ።

መተግባር የሚገባዎ
እግርዎን ቢያንስ በቀን አንዴ መታጠብ ( ከተቻለ ፀረ- ባክቲሪያ የሆኑ ሳሙናዎችን ይጠቀሙ)
እግርዎ ላይ ደረቅ ቆዳዎች ካሉ ያስወግዱ እንዲሁም የእግር ጥፍርዎን ያሳጥሩ፥ በንፅህናዉንም ይጠብቁ
የእግር ላብ መቀነሻ ፓዉደሮችን አሊያም መድሃኒቶችን ይጠቀሙ
የረጠበ ጫማ ካለዎ መልሰዉ ከማድረግዎ በፊት መድረቁን ያረጋግጡ
አየር በቀላሉ ሊያዘዋዉሩ የሚችሉ ጫማዎችን ይጫሙ፤ እንዲሁም ከተፈጥሮ ነገሮች እንደ ከጥጥ ወይም ቆዳ የተሰሩ መጫሚያዎችን ይምረጡ።

ማድረግ የለለብዎ
በጣም ጠባብ ጫማዎችን አያድርጉ
እርጥበት ባለባቸዉ ቦታዎች ለምሳሌ በመዋኛ ና ጂም ቦታዎች ባሉ ሻወር ቤቶች አካባቢ በባዶ እግር አይጓዙ
የእግር ካልሲ በተከታታይ ከሁላት ቀናት በላይ አያድርጉ፤ ከተቻለም ጫማዎችንም በየሁለት ቀኑ ለመቀያየር ይሞክሩ።
የአግር ሽታ እንዲከሰት የሚያደርጉ መንስኤዎች
ለእግር ጠረን መከሰት ዋነኛ መንስኤዎች የእግር ላብና በእግርዎ ላይ ባክቴሪያ መከማቸት እንዲሁም እንደ አትሌቲክ- ፉት ያሉ የፈንገስ በሽታዎች ናቸው።

የእግርዎ የላብ መጠን ሊወስኑ የሚችሉ ነገሮች
ሞቃት የአየር ፀባይ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
ቀኑን በሙሉ ቆሞ መዋል
የሰዉነትዎ ክብደት ከፍተኛ መሆን
የሆርሞን ለዉጦች፦ በጉርምስና፣ በማረጥና በእርግዝና ወቅት የሚከሰቱ
መድሃኒቶች፦ ልድብታ የሚሰጡ
ከመጠን ያለፈ የሰዉነት ላብ እንዲፈጠር የሚያደርጉ ችግሮች ናቸዉ።

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/