Get Mystery Box with random crypto!

አስገራሚዉ የመፅሀፍ ቅዱስ ትረካ -=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=- መፅሀፍ ቅዱስ በ | 1 ነት ጀምአ

አስገራሚዉ የመፅሀፍ ቅዱስ ትረካ
-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-

መፅሀፍ ቅዱስ በማቲዮስ ምእራፍ "15" አንቀፅ ቁጥር ከ "21" እስከ "28" ድረስ አስገራሚና ቀፋፊ ትእይንቶች ያስቃኘናል ታሪኩን እካቹ:-

ማቴዎስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ ኢየሱስም ከዚያ ወጥቶ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና አገር ሄደ።
²² እነሆም፥ ከነናዊት ሴት ከዚያ አገር ወጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረኝ፤ ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞአታል ብላ ጮኸች።
²³ እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ በኋላችን ትጮኻለችና አሰናብታት እያሉ ለመኑት።
²⁴ እርሱም መልሶ፦ ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ።
²⁵ እርስዋ ግን መጥታ፦ ጌታ ሆይ፥ እርዳኝ እያለች ሰገደችለት።
²⁶ እርሱ ግን መልሶ፦ የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም አለ።
²⁷ እርስዋም፦ አዎን ጌታ ሆይ፤ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ አለች።
²⁸ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ፦ አንቺ ሴት፥ እምነትሽ ታላቅ ነው፤ እንደወደድሽ ይሁንልሽ አላት። ልጅዋም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ዳነች።

ታሪኩን እንዳነበባቹት በመጀመሪያ ከነናዊቷ (ከነአናዊቷ) ሴትዮ እየሱስን በአንቀፅ "22" ላይ ልጇን እንዲያድንላት እርር ብላ ጮሀ እንደለመነችዉ ያስረዳናል

ከዛ ወረድ ብለን አንቀፅ "23"ን አስተዉለን ስናነበዉ አሁን ላይ ክርስቲያኖች አዛኝ የሚሉት እየሱስ እንደዛ እየጮኸች የምትለምነዉን #ከነናዊት ሴት ያለ አንዳች ሀዘን ምንም ሳይመልስላት ፀጥ እንዳላትና ደቀ መዛሙርቶቹ ደግሞ <<አረ አንተ ሰዉ እዘን>> የሚሉት በሚመስል ሁኔታ ሴትየዋን እንዲያስተናግዳት ሲለምኑት እናያለን

ወደ አንቀፅ "24" ወረድ ስንል ደግሞ እየሱስ ደቀ መዛሙርቶቹ ቀርበዉ #ከነናዊቷን ሴትዮ የጠየቀችዉን እሺ ብሎ እንዲያሰናብታት ለጠየቁት ጥያቄ <<ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላኩም>> ብሎ በመመለስ እርሱ የተላከዉ ለእስራኤሎች ነዉና ሴትየዋ ደግሞ እስራኤላዊ ሳትሆ #ከነናዉ ስለሆነች ስለሷ እንደማይመለከተዉ ያስረዳቸዋል

በአንቀፅ "25" ደግሞ ሴትየዋ ልመናዋን አጡፋዉ ሰግዳ ተደፍታ ለመነችዉ

ከዚያም በአንቀፅ "26" እየሱስ እንዲ እርር ብላ ለምትለምነዉ #ለከነናዊቷ ሴትዮ ጥንብ የሆነዉ ዘረኝነት የተጠናወተዉ ለጆሮ የመከብድ አፀያፊ ንግግር እዲህ በማለት ተናገራት ተናገራት:- "የልጆችን እንጀራ ይዞ ለቡችሎች መጣል አይገባም" እንግዴ እዚህችጋ በአዉደ ንባቡ በግልስ እንደምንረዳዉ እየሱስ የራሱን ዘሮች እስራኤላዊያንን "ልጆች" ብሎ ጠርቶ ከነሱ ዉጪ የሆኑት "ቡችላ" እያለ ነዉ ይህ ደግሞ ንፁህ አእምሮ ላለዉ ሰዉ ግልፅና መራር የሆነ ዘረኝነት ነዉ።

ወደ አንቀፅ "27" ወረድ ስንል ደግሞ ሴትየዋ እንዲህ በማለት ለመነችዉ:- አዎን ጌታ ሆይ፤ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ” የችግሯን ብችላ የሚለዉ መጠሪያዋን ተቀብላ ነገርግን ቡችላ ከቤቱ አባቶች የወዳደቀዉን ፍርፋሪ እንደሚበላ አስረድታ ፍርፋሪ ይገባኛል ስትል ለመነችዉ

በአንቀፅ"28" ደግሞ እንደ ክርስቲያኖች እምነት የአለማት ጌታ የተባለዉ እየሱስ ይዞት ከነበረዉ አላድንሽም የሚል የተሳሳተ አቋም በአንዲት ተራ ሴት ተሸንፎ ልጇን እንዳዳነላት ይነግረናል

ማጠቃለያ:-
""" """" ""
እንግዲ እንዳያቹት ከማቲዎስ "22" አንስቶ እስከ "28" አንድ አምላክ ከሚባል አካል የማይጠበቁ ቡዙ ነገሮችን አይተናል

◆ለምሳሌ አያዝንም ይህንንም ሴትየዋ እሪይ ብላ ስትጮህ ሰዉ መቶ እስኪለምነዉ ፀጥ በማለት አሳይቶናል።

እና የማያዝንን አካል ጌታ ብላቹ የምታመልኩት ምን ዋስትና አግኝታቹ ነዉ?

◆ለላዉ ደግሞ ዘረኛ ነዉ እሱንም የራሱን ዘሮች ልጆ ብሎ ጠርቶ ሌሎቹን ዘሮች ደግሞ ቡችላ በማለት አሳይቶናል

እና ክርስቲያኖች ሆይ የራሱን ዘር እስራኤሎችን ልጆች ብሎ እናንተን ቡችላ እያለ የሚያዋርዳቹን እንዴት ጌታ ብላቹ ታመልካላቹ?

◆እንደገና ደግሞ እየሱስ እንሚሳሳትም አይተናል እሱንም ሴትየዋን አላድንም ብሎ ሲከራከር ቆይቶ ኋላ ላይ በመልስ ምቷ ተረቶ #ፍርፋራ እንደሚገባት አምኗል እንግዲ አስቡት ይህቺ ሴትዮ እንዲ ባትከራከረዉ ከእስራኤል ዉጪ ላሉቱ ዜጎች የመልእክቴ ፍርፋሪ እንኳ አይገባቸዉም ብሎ ተሳስቶ ይኖር ነበር በዚ አይነት
ማን ያዉቃል አልተከራከሩትም እንጂ አሁንም ስንት የተሳሳተባቸዉ ነገሮች ይኖራሉ

ክርስቲያኖች ሆይ እንዴት የሚሳሳትን ጌታ ታመልካላቹ የሚሳሳት ከሆነ የገነት የሆንከዉን ተሳስቶ ወደ ሲኦልምኮ ሊነዳህ ይችላል ምን ዋስትና ይዘህ ነዉ?

◆ሌላዉና የመጨረሻዉ ደግሞ ከእስራኤል ዉጭ ያላቹ የእየሱስ አማኞች ቡችላ እንደመሆናቹም መጠን የእየሱስ መልእክት ለናንተ አይደለም ምናልባት ከመልእክቱ ባለቤቶች ከእስራኤላዉያን የወዳደቀዉን ፍርፋሪ ካልሆነ በቀር

እኔ የምላቹ ለናንተ የማይገባ ቦታ ሄዳቹ ፍርፋሪ ከምትለቃቅሙ ለአለም ህዝብ ሁሉ ዘር ሳይለይ ተገቢ የሆነዉን እስልምናን ተቀብላቹ ሰላም ለምን አትሆኑም?

ኢብኑ አብራር

ቻናላችንን ለመቀላቀል

https://t.me/joinchat/YlCprY3U05wzNWY8