Get Mystery Box with random crypto!

እንግዲህ ወገብን ጠበቅ ማድረግ ነው። ህወሀት እያሟሟቀ ነው። ተንደርድሮ ወደ ማይጠብሪ ለመግባት ከ | የአማራ ድምጽ

እንግዲህ ወገብን ጠበቅ ማድረግ ነው። ህወሀት እያሟሟቀ ነው። ተንደርድሮ ወደ ማይጠብሪ ለመግባት ከሽሬ አሰፍስፎ እየጠበቀ ነው። በማይጠብሪ ግንባር የነበረው ከ15ሺህ በላይ የአማራ ልዩ ሃይል በኦሮሚያ ብልጽግና ውሳኔ መሰረት ከአከባቢው እንዲነሳ ተደርጎ አብዛኛው ወደተለያዩ አካባቢዎች ተበታትነዋል። ቀድሞውኑ ዓላማውም ይኸው ነበረ። ህወሀት ጥይት ሳያስጮህ ፈንዲሻ እየበተነ ማይጠብሪን በቅርቡ በእጁ እንደሚያስገባ ይጠበቃል። በራያ ያለውም ተመሳሳይ ነው። ዛሬ ''የደቡብ ትግራይ'' ዋና አስተዳዳሪ የአማራ ልዩ ሃይል ከራያ መልቀቁን በገለጹበት መግለጫቸው ቀጣዩ ስራቸው ''በአማራ ልዩ ሃይል የተዘረፉትን ተቋማት ማስተካከል'' ነው በሚል የራያን እጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ይፋ አድርገዋል።

የብልጽግና ሚዲያዎች አሁንም አሳሳችና ቅጥፈት የተሞላበት ፕሮፖጋንዳዎችን እያሰራጩ ነው። ህዝቡን ያስበሉት የአማራ ክልል አመራሮች በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ እያሉ ለኦሮሚያ ብልጽግና አለቆቻቸው ያላቸውን ታማኝነት እስከቀራኒዮ እንደሚደርስ በመግለጽ ላይ ናቸው። የህዝብን ፍላጎት በዚህ መልኩ ማፈን አይቻልም። በጉዳዩ ላይ ያነጋገርኳቸው የአማራ ክልል የአንድ ቢሮ ሃላፊ '' የወልቃይትና የራያ ጉዳይ የህዝብ ነው። ልዩ ሃይል በመኖሩ የተጀመረ ንቅናቄ አይደለም። ወደፊትም ከህዝብ ጋር የሚኖር አጀንዳ ነው። ህዝቡ ወስኗል። በሃይል የሚደረግ ነገር ካለ መጨረሻውን አብረን እናያለን'' ብለውኛል። እኔም በዚህ አምናለሁ። የኦሮሚያ ብልጽግና አይኑን ጨፍኖ የመጠቅለልና የመሰልቀጥ ህልሙን ከዳር ለማድረስ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እየደረስኩ ነው የሚል መልዕክት በእጅ አዙር እያስተላለፈ ይመስላል። ሁሉንም ጊዜ የሚያሳየን ይሆናል።

አንድ የኦሮሚያ ብልጽግና ዲፕሎማት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በአንድ የወዳጃሞች ድግስ ላይ እንዲህ አሉ '' ህወሀትን ጥርሱን አራግፈነዋል። ከእንግዲህ ለእኛ ፈጽሞ ስጋት አይሆንም። አንድ ዙር ጦርነት ከአማራው ጋር ይቀረናል። ከዚያ በኋላ በማዕከላዊው መንግስት ለረጅም ጊዜ በስልጣን ለመቆየት የሚያስችለውን ማረጋገጫ እናገኛለን።'' እንግዲህ ሁሉንም ወደፊት የምናየው ይሆናል። ሌሎች ክልሎችም ልዩ ሃይላቸውን እየፈቱ ነው የሚለውን ደረቅ ፕሮፖጋንዳ እየተጋተ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ነገሮችን በትዕግስትና በጥሞና እየተከታተለው እንዳለ ተስፋ አደርጋለሁ። መልካም የፋሲካ በዓል!