2022-04-23 14:06:19
የፋሲካን በዓል ምክንያት በማድረግ ለተቸገሩ ወገኖች ለበዓል የሚያስፈልግ ድጋፍ ተደረገ
ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 15/2014 ዓ.ም (ደሬቴድ) በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የሆሳዕና ቃለ ሕይወት ቤተከርስቲያን የፋሲካን በዓል ምክንያት በማድረግ ለተቸገሩ ወገኖች ለበዓል የሚያስፈልጉ ድጋፎችን አደረገች።
የሆሳዕና ቃለ ህይወት ቤተ ክርስቲያን መሪ አቶ ዮናስ ዱባለ በበዓሉ ስጦታ ወቅት እንደተናገሩት እምነቱ እንደሚያዘው የተቸገሩትን መርዳት የአምልኳችን አንዱ ክፍል በመሆኑ በተለይ በበዓላት ወቅት ቤተክርስቲያኗ ልዩ ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል ።
በጎነትንና ቸርነትን ማድረግ በበዓላት ወቅት ብቻ ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባር መሆን አለበት ያሉት አቶ ዮናስ ቤተ ክርሰቲያኗ በተለያዩ የኑሮ ችግር ላይ ያሉትን ወገኖች በፍቅርና ርህራሄ አገልግሎት ዘርፍ ድጋፎችን በቋሚነት ታደርጋለች።
የደሃ ደሃ የሆኑና ተንቀሳቅሰው ሊሰሩ የሚይችሉ ሰዎችን በመለየት በራስ ማስቻል ኘሮግራም ስልጠና በመስጠት ና የገንዘብ ድጋፍም በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ቤተ ክርስቲያኗ እየሰራች ትገኛለች ብለዋል።
ለ2014 የፋሲካ በዓል ከ3 መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የእህል ዱቄትና የቅርጫ ስጋ ድጋፍ መደረጉንም በመግለፅ።
በሆሳዕና ቃለ ህይወት ቤተ ክርስቲያን ፍቅርና ርሆራሄ አገልግሎት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ተፈራ ኤርገኖ በበኩላቸው የዘንድሮውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ ለ250 አረጋዊያን ፣አካል ጉዳተኞች ና በተለያዬ ችግር ላይ ላሉ ወገኖች የ25 ክ.ግ የእህል ዱቄትና የቅርጫ ስጋ ድጋፍ መደረግ መቻሉን ገልጸዋል።
ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ https://www.facebook.com/southradioandtelevisionagency/photos/pcb.1477396089386319/1477395152719746/
995 views11:06