Get Mystery Box with random crypto!

Spirit Life Movement/leader sol/

የቴሌግራም ቻናል አርማ spirit_life_leader_sol — Spirit Life Movement/leader sol/ S
የቴሌግራም ቻናል አርማ spirit_life_leader_sol — Spirit Life Movement/leader sol/
የሰርጥ አድራሻ: @spirit_life_leader_sol
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 435
የሰርጥ መግለጫ

በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠውን እግዚአብሔርን በመንፈስ ቅዱስ ተረድተን ታግዘን በምድር የእግዚአብሔርን መንግስት ህያው እናደርጋለን።
@Sol_LifeGiver

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-24 10:48:04 Success in Practice
part 3
ስኬት ሲተገበር ፫
By Nati
@Spirit_Life_leader_Sol
@Spirit_Life_leader_Sol
123 viewsedited  07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 10:47:28 Success in Practice
part 2

ስኬት ሲተገበር
By Nati
@Spirit_Life_leader_Sol
@Spirit_Life_leader_Sol
120 viewsedited  07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 20:36:13 Success in Practice
part 1
ስኬት ሲተገበር ፩
By Nati

@Spirit_Life_leader_Sol
@Spirit_Life_leader_Sol
228 viewsedited  17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 14:38:31 ዘጠነኛ ፡ በተደጋጋሚ የምታያቸው ፊልሞች ውስጥ ሁሉ የተመሳሳይ ፆታን ግንኙነት (homosexuality) የሚያበረታቱ ክፍሎች እንዳሉት አስተውለሀል? በጣም የምትወደው ፣ ጥሩና ደግ የሆነው ገፀ-ባህርይ ከተወሰነ ክፍል በኋላ ጌይ መሆኑን አስተውለሃል? ሆሊዉድ ይህንን ሆን ብሎ በፊልምና በሙዚቃዎች እያስፋፋ መሆኑ ገብቶሃል? አእምሮህ ላይ ምን እየሳሉብህ ይመስልሃል? የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን እንደ ኖርማል እንድትቀበለው አጓጊ ታሪኮችን እያነሱ ነፍስህ የሚያስሯትን ፀሐፊዎች አስተውለሃል። ውድ ወዳጄ ንቃ! ማምለጥ ትችላለህ።

አስረኛ ፡ ገንዘብ የሚረዳህ ፣ የሚያጫውትህ ፣ የሚያስፈልግህን ሁሉ የሚያሟላልህ ሰው ሁሉ ጋር ሰውየውን ለማስደሰት አብረኸው መተኛት እንዳለብህ ለምን አሰብክ ? ውድ ወዳጄ! አብረኸው መተኛት ግዴታ አይደለም። መንቃት አለብህ። ይህ ሲባል በቅንነት ከንፁህ ልብ መልካምን የሚያደርጉልህን አይጨምርም።

አስራ አንደኛ ፡ "እስኪ ይህንንም ላይፍ ልሞክረው" ብለህ ገብተህበት ሊሆን ይችላል። ሞክረህ አየኸው አይደል? ምን ያህል አስጠሊታ እንደሆነ ፣ ፀፀት የሞላበት እንደሆነ ፣ ወጣቶች ራሳቸውን ሲያጠፉበት ፣ ተስፋ አስቆራጭ እንደሆነ ፣ ሁሌም የፍርሃት እና ተደብቀህ የምትኖረው የጨለማ ህይወት መሆኑን አየኸው አይደል? ታዲያ ምን ትሰራለህ? ማን ነው መውጣት አትችልም ያለህ? እንደ ገባሃት መውጣት ትችላለህ። እውነት ነው ቆራጥነት እና ትግል ይጠይቃል ፤ ነገር ግን ተስፋ አትቁረጥ። መውጣት ይቻላል።

አስራ ሁለተኛ ፡ ለምን ውሎህን ፣ ሰፈርህን ፣ ጓደኞችህን ፣ አካባቢህን ፣ ትምህርት ቤትህን አትቀይርም ወይም ለዚህ ነገር ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ላይ ለምን ትገኛለህ? ከዚህ ጋር ተያይዞ ፌስቡክህን ፣ የወሲብ ቪድዮ የምትመለከትባቸው ሳይቶችህን ፣ የቴሌግራም ግሩፕህን ለምን አትቀይርም? ሚዲያ ትልቅ ኃይል ስላለው አትከተለው። ለምን ከጓደኞችህ ጋር ክለብ መውጣት ፣ መጠጣት ፣ መቃም ፣ አብሮ ማደር አታቆምም? ከህይወትህ እኮ አይበልጥም። በተበሳጨህ ቁጥር የግድ መጠጣት እና ከወንድ ጋር ማደር እንዳለብህ ማን ነው የነገረህ? አተረጓጎምህን ቀይር ፤ ህይወትህ ይቀየራል።

አስራ ሦስተኛ ፡ በዚህ ህይወት ውስጥ ያሉ ሰዎችን ለምን የህይወትህ ሞዴል አድርገህ ትከተላለህ? አኗኗራቸውን ፣ አለባበሳቸውን ፣ አነጋገራቸውን ፣ ፊልማቸውን ፣ በጠቅላላ ስታይላቸውን ለምን ትከተላለህ? አንተ እኮ ለዚህ ክፉ ህይወት አልተፈጠርክም። መንገድህን አስተካክል።

አስራ አራተኛ ፡ " አብሬያቸው ወሲብ የፈፀምኳቸው ሰዎች ቪድዮ ቀድተውኛል ፤ ስለዚህ እያስፈራሩኝ ስለሆነ በዚሁ ህይወት ሳልወድ በግዴ እቀጥላለሁ" በሚል ህይወትህን ለምን እስረኛ ታደርጋለህ? አብዛኛው ሰው ባለፈ ህይወቱ የብዙ ነገር ሱሰኛ እና እስረኛ ነበር። ጌታ ኢየሱስ ነፃ አውጥቶት እንጂ። በዚህ ነገር እያስፈራሩህ ታስረህ ከምትቀር ወደ ጌታ መጥተህ ህይወትህን ብትቀይር ይሻልሃል። ጌታ ደግሞ ያለፈ ውድቀትህን ደግሞ አያስበውም። መውጫ መንገድን ያዘጋጅልሃል።

የመጨረሻው ፡ ይህ ነገር የመናፍስት ጥቃት ስለሆነ ነፃ መውጣት ትችላለህ። እንዲህ አይነት መንፈስ The spirit of perversion (ለዋጭ መንፈስ) ተብሎ ይጠራል። ይህ መንፈስ በተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ፣ ፆታቸውን በሚቀይሩ እና ከዚህ ጋር በሚመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ የሚሰራ መንፈስ ነው። ውድ ወዳጄ! እንዲህ ነህ ብሎ ያሳመነህ ይህ መንፈስ ነው። ነፃ መውጣት ትችላለህ። ኢየሱስ ከዚህ እስራት ይፈታሃል። ሰዎች (የዚህ ነገር አቀንቃኝ የአጋንንት መልዕክተኞች) የሚሉህን አትስማ። አንተ የተወደድክ ፣ ዋጋ የተከፈለብህ ታላቅ ሰው ነህ። እግዚአብሔር ይወድሃል ፤ በዚህ ህይወት ታስረህ እንድትቀጥል አይፈልግም። ከፊትህ ትልቅ ተስፋ አለህ ፤ እስከ መቼ በምስጢራዊ ህይወት ታስረህ ትመላለሳለህ? ዛሬ አምልጥ።

ውድ ወዳጆቼ! መልዕክቱን ስፅፍ በወንድኛ ብቻ የፃፍኩት ቢመስልም በዚህ ነገር እስረኛ የሆኑ ሴቶችንም ያጠቃልላል። ይህ መልዕክት ነፃ ለመውጣት አንድ ደረጃ (step) የሚያስኬድ ስለሆነ ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ እንድትረዱኝ በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ።

አመሰግናለሁ ፤ እወዳችኋለሁ!!

ፓስተር ተስፋጽዮን ዳዊት
ሐሙስ ግንቦት 18/2014 ዓ.ም

ይህንን መልዕክት ለሌሎች ሼር በማድረግ ነፃ ያውጧቸው ፤ አስተያየትዎንም ይፃፉ።
505 views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 14:38:31 'የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ (homosexuals) ነን' ብለው ስለሚያስቡ ሰዎች ምን አስባለሁ?!

በልጅነት ባደኩበት በሐዋሳ ከተማ ከምሰማቸው ነገሮች መካከል "እከሌ እከሌን አደረገው" ተብሎ በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ወንዶች ልጆች መካከል ስለተደረገ ወሲብ እሰማ ነበር። የዚያኔ በልጅነት እንደ ትልቅ ጉዳይ ስለማይታሰብ እነኚያ ወንድ ልጆች ሲያድጉ ደንበኛ የሴት አፍቃሪ ሆነው እና አግብተው ፣ ልጅ ወልደው የተረጋጋ ትክክለኛ የፍቅር ህይወት ሲኖሩ አይቻለሁ። መቼም አንድ ነገር በልጅነትህ ወይም በሆነ አጋጣሚ አደረከው ማለት አንተ እንደዚያ ነህ ማለት አይደለም ፤ መለወጥ ትችላለህ። ይህ ነገር እያደግን ስንሄድ ግን ለጆሮ የሚሰቀጥጥ አስነዋሪ ነገር እንደሆነ ፤ መጽሐፍ ቅዱስም ላይ ከባድ ኃጢአት መሆኑን ሳውቅ እነኚያ ልጆች ያንን በልጅነት አእምሯቸው ቢያውቁት ኖሮ " እኔ በቃ እንዲህ (ጌይ) ነኝ" ብለው ይቀጥሉበት ነበር ብዬ አስባለሁ። እንኳንም አላወቁት። ምክንያቱም አእምሮ ከባድ ተርጓሚ ማሽን ስለሆነ ማለት ነው።

ውድ ወዳጆቼ! ይህንን አስተሳሰብ በጣም ከባድ የሚያደርገው በአጋንንት ትምህርት በደንብ እየተቃኘ (indoctrinate እየተደረገ) ስለመጣ ነው። ዛሬ ትምህርቱ ሲመታ ይህ መንፈስም እየተመታ ይሄዳል።ምናልባት በዚህ ህይወት ውስጥ አለሁ ብለው የሚያስቡ ሰዎች ዛሬ በተወሰነ መልኩ ነፃ ሊወጡበት ይችላሉ ብዬ አምናለሁ።

ውድ ወዳጄ! " ወንድ ሆኜ ከሴት ይልቅ ሌላ ወንድ ይስበኛል" ብለህ አስበህ " ስለዚህ እኔ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ (gay) ነኝ " ብለህ አታስብ። በፍፁም አይደለህም። በአንዳንድ ሁኔታዎች ይህ ገጥሞህ ወደ ፍቅር ገብተህ ይሆናል። ለምሳሌ :- መጽሐፍ ቅዱስ ላይ “ዳዊትም ለሳኦል መናገሩን በፈጸመ ጊዜ የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ ታሰረች፥ ዮናታንም እንደ ነፍሱ ወደደው።” ይላል(1ኛ ሳሙኤል 18:1)። በሌላ ስፍራ ላይ ደግሞ “ወንድሜ ዮናታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨነቃለሁ፤ በእኔ ዘንድ ውድህ እጅግ የተለየ ነበረ፤ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅርህ ለእኔ ግሩም ነበረ።” ይላል ( — 2ኛ ሳሙኤል 1፥26)። ውድ ወዳጄ! ትርጉምህን አስተካክል ፤ ፍቅር ማለት ወሲብ ማለት አይደለም። ፍቅር የነፍስ ትስስር ነው። ዳዊትና ዮናታን የነፍስ ትስስር ነበራቸው ፤ በጣም ይዋደዳሉ ፤ እንደውም ከሴት ፍቅር ይልቅ የባሰ ነበር ፍቅራቸው ። አየህ ይህ ማለት የተመሳሳይ ፆታ ፍቅር ውስጥ ነበሩ ማለት አይደለም ። ይህንን ጥቅስ በተሳሳተ መንገድ በመተርጎም ዳዊትና ዮናታን gay ነበሩ የሚሉ እንዳሉ አውቃለሁ ። አንተ ግን አእምሮህን አስተካክል። ለነፃነትህ ነው የማወራው። ወደ ወንድ ስለተሳብክ gay ነህ ማለት አይደለም ፤ ወደ ሴት ስለተሳብሽ ሌዝቢያን ነሽ ማለት አይደለም። በጣም የምትወዳቸው ፣ ነፍስህ በእነርሱ የታሰረ ሰዎች በእርግጥም ሊኖሩ ይችላሉ። በዚህ ግራ አትጋባ። በህይወትህ እንደ ሞዴል የምትመለከታቸው ፣ አስተሳሰባቸው የሚማርክህ ፣ ጨዋታቸው ነፍስህን የሚገዛ ፣ መንፈሳዊ ህይወታቸው የሚስብህ ፣ ትሁት የሆኑ ፣ እንደ ዳዊት ጀግና የሆኑ ፣ የፍቅር ሰዎች የሆኑ ፣ ከራሳቸው ይልቅ ለሌሎች መልካምነት የሚኖሩ ፣ ወዘተ ሰዎች ነፍስህን ሊማርኳት እና ከነፍስህ ልትወዳቸው ትችላለህ። ያንን ወደ ሌላ አትተርጉመው።

ሁለተኛ ፤ ስትፈጠርም እንደዚህ ሆነህ ነው የተፈጠርከው (You're born gay) ብለው የነገሩህ ውሸት ነው። እንደዚህ አይነት ትምህርቶች በተለይ ሰለጠነ (ሰየጠነ) በሚባሉ አገሮች በትምህርት ስርዓታቸው ውስጥ አካተው ያስተምራሉ። ኢትዮጵያ ላይም ለማስገባት ተደጋጋሚ ጥረት እያደረጉ ነው ፤ ነገር ግን አይሆንም። ወዳጄ! በተደጋጋሚ ወደ ወንድ ስትሳብ "እኔ በዚህ መልኩ ነው የተፈጠርኩት" ብለህ ማሰብህ ሰይጣን ህይወትህን ፣ ፍፃሜህን ለማበላሸት የነገረህ ክፉ ትምህርት ነው። ውድ ወዳጄ! ፍቅር የመላመድ ጉዳይ ነው። አብረህ ከሴቶችም ጋር እያሳለፍክ በመጣህ ቁጥር እየተላመድክ ትመጣለህ። አስተሳሰብህን ቀይር ሴቶችንም ማፍቀር ትችላለህ። ውሎህን አስተካክል።

ሦስተኛ ፤ አንድ ጊዜ በተመሳሳይ ፆታ የመደፈር አደጋ ስለደረሰብህ የአንተ ህይወት ያ ነው ማለት አይደለም። አንዳንድ ጊዜ በቀለኛ በመሆን ያንን ህይወት ለመቀጠል ካሰብክ ዛሬ አቅጣጫህን ቀይር። ህይወት ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አይደለም። "የተደፈረች ሴት ሁሉ ሴተኛ አዳሪ ትሆናለች ፤ የተደፈረ ወንድ ሁሉ ወንደኛ አዳሪ ይሆናል" ያለህ ማን ነው? ወዳጄ ንቃ! አንተ ትልቅ ፍፃሜ ያለህ ሰው ነህ። ምንአልባት ስትደፈር የኤች አይ ቪ (HIV) ቫይረስ ተጠቂ አድርገውህ ሊሆን ይችላል። ወዳጄ! ማራዘሚያም ቢሆን እየተጠቀምክ የህይወት ግብህን እየፈፀምክ ቀጥል እንጂ "አንዴ ህይወቴ ስለተበላሸ የሌሎችንም ህይወት በማበላሸት እቀጥላለሁ" አትበል። ጌታ ኢየሱስ ደግሞ ከHIV በሽታም ቢሆን ይፈውስሃል።

አራተኛ ፤ በሴቶች እህቶችህ መካከል ያለ አባት በማደግህ የወንድ አኗኗር እንዴት እንደሆነ አላወቅህም ማለት አንተ ሴት ነህ ማለት አይደለም። አንዳንድ ጊዜ አካሄድህ (አክትህ) እንደ ሴት ስለመሰለ ሴት ነህ ማለት አይደለም። አንዳንድ ወንዶች አይተውህ " ሴታሴት ነህ" ስላሉህ አትቀበላቸው። አንተ ወንድ ነህ ፤ እንደ ወንድም አክት ማድረግ መለማመድ ትችላለህ። ህይወት ልምምድ ስለሆነ የማይቀየር ነገር የለም። ስጋህም ፣ ነፍስህም በባህሪያቸው ለማዳ ናቸው።

አምስተኛ ፤ እናትህ ሴት ልጅ መውለድ እየፈለገች ወንድ ልጅ በመውለዷ እንደሴት ልጅ እየጠራችህ ወይም እንደሴት ልጅ እያለበሰችህ ስላደግህ ፣ የሰፈርም ሰዎች እንደሴት ስለጠሩህ አንተ ሴት ነህ ማለት አይደለም። ዛሬ አስተሳሰብህ ላይ ሰብረህ መውጣት ትችላለህ። አንተ ወንድ ነህ። ለራስህ ደጋግመህ እንዲህ ብለህ ተናገር። " እኔ ወንድ ነኝ እንጂ እነርሱ እንዳሉኝ ሴት አይደለሁም!! "

ስድስተኛ ፤ ድንገት የወንድ ለወንድ የወሲብ ፊልም አይተህ ወይም ፅሑፍ አንብበህ ከጓደኛህ ጋር በዚያ ኃጢአት ወደቅህ ሊሆን ይችላል። ይህ ማለት ግን አንተ ሁሌም እንደዚያው ነህ ማለት አይደለም። አንዴ ያመነዘረ ሁሌም አመንዝራ ሆኖ ይቀጥላል ያለው ማን ነው? ወዳጄ ነቅተህ አምልጥ። ከዚህ ጋር ተያይዞ ፌስቡክ ላይ ወይም በሌላ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተዋወቅኸው ሰው አብሮህ ለመተኛት ሲጋብዝህ እንዴት ተንደርድረህ ትሄዳለህ? እባክህ አንተ ልጅ ተረጋጋ። ለወሲብ የፈለገህ ሁሉ ይወድሃል ማለት አይደለም። ተሳስተህም ወሲብ ፈፀምክ ማለት አትወጣም ከዚህ ህይወት ማለት አይደለም።

ሰባተኛ ፡ ወንድ ጓደኛህ " ሴት ብትሆን አገባህ ነበር " ስላለህ እውነት መስሎህ እንዴት ራስህን እንደሴት ትቆጥራለህ? ሰይጣን አእምሮህን ለክፉ እያዘጋጀው ነው። ተጠንቀቅ። አንተ ሴት አይደለህም ፤ ወንድ ነህ። በተለይ ወንዶች "አማላይ (Sexy) ነህ" እያሉ ደጋግመው ይህንን የሚጠቀሙ ከሆነ ጥንቃቄ አድርግ። ዝም ብለህ አትሳቅላቸው ፤ እያሰቡት ያለ ነገር ስላለ አስተውለህ ተራመድ።

ስምንተኛ ፡ ቆንጆ ወንድ ሁሉ ጌይ ነው ያለህ ማን ነው? ቆንጆ ስለሆንክ ሴት ነህ ያለው ማን ነው? በተደጋጋሚ ቆንጆ እንደሆንክ የሚነግሩህ ወንዶች እንዴት አእምሮህን ማረኩህ? አብረን እንደር ሲሉህ እንዴት ሰማሃቸው? ወደ ወጥመድ ውስጥ እየከተቱህ እኮ ነው። በተለይ ቲክቶክ ፣ ፌስቡክ ላይ የምትሰሩ "ቆንጆ" ወንዶች ጥንቃቄ አድርጉ። የቃላቸው ሰለባ አትሁኑ።
246 views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 08:41:32 የስኬት መሰረታዊ መርሆች ፮
The First Principles of Success part 6
by NATI


@Spirit_Life_leader_Sol
@Spirit_Life_leader_Sol
269 viewsedited  05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 08:33:19 የስኬት መሰረታዊ መርሆች ፭
The first principles of Success part 5
by NATI

@Spirit_Life_leader_Sol
@Spirit_Life_leader_Sol
336 viewsedited  05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 23:28:41
ነገ ከ 5:30 ጀምሮ
311 views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 18:49:16
የስኬት መሰረታዊ መርሆች ፬
Part 4

by NATI


@Spirit_Life_leader_Sol
@Spirit_Life_leader_Sol
393 viewsedited  15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 12:58:41
ነገ ከ 5:30 ጀምሮ
450 views09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ