Get Mystery Box with random crypto!

ያ ረሱለላህ! እንወድዎታለን። ይቀበሉናል? እኛ እርሶን ስንወድ በእርግጥ የፊትዎን ፍካት ለመመል | ኡመተ ረሱል

ያ ረሱለላህ! እንወድዎታለን። ይቀበሉናል?

እኛ እርሶን ስንወድ
በእርግጥ የፊትዎን ፍካት ለመመልከት እድል አግኝኝተን አይደለም። ወይም የድምፅዎን መስረቅረቅ በጆሮዎቻችን አዳምጠን አይደለም።

እኛ እርስዎን ስንወድ
ከጎንዎ ሰይፍ አንግተን ከሙሽሪኮች የመፋለም እድል ኖሮን አይደለም። አልያም በኡሑድ ዘመቻ ከእርስዎ ጎን ተሰልፈን ተዋግተንም አይደለም።

እኛ እርስዎን ስንወድ
ቤት ንብረታችንን ትተን በረሀ ለበረሀ ተሰደን አይደለም። እርስዎ ሲሰደዱ ስንቅ አመላልሰንም አይደለም። ወይም እርስዎ ሲሰደዱ ለርሶ መከታ ሆነን ተቀብለንዎትም አይደለም።

ነገር ግን ያ ረሱለላህ! እኛ ወላሂ እንወድዎታለሁ።

ምን እናድርግ! ፍቃዱ የኛ ባልሆነበት ጉዳይ ላይ ከርሶ ዘመን ዘግይተን ተፈጠርን። በወላጆቻችን ላይ አላህ በዋለው የእስልምና ፀጋ እኛም ተቋደስን፤ ስለ እርስዎም እየሰማን አድገን ጎረመስን፤ ስለ እርስዎ እያሰብንም በናፍቆት አነባን።

ዘመንዎን ደርሰን ሳናይ በዘመንዎ የኖርንበት ያህል እየናፈቀን ያልኖርንበትን ዘመን ዳግም በተመለሰ ብለን ተመኘን።

እርስዎ በዘመንዎ ሁነው የኛን ዘመን ናፍቀው እንዳነቡት ሁላ እኛም በዘመናችን ሁነን የእርስዎን ዘመን እየናፈቅን በማንባት የመገናኛ ቀጠሮአችንን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን።
ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም

#ሼር
#share #join
Https://t.me/smithhk