Get Mystery Box with random crypto!

የተወደደ አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡- እግዚአብሔርን የምትወዱት፥ ይልቁንም እግ | ቅድስት ፌብሮኒያ

የተወደደ አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡-

እግዚአብሔርን የምትወዱት፥ ይልቁንም እግዚአብሔር አብልጦ የሚወዳችሁ ሆይ!

ሕፃናት የእናታቸውን ጡት ለመጥባት ምን ያህል እንደሚጓጉ አስተውላችኋልን? እኛም ወደ ቅዱሱ ማዕድ መቅረብ ያለብን፣ ከመንፈሳዊው ጽዋ ጡትም ለመጠጣት መጓጓት ያለብን እንደዚህ ነው፡፡

ሕፃናቱ የእናታቸውን ጡት ሲያዩ እንዴት ደስ እንደሚሰኙም ተመልክታችኋል! እኛም የመንፈስ ቅዱስን ፍቅር ስንመለከት ደስ ሊለን የሚገባው እንደዚህ ነው፡፡

ሕፃናቱ የእናታቸው ጡት ሲከለከሉ ምርር ብለው እንደሚያለቅሱ ኹሉ፥ እኛም ከዚህ ማዕድ (ከቅዱስ ቁርባን) ስንርቅ ምርር ብለን ልናለቅስ ይገባናል::
@Slehiwetwe ይቀላቀሉን።