Get Mystery Box with random crypto!

ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ። ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይል | ቅድስት ፌብሮኒያ

ልጹም ትላለህ ፤ ተው አትጹም ይልሃል!አንተም ትተወዋለህ።
ልመጽውት ትላለህ ፤ ተው አትመጽውት ይልሃል። አንተም ትተወዋለህ።
ንስሐ ልግባ ትላለህ ፤ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ያለንስሐ ትሞታለህ።
ልቁረብ ትላለህ ፤ ገና ነህ ትንሽ ቆይ ይልሃል። አንተም ሳትቆርብ ትሞታለህ
ላስቀድስ ትላለህ ፤ ተው ትንሽ ተኛ ይልሃል። አንተም ሳትሄድ ታረፍዳለህ።
ጸበል ልግባ ትላለህ ፤ ጤነኛ ነህ ይልሃል። ገዳም ልባረክ ልሂድ ትላለህ ፤ ተው ስራን
ስራ ይልሃል፡፡ አንተም ሳትሄድ ስትቆጭ ትኖራለህ።
አስራት በኩራት ልስጥ ትላለህ ፤ ተው አትስጥ የለህም ይልሃል። አንተም
ትተወዋለህ።
በአንድ ልወሰን ትላለህ ፤ ተው ቆንጆዎቹ ያልፉሃል ይልሃል። አንተም በዝሙት
ትወድቃለህ።
# በመጨረሻም_የተወሰነልህ_ግዜ_ያልቃል ። ነፍስህን አጋንንት እንደ ኳስ እየተቀባበሉ
ይወስዷታል።
# ልጠጣ ስትል ፤ ጠጣ ይልሃል። ያሰክርሃል።
# ልዝፈን ስትል ፤ዝፈን ይልሃል። ያስጨፍርሃል!
# ልስረቅ ስትል ስረቅ ይልሃል። ያሰርቅሃል!
# ልጣለው ስትል ተጣላ ይልሃል። ያጣላሃል።
# ልዋሽ ስትል ዋሽ ይልሃል። ያስዋሽሃል! ስጋዊ ተድላን ይሰጥሃል። ይመችሃል፡ስጋህ ወፍሮ
፣ ቀልቶ ፣ ወዝቶ በጓደኞችህ ‹ ተመቸህ እኮ ! › ያስብልሃል። አንተም ደስ ይልሃል! በዛው
ትገፋበታለህ።
# ሃሳብህ ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ቀርቶ ወደ ጅምናዝየም ቤት መሔድ
ይሆናል።
# ሃሳብህ ሁሉ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ይሆናል። ሃሳብህ ሁሉ ሳውና ባዝ ፣
ስቲም ቤት ፣ማሳጅ ቤት ሂደህ መታሸት እና መዝናናት ይሆናል።
# እግርህ ሁሉ ወደ ሲኒማ ቤት ፣ ወደ ናይት ክለብ ቤት ፣ ወደ ሆቴል ቤት ፣ ወደ
ግሮሰሪ ቤት ፣ ወደ ሱፐር ማርኬት ፣ ወደ ምናምን ቦታ ይሆናል።
በእነዚህ ሁሉ ስጋህ ሲመቸው
ቁሞ መጸለይ ይደክምሃል።
መስገድ ያቅትሃል።
መጾም ይከብድሃል።
ቤተክርስቲያን ለመሄድ ይጨልምሃል።
ስጋህ በአጋንንት መረብ ይጠመዳል።
ደም ብዝት አስይዞ ሴት ያዝልሃል።
ደም ብዛት አሲይዞሽ ወንድ ያዝልሻል።
የነርቭ በሽታ አስይዞ መቆምና መሄድ ያስቅትሃል።
ስኳር በሽታ አሲይዞ ከጾም ይከለክልሃል።
ጨጓራ በሽታ አስይዞ ጾምን ይከለክልሃል።
# ምላስህ እግዚአብሔርን ማመስገንን ሳይሆን ዘወትር ስለ በሽታህ እንድትዘምር
ያደርጋታል።
# በጣም ብዙዎች ሃብት ሞልቷቸው በሽተኛ ያደርጋቸዋል። ገና ከጥዋቱ እነዚህ ሰዎች
የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትለው ቢሄዶ ኖሮ ፤ እንደ አብርሃም ፣እንደ ይስሐቅ እና እንደ
ያዕቆብ በምድር ሃብታም እንደ ሆኑ ሁሉ በሰማይም እንደ ቅዱሳኑ የገነት ባለቤት በሆኑ
ነበር።
# ሰይጣን ክፉ ነው! ሃብታሙን በሽተኛ ፣ ድሃውን ደግሞ ጤነኛ አድርጎ አምላክን ወቃሽ
ያደርገዋል።እንዲህ እንዲህ እያለ የመሰናበቻ ጊዜ ይደርሳል። በኃጢአት የዳበረው ስጋችን
አፈር ነውና በቅጽበት እሬሳ ተብሎ ወደ አፈር ይገባል። ነፍስ ግን እያዘነችና እየተፀፀተች
ወደ ሲዖል ትወረወራለች።
# የምናያቸው ቆንጆ ሴቶች ፣ የምናያቸው ቆንጆ ወንዶች ፣ የምናየው የልኳንዳ ስጋ ፣
የምናየው መጠጥና ምግብ ሁሉ ያምረናል። ስጋችን ያሸንፈናል፥ ነፍሳችን ትሸነፋለች።
ለገነት ተፈጥረን ለሲዖል እንሆናለን።ሁላችንም ወደ እግዚያብሄር ተመልሰን ንሰሀ እንግባ።።