Get Mystery Box with random crypto!

እውነተኛ የጸሎት ጥበብ ሰው እንዲማረው የሚደረገው እግዚአብሔር ራሱ እንዲጸልይ ባደረገው በዚያ ሰው | ቅድስት ፌብሮኒያ

እውነተኛ የጸሎት ጥበብ ሰው እንዲማረው የሚደረገው እግዚአብሔር ራሱ እንዲጸልይ ባደረገው በዚያ ሰው ነው። በልማድ የሚደረግ ጸሎት ግን ያለ ጸጸት መንፈስ ስለሚቀርብ እግዚአብሔርን ደስ አያሰኘውም።

እግዚአብሔር የምትወድ ነፍስን ያለ ጸሎት ልትኖር አትችልም። እግዚአብሔር አምላክ ነፍስን ወደ እርሱ የሚያቀርባት ለእርሱ በምታቀርበው ጸሎት አማካይነት ነው። እግዚአብሔር ፍጹም የሆነውን የጸሎት ጥፍጥና የሚሰጠው ትሑት ለሆነው ብቻ ነው። ንጹሕ ሊሆን የሚችለው የትሑት ሰው ጸሎት ብቻ ነው።

| አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ |