Get Mystery Box with random crypto!

የአሁኗ ቅፅበት የመጨረሻ የሕይወት ጊዜህ ልትሆን እንደምትችል ማሰብ አያስፈራም? ሁሌም ሌላ ዕ | Art of motivation

የአሁኗ ቅፅበት የመጨረሻ የሕይወት ጊዜህ ልትሆን እንደምትችል ማሰብ አያስፈራም?

ሁሌም ሌላ ዕድል ሲሰጥህ ይህንን በአእምሮህ ውስጥ አስገባ፣ ሁሉም ነገር እንደገና ላይመጣ ይችላልና ፣ምክንያቱም ሕይወት ሁልጊዜ ሁለተኛ ዕድል አትሰጥም ፣ በየጊዜው የሚመጡትን ዕድሎች እንደ ቀላል አድርገህ መውሰድ የለብህም።

አሁን የሚታየውን ነገር ሁሉ ለመጨረሻ ጊዜ እያየህ እንደሆነ በማሰብ ከልብ ነገሮችን ተመልከት ፣ ሁል ጊዜ እያንዳንዱን ደቂቃ በማስተዋል እንዲቆጥር ማድረግ አስፈላጊ ነው ፡፡
ሕይወት አጭር ናትና

አንድ ቀን ደስታ ቤቴ ይገባል ብለህ ደስታህን አትግፋ፣ ዛሬ ደስተኛ የምትሆንበት አንድ ነገር ይኖራል። የአሁኑን ደቂቃ በጥልቀት መመልከት ከቻልክ ሁል ጊዜም የሚያስደስት ነገር አታጣም ፡፡

ደስታ የችግሮች መቅረት አይደለም ፣ ግን በችግሮች መካከልም እንኳን የምስጋና መኖር ነው ፡፡ሁልጊዜ ደስተኛ ለመሆን ሊኖርህ የሚገባው አመለካከት ይህ ነው፣ አሁን ባለህ ነገር ደስተኛ ሁን ፣ቅፅበትህ የምታመጣውን የተትረፈረፈ ደስታ አጣጥም፡፡

ባለህበት ደስተኛ ካልሆንክ ወደ ምትሄድበት ስትደርስም ደስተኛ አትሆንም ፡፡ሕይወት አጭር ናት ፣ ለዘላለም አትኖርም ፣ ስለዚህ አሁን ደስተኛ ሁን ፡፡