2023-05-13 20:16:13
በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ የበልግ ልማት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
#ግንቦት_ 5/2015 ዓ ም ስልጢ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን
የስልጢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ #ከድር_ደድገባና የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ #ጨፋ_ከድር የበልግ ልማት እንቅስቃሴ ንቅናቄ ከተፈጠረበት ግዜ ጀምሮ ያሉ ተግባራትን መነሻ በማድረግ በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የመስክ ምልከታ አድርገዋል።
የበልግ እርሻ አቅምን አሟጦ በመጠቀም የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ንቅናቄ ተፈጥሮ ወደ ተግባር መገባቱ ይታወቃል ፡፡
ከዚህ መነሻም እቅድ ተይዞ በስልጢ ወረዳ አርሶአደሩ ባለው መሬት ያህል በቆሎ፣ ቦሎቄና ድንች እንዲሁም ሌሎች ሰብሎችን እንደየአመቺነቱ በማልማት ላይ ናቸው።
አሁን ላይ ያለው የዝናብ ሁኔታ ተስፋ የሚሰጥ በመሆኑ አርሶ አደሩ እድሉን ተጠቅሞ በአጭር ግዜ የሚደርሱ ሰብሎችን በማልማት ተጠቃሚነቱን ልያሳድግ ይገባል።
የግብዓት አጠቃቀም፣የአረም፣ በሽታና የተባይ ቁጥጥር ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት እየጣለ ያለው ዝናብ አሉታዊ ተፅእኖ በሚፈጥርባቸው አካባቢዎች ደግሞ ውሃ የማፋሰስ ስራ በሚገባ መስራትም ያስፈልጋል።
64 viewsSheycho Atiso, edited 17:16