Get Mystery Box with random crypto!

አዳዲስ ኮምፒዉተሮችን ከመጠቀማችን በፊት መደረግ ያለበት ጥንቃቄ አዲስ ኮምፒዉተሮችን ከኢንተርኔት | Sime Tech

አዳዲስ ኮምፒዉተሮችን ከመጠቀማችን በፊት መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
አዲስ ኮምፒዉተሮችን ከኢንተርኔት ጋር ግንኙነት ከመፍጠራችን በፊት ማድረግ ያሉብን የደህንነት ጥንቃቄዎች የትኞቹ ናቸው?
የኮምፒዉተር ደህንነትን መጠበቅ እጅግ አስፈላጊ የሆነበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም አዲስ የገዛናቸዉን ኮምፒዉተሮች መጠቀም ከመጀመራችን በፊት ማድረግ ያሉብን የደህንነት ጥንቃቄዎች አሉ፡፡
ከእነዚህ ጥንቃቄዎች መካከል፡-
የኔትዎርክ ማገናኛ መሳሪያ የሆነውን የራዉተር(router) ደህንነት መጠበቅ.
ኮምፒዉተራችንን ከኢንተርኔት ጋር በምናገናኝበት ወቅት በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ሌሎች ኮምፒውተሮች ጋር ተገናኘን ማለት
ነዉ::
ታዲያ ይህ ሲሆን የራዉተርን ደህንነት መጠበቅ እጅግ ወሳኝ ነዉ፡፡ ምክንያቱም የኢንተርኔት ግንኙነቱ የመጀመሪያ መዳረሻ ራውተር በመሆኑ፡፡
የፋየርወል(firewall) ደህንነት ማስተካከያን ወይም ዲቫይስን
መጠቀም፡- ፋየርወሎች የኮምፒዉተራችን ግንኙነት ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን የሚያስችል በመሆኑ አዳዲስ ኮምፒዉተሮችን
ከበይነ-መረብ ጋር ከማገናኘታቸን በፊት
የፋየርወል ማስተካከያዎችን ማድረግ ጠቃሚ ነዉ:: በተለይ የኮምፒዉተር ፋየርወልን ኦንና ኦፍ (on & off) አማራጮችን 'ኦን' ማድረግ ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚፈልግ ጉዳይ ነዉ።
ፀረ-ቫይረስ (antivirus) ሶፍትዌሮችን በቅድሚያ መጫን፡- አዳዲስ ኮምፒዉተሮችን ከበይነ-መረብ(internet) ጋር ከማገናኘታችን በፊት ፀረ-ቫይረሶችን እና ፀረ-ማልዌሮችን (anti malware) ጭነን ቢሆን
ለኮምፒዉተራችን ደህንነት ተመራጭ ነዉ፡፡
እነዚህ ጸረ-ቫይረስ እና ማልዌሮችን በየጊዜዉ ማዘመን መዘንጋት አይገባም፡፡
አላስፈላጊ የሆኑ ሶፍትዌሮችን ማጥፋት
@simetube