Get Mystery Box with random crypto!

Tech News ፡ ጉግል አዲስ ስማርት ስልክ አስተዋወቀ፡፡ ጉግል ፒክስል ተብለው ከሚታወቁት የ | Sime Tech

Tech News ፡ ጉግል አዲስ ስማርት ስልክ አስተዋወቀ፡፡

ጉግል ፒክስል ተብለው ከሚታወቁት የኩባንያው ምርቶች ቀጣይ የሆነውን ፒክስል 6 የተባለ አዲስ ስማርት ስልክ ማስተዋወቁ ተገለፀ፡፡

እጅግ ፈጣን የ5ጂ ገመድ አልባ አቅም እንደያዘ የተነገረለት አዲሱ ስማርት ስልክ በገበያ ላይ ካሉ ተመሳሳይ ምርቶች አንጻር የላቀ አቅም እንዳለው ተነግሮለታል፡፡

ለስልኩ ዋነኛ ግብዓት የሆነው ቺፕ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የማሽን ለርኒንግ አቅም መያዙን ቴክ ክረንች አስነብቧል፡፡ ቺፑ ላለፉት አራት ዓመታት በኩባንያው ሲበለፅግ መቆየቱን ዘገባው ያትታል፡፡

በተያዘው የአውሮፓውያኑ ዓመት መጨረሻ ለገበያ እንደሚቀርብ የሚጠበቀው ፒክስል 6 የተሻለ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አማራጭን በማቅረብ ለተጠቃሚዎች እጅግ ምቹ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

||| @simetube