Get Mystery Box with random crypto!

ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ ! ክፍል 8 . . . የተኛሁበት ብርድልብስ ሲገለጥ ብንን ስል የጠፋው | የፍቅር አለም LOVES WORLD

ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ !

ክፍል 8
.
.
.
የተኛሁበት ብርድልብስ ሲገለጥ ብንን ስል የጠፋው መብራት በርቶ ራሔል መጠጡ አፏ ውስጥ
የተጠመቀ ይመስል ጋን ጋን እያለች ወንፊት የሆነ ፒጃማ ለብሳ ፊት ለፊቴ ቆማለች። ዓይኖቿ
ደፈራርሰው ከእኔ የፈለጉትን ነገር ለመቀበል አፍረው እየተለማመጡኝ ሲቁለጨለጩ አየኋቸው።
ጡት ማስያዢያ ስላላደረገች ውበቷ ሊረግፍ አንድ ሐሙስ እንደቀረው የሚያሳብቁት ዘልዛላ ጡቶቿ
ፊቴ ላይ አፈጠጡብኝ። አውቃ ይሁን ሳታውቅ( የማውቀው ነገር የለም)ፒጃማዋ ላይ ውሀ ወይም
መጠጥ ስለደፋችበት ደረቷና ዳሌዋ ላይ ተለጥፎ ሳየው ወንድነቴ ይፈታተነኝ ጀመር። የተፈጠረብኝን
ስሜት ለመሸፋፈን እየሞከርኩ (ኡኡቴ አልቀረብኝም እንኳን የኔን ቀርቶ የስንቱን ወንድ ስሜት
በአንድ እይታ ብቻ ስታነብ ከከረመችው ሴት ስሜቴን ለመደበቅ መሞከሬ ለራሴም ሳይቀር አሳቀኝ)
"ሪችዬ ችግር አለ እንዴ?"
ዝም አለች ከታገደምኩበት ተነስቼ አጠገቤ ቁጭ አደረኳት።
"ምን ሆነሻል ለምን አትናገሪም?"
"ልጄ?!"
"ልጅሽ ምን ሆነ?"
"ምንም አልሆነም እስከዛሬ ድረስ ሙሉ ሴት መሆኔ የሚሰማኝ በገንዘቡ እንደ ሸቀጥ ገዝቶኝ
ከሚጋልበኝ ሰው ጋር ሳድር ሳይሆን ከንፁህ ልጄ ጋር ሳድር ነው። ታዲያ አሁን አንተ እንደምትመጣ
ስትነግረኝ እየጮኸና እየተሯሯጠ እንዳይረብሸን
ብዬ ሞግዚቱ ጋር ስላሳደርኩት ብቻዬን መተኛት ፈራሁ"
" እና "
"እናማ ቅር የማትሰኝ ከሆነ አብሬህ ልተኛ" አለችኝ።
"አአአኧኧኧ ኧረ ችግር የለውም" በቅንዝረኛ ዓይኖቼ እያየኋት ስለሆነ አፌ ተያያዘብኝ። እርሷ ደገፍ
ብላኝ በእህትነት ስሜት አንገቴ ስር ሽጉጥ ስትል እንደ ዋሽንት ዜማ ያለው ትንፋሿ ማሰቢያዬን
ፐወዘብኝ ፣ እንኳን ነክተውት አይደለም ጮክ ብለው ሲያዩት እንኳን የሚቀደድ የሚመስለው ለስላሳ
ገላዋ ገላዬን ሲነካኝ ሰውነቴ መጋል ጀመረ።
የሴት ልጅ ጠላቷ የሆነው ዕድሜ እያሟሸሻቸው ያለውን ከንፈሮቿን ልስማት አንገቷን አቅፌ ቀና
ሳደርጋት ፣ ዓይኖቿ በቅንዝረኝነት ስሜት ሳይሆን በእንቅልፍ ተዳክመው ገርበብ ብለው ተከፍተው
አዩኝ። ጥቁሩ ብሌኗ ውስጥ ለኔ ያላትን ንፁህ የወንድምነት ስሜት አነበብኩኝ። ቀስ ብዬ ስሜቴን
ለማኮማሸሽ ሞከርኩ። እላዬ ላይ እንደለስላሳ ሀረግ ተጠምጥማብኝ ተኛች።
ጠዋት እነፊት መታጠብን እነ ቁርስ መብላትን ምናምን ምናምን ካደረግን በኋላ ሺሻዋን
እያንደቀደቀች ወደ ቀድሞ ጨዋታችን ተመለስን።(አሁን ብፅፋቸው ከአደግንበት ባህል ጋር
የሚጣረዙ ፣ መረን የሆኑ የራቁት ቤት ሚስጥሮችን ነግራኛለች። ወዴት እየሄድን እንዳሉ
የሚጠቁሙ ሚስጥራዊ ክሽፈቶቻችንን አጫውታኛለች። ለምሳሌ ስለ ሴት ለሴት ወሲብ/
Lesbians ፣ ጋጠ-ወጥ ባህሪ ስላላቸው ታዋቂ ሰዎቻችን ፣ ስለ ሸሌዎችና ስለ ጠንቋዮቻቸው ፣
18 ዓመት ሳይሞላቸው በዝግ ቤት ስለሚጠጡት የባለስልጣኖቻችን ልጆች ብቻ ብዙ
አውርታኛለች።)
ወንዴ ያ ራቁት ጭፈራ ቤት ሲዘጋ ደዘደዟ ያጠራቀምኩትን ወደ መቶ ሀያ ሺ ብር የሚጠጋ ገንዘቤን
ሰጠችኝ። እሱን ብር ይዤ ከዚህ ከገሃነም ህይወት መውጣት ስችል የሚያልቅ አልመስል ብሎኝ
ስመነዝር ስመነዝር በስድስት ወራት ውስጥ ዶግ አመድ አደረኩት። እንደገና ዲካርት ገባሁ።
የአመታት ልፋቴን ሁሉ በዜሮ አባዛሁት። ሳይታሰብ ከሚመጣ ሀብት ይልቅ አብሮ የኖረ ድህነት
የሚሻል መሆኑን ያኔ ኖሬበት ተረዳሁ። ከዛልህ የስራ ቦታዬን ወደ ቺቺኒያ ቀየርኩ። ወንዴ ‘’ ሚሚ
ቂጦን ቤት ታውቀዋለህ አይደል?" አለችኝ። (እንደዛሬ በቺቺኒያ ምድር club H2O ከመንገሱ በፊት
የቺቺኒያ አድባር የሚሚ ቂጦ ቤት ነበር። ይሄ ቤት ዝናው ከሀገር አልፎ አውሮፓና አሜሪካ ድረስ
ስለሚወራለት አብዛኛው ዲያስፖራ ወደ ሀገር ቤት ሲመጣ ሳይጎበኘው አይሄድም። በዚህ ቤት
ውስጥ ብዙ የከተማችን ባለሀብቶች ካዝናቸውን አራቁተው በሸሌዎች ድግምት ተተብትበው
አብደውና የነሱን ፓንት አጣቢ የቀሩ ሰዎችን አውቃለሁ። ለነገሩ ሙሉ የቺቺኒያ ምድርን
የሚያሽከረክሯት በሸሌዎቹ የሚገበርላቸው የዛርና የአውሊያ መናፍስቶች እነ አዳል ጠቋር ፣
የአርሲዋ እመቤት ፣ የደብረዘይቱ ቆሪጥ ፣ እነ ወሰን ገላ ፣ የወለጋው ሞቴ እነ እውሪት
ብርሀኔ......እና ሌሎች መሆናቸውን የአንድ ሰሞን የቺቺኒያ ተሳላሚ ስለነበርኩ በደንብ
አውቀዋለሁ። አብዛኞቹ ጠባብ ፐቦች ውስጥ ወንድ እንዲስብላችሁ እየተባሉ በጠንቋዯቻቸው
የሚሰጣቸው እጣን ይነዳል ፣ ከ1:00-3:00 ባለው ጊዜ ውስጥ እየተቃመ ይዘየራል ፣ ጥቂት
የማይባሉት ቤቶች ውስጥ ጥጃ ከነነፍሱ ተቀብሯል ፣ ደጃፋቸው ላይ ደንበኛቸው ከቤቱ
እንዳይላቀቅ ድፍን እንቁላል ይቀብራሉ ፣ የጥቁር ፍየልና የጥቁር ዶሮ ደም ያፈሳሉ። ስለዚህ ጉዳይ
ሌላ ቀን በሰፊው እንጨዋወታለን።)
"እንዴታ ሪች! ድድ ማስጫ ተወልጄ ሚሚ ቂጦ ቤት ሰክሬ ካልተለፋደድኩኝ ምኑን ወጣትነቴን
ቀጨሁት" አልኳት። እዛ ገሀነም ጭፈራ ቤት ውስጥ ያባከንኳቸውን ጊዜያቶች እያስታወስኩ።
( ከሹገር ማሚዋ ጋር ነው አይደል ቺቺንያ ስትጨፍር የከረምከው? ስትሉ ሰማኋችሁ ልበል!?)
"ወንዴ መቼም ቺቺንያ እንዲህ እንደዛሬው እንደሰካራም ፊት ቡድስድስ ከማለቷ በፊት የሀጢያት
ዘውዷን ከአሮጊቷ ካዛንችስ ከተረከበች በኋላ ብዙ ተአምር ተሰርቶባታል። ብዙ ባለሀብቶችን
አደህይታለች ፣ እልፍ ደሀዎችን ደግሞ ሀብታም አድርጋለች ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶችን
ቅርጥፍጥፍ አድርጋ በልታለች ፣ ብዙዎቻችንን ከሲጋራ እስከ ኮኬን ድረስ ከትባናለች ይሄንንም
የታዘቡ እንዳንተ ዓይነት ቸክቻኪዎች የፈጠራ ታሪካቸውንና እውነታውን አደበላልቀው ብዙ ገድሎቿን
በመፅሃፍ አሳትመው ሀብታም ሆነውባታል። ስለ ሸሌ የተፃፉ መፅሐፍት በሙሉ የብዕራቸው አሞራ
የሚያንዣብበው በዚች ቅዱስ ሚካኤል የጣለው ሳጥናኤል በታሰረባት በተአምረኛዋ ቺቺኒያ በኩል
ነው። እኔ እንኳን ያነበብኳቸው መሀልየ መሀልየ ዘ ቺቺኒያ ፣ የቺቺኒያ ሚስጥራዊ ለሊቶች ፣ ሰአት
እላፊ ላይ ያሉ ታሪኮች ፣ ሮዛ ብቻ ሌሎችም የማላስታውሳቸው ብዙ ተሞንጭረዋል። እናልህ እዚህ
ሚሚ ቂጦ ቤት ገቢዬ እንደደዘደዟ ቤት ባይሆንም እሱ የከፈተውን እ*** እሱ ሳይዘጋው አያድርም
ነበር። እንግዲህ እዚህ ቤት ነው በሀምሳ ብር የሸጠኝን ባሌን የተዋወኩት
"እንዴት?" አልኳት ለወሬ የቋመጡ ጆሮዎቼን ቀጥ አድርጌ
"ሚሚ ቂጦ ቤት አመት ከምናምን እንደሰራሁ

ይቀጥላል..

╔═══❖• •❖═══╗
@silefikrr
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@silefikirbot
❥❥________⚘_______❥❥