Get Mystery Box with random crypto!

ለአገልግሎት ጥራት ከአገልጋዮች ጋር የተደረገ ውይይት የ አገልግሎት ጥራትን በመጨመር ህብረተሰብ | Sheger Mass Transport Service Enterprise

ለአገልግሎት ጥራት ከአገልጋዮች ጋር የተደረገ ውይይት

የ አገልግሎት ጥራትን በመጨመር ህብረተሰብ መጠን አገልግሎት መስጠት የማያስችለውን ውይይት ሸገር ከሰራተኞቹ ጋር አካሄደ

በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጎን ሸገር አሳወቀ።

በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ከቃሊቲና ሸጎሌ ዴፖ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ውይይት ከታች ያለው ሰራተኛ እና አመራሩ ተቀራርቦውና ተናቦው እንዲሰሩ ከማገዙ ባሻገር በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረምና በጋራ ለማስተካከል የሚያስችሉ የመትሄ ሀሳቦች የተገኙበት እንደነበር የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቢተው ደመላሽ ተናግረዋል፡፡

አቶ ቢተው አያይዘውም በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችንም ሆነ ከሰራተኞቹ እየተነሱ ያሉ ችግሮችን በአጭር ጊዜ በማስተካከል ለደንበኞቻችን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት መረባረብ አለብን ብለዋል፡፡
#sheger_bus