Get Mystery Box with random crypto!

መውሊድን ማክበር እንደሚፈቀድ እና በማክበሩም ምንዳ እና አጅር እንዳለው የሚገልፅ ብያኔ (ክፍል | ሻሚል - shamil

መውሊድን ማክበር እንደሚፈቀድ እና በማክበሩም ምንዳ እና አጅር እንዳለው የሚገልፅ ብያኔ

(ክፍል 10
)

እንደዚህ አይባልም «መውሊድ መልካም ሱና ነው ይባላል እንጂ፤ መውሊድ መልካም ስራ ቢሆን ኖሮ ነቢያችን ﷺ ኡመቶቻቸውን ያመላክቱ ነበር አይባልም»።


ቁርኣንን በአንድ ሙስሐፍ መሰብሰብና ነጠብጣብ ሆነ ተሽኪል ማድረጉ መልካም ስራ ነው። ሆኖም ግን ነቢያችን ﷺ እንዲደረግ አልጠቀሱም ፣ እሳቸውም አላደረጉትም። እነዚያ መውሊድ መልካም ስራ ቢሆን ኖሮ የአሏህ መልክተኛ ﷺ ያመላክቱን ነበር በማለት መውሊድን ማክበር የሚከለክሉ እራሳቸው ነጠብጣብና ተሽኪል ያለበትን ቁርኣን የሚያነቡ ናቸው በመሆኑም ከሁለት ነገሮች ውስጥ አንዱ ላይ ይወድቃሉ።

አንደኛው አማራጭ «ቁርአንን ነጠብጣብና ተሽኪል ማድረግ የአሏህ መልክተኛ ስላላደረጉት አድርጉትም ብለው ኡመታቸውን ስላላመላከቱ መልካም ስራ አይደለም፤ ሆኖም ግን እኛ እናደርገዋለን» ሊሉ ይችላሉ።

አልያም የቀራቸው አማራጭ «ቁርኣንን ነጠብጣብና ተሽኪል ማድረግ የአሏህ መልክተኛ ባያደርጉትም፤ አድርጉትም ብለው ኡመቶቻቸውን ባያመለክቱም መልካም ስራ ነው ለዚህም ነው እኛ ምናደርገው» በማለት ሁለት አማራጭ ብቻ ይኖራቸዋል።

በሁለቱም አማራጮች ግን ከራሳቸው ጋር ይጋጫሉ። (ማለትም ንግግራቸው እንደ ማስረጃ አድርገው ካቀረቡት ጋር ይጋጫል።)

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil

https://t.me/shamilunkamil