Get Mystery Box with random crypto!

لله تعالى በዓረፋ ቀን የሚደረጉ ዱዓዎች الحمد لله والصلاة والسلام على رس | SHAMIL

لله تعالى
በዓረፋ ቀን የሚደረጉ ዱዓዎች

الحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله
በዓረፋ ቀን በጠበቀ መልኩ ዱዓን ማብዛት ይወደዳል።
ነቢያችን በዓረፋ ቀን መውቂፍ ላይ በብዛት ያደረጉት ዱዓእ
اللهم لك الحمد كالذي تقول وخيرا مما نقول اللهم لك صلاتي ونسكي ومحياي ومماتي وإليك مآبي ولك ربي تراثي اللهم إني أعوذ بك من عذاب القبر ووسوسة الصدر وشتاة الأمر اللهم إني أعوذ بك من شر ما تجيئ به الريح

እንደዚሁም ዓረፋት ላይ ለቆመ ሰው አነዴ ኢስቲግፋር ማድረጉ፣ ለብቻውም በጀመዓም ሆኖ ዱዓ ማድረጉ ይወደዳል።

አንዳዴ ተልቢያ ያደርጋል (ለበይከሏሁመ ለበይክ ይላል) አንዳዴ ደግሞ ተክቢራ ያደረጋል አንዳዴ ደግሞ ተህሊል ያደርጋል።

እንዲዚሁም ለራሱ፣ ለወላጆቹ፣ ለዘመዶቹ፣ ለመሻይኾቹ፣ ለጓደኞቹ፣ ለወዳጆቹ እና ለሌሎችም ጥሩ ላደረጉለት ሙስሊሞች ሁሉ ዱዓ ማድረግ ይኖርበታል።

ነቢዩ ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም እንዲህ ብለዋል፡
«مارأي الشيطان أصغر ولا أحقر ولا أدخر ولا أغيظ منه في يوم عرفة وماذاك إلا أن الرحمة تنزل فيه فيتجاوز عن الذنوب العظام»
«እንደ ሸይጧን በዓረፋ ቀን አንሷ፣ ተዋርዶ ተሸንፎ እና ተናዶ የታየ የለም ይህም የሆነው በዓረፋ ቀን በሚወርደው የአሏህ እዝነት አማካኝኘት ነው እናም ከባባድ ወንጀሎች ይማሩበታል»

ከፉዶይል ኢብኑ ዒያድ እንደተዘገበውም ዓረፋ ላይ የሰዎችን ለቅሶ ተመለከቱና እንዲህ አሉ፡« አያቹህ እነዚህ ሰዎች ወደ አንድሰው ሂደው ዳነቅን (የዲርሀምን 1/6ኛ) ቢጠይቁት ይመልሳቸው ነበር?» አይመልሳቸውም ተባሉ ከዛም እሳቸው፡« በአሏህ ይሁንብኝ እነዚህን ሰዎች ምህረት መስጠት ዳነቅን ከሚሰጠው ሰው ለአሏህ ቀላል ነው» አሉ

ከሳሊም ኢብኒ ዓብዲላህ ኢብኒ ዑመር ኢብኒል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዓንሁም እንደተዘገበው በዓረፋ ቀን አንድ ለማኝ ሰውን እየጠየቀ አዩ እና እንዲህ አሉ ፡« ማግኘት የተሳነህ ሆይ በዚህ ቀን ከአሏህ ውጭ ሌላን ትጠይቃለህ!?»

ከተመረጡ ዱዓዎች መካከል
اللهم آتنا في الدنيا حسنة وفي الآخرة حسنة وقنا عذاب النار، اللهم إني ظلمت نفسي ظلما كثيرا وإنه لا يغفر الذنوب إلا أنت فغفر لي مغفرة من عندك، ورحمني إنك أنت الغفور الرحيم، اللهم اغفر لي مغفرة من عندك تصلح بها شأني في الدارين، وارحمني رحمة منك أسعد بها في الدارين، وارزقني توبة نصوحا لا أنكثها أبدا، وألزمني سبيل الاستقامة لا أزيغ عنها أبدا، اللهم انقلني من ذل المعصية إلى عز الطاعة، وأغنني بحلالك عن حرامك وبطاعتك عن معصيتك وبفضلك عمن سواك، ونور قلبي وقبري، وأعذني من الشر كله واجمع لي الخير كله، استودعتك ديني وأمانتي وقلبي وبدني وخواتيم عملي وجميع ما أنعمت به علي وعلى جميع أحبائي أجمعين.
https://t.me/shamilkaml