2022-07-31 12:15:06
ለናንተ
ሞቅ ያለ ውሃን የመጠጣት አስገራሚ ጠቀሜታዎች
አብዛኛዎቻችን ከአልጋችን ከተነሳን በኋላ ሰውነታችንን ለማነቃቃት እራሳችንን በትኩስ ቡና ወይም ሻይ ቀኑን እንጀምራለን፡ ውሃ በምንጠጣበት ጊዜም ቀዝቃዛ እንዲሆን እንመርጣለን ነገር ግን ይህ ስህተት ነው።
በተለይም በጠዋቱ ሞቅ ያለ ውሃን መጠጣት ሰውነታችን የተፈጥሮ በሽታ ተከላካይ ሕዋሳችን ውስጥ ሊገነባ የሚችል ሜታክቢክ ፈሳሽ በመፍጠር ሰውነታችንን ማዳን ይችላል
ሞቅ ያለ ውሃ መጠጣት ለአፋችን ባይጣፍጠንም ካፌይን እና ሻይ የመሳሰሉትን በመቀነስ ለጤንነትዎ በእጅጉ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።. ለዚህም ስድስት ምክንያቶችን ማስቀመጥ ይቻላል።
1. ጠዋት ላይ አንድ ሞቅ ያለ ኩባያ ዉሃ ከሰውነትዎ ዉስጥ መርዛማ ነገሮችን ለማፅዳት ይረዳል።
2.በባዶ ሆድ የሞቀ ዉሃ መጠጣት የሆድ ድርቀትንም ይከላከላል
3. ተፈጥሯዊ ከፍተኛ ኃይል ያለው የቤት ውስጥ መድሐኒት ተብሎ የሚጠራው የሞቀ ውሃ, ከወር አበባ እና የራስ ምታ ህመምን ለማስታገስ ይረዳል ።
4. አንድ ብርጭቆ ሞቃት ውሃን ማለዳ ማለዳ መጀመሪያ ላይ መጠጣት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል።
5. የደም ዝውውርን ያሻሽላል፡ ይህም ጡንቻዎች ዘና እንዲሉ በማድረግ, ደካማ የደም ዝውውርን እና ፍሰትን ያስወግዳል
6. ከእድሜ ቀድሞ የሚመጣን እርጅና ያዘገያል። የሞቀ ውሃው ከሰውነታችን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ለማጽዳት ይረዳል። የቆዳ ሴሎችን በመጠገን የቆዳችንን የመሳብ /elasticity ይጨምራል
510 viewsMimi Nigusse, edited 09:15