Get Mystery Box with random crypto!

ድንቅ ልማድ አንድ ልማድ ስትጀምረው እንደማይታይ ክር ነው፤ ያ ክር እርስበርሱ ሲደጋገም ሲጠላለፍ | ሰውነት 🗣🚶‍♀🚶‍♂

ድንቅ ልማድ

አንድ ልማድ ስትጀምረው እንደማይታይ ክር ነው፤ ያ ክር እርስበርሱ ሲደጋገም ሲጠላለፍ ትንሽ ቆይቶ በቀላሉ የማይበጠስ ሀያል ገመድ ይሆናል።

አየህ አሪፍ ልማድን ስትጀምረው እንደ ክሩ ስስ ነው፤ ለመበጠስ ቅርብ ነው፤ ስትደጋግመው ግን አንተ ውስጥ ጠንካራ ማንነት ይፈጥራል።

ግድ የለህም ወዳጄ በጠዋት መነሳቱን፣ ማንበቡን፣ ስፖርት መስራቱን፣ ቋንቋ መለማመዱን በቃ የጀመርከውን አሪፍ ልማድ ሳትሰለች ትንሽ ደጋግመው፤ ከዛ ምን አይነት ሰው እንሚያደርግህ ታየዋለህ!
@sewnet_et
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!