Get Mystery Box with random crypto!

👨ሰው መሆን👩 ሰው ነንና!!!

የቴሌግራም ቻናል አርማ sew_mehon_sew_nenena — 👨ሰው መሆን👩 ሰው ነንና!!! ሰ
የቴሌግራም ቻናል አርማ sew_mehon_sew_nenena — 👨ሰው መሆን👩 ሰው ነንና!!!
የሰርጥ አድራሻ: @sew_mehon_sew_nenena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 405
የሰርጥ መግለጫ

<<ለተፈጠርንለት አላማ መኖር ሰው ከመሆን ይጀምራል።>>
~ፈጣሪ እስትንፋሳችንን ሲያስቀጥል በመኖራችን ሊሰራ የፈለገው ነገር አለ። እርሱ ተራ አይደለምና ሲያኖረን በእኛ ተራ ነገር ሊሰራም አይደለም ማለት ነው።
#ሰው_መሆን
@sew_mehon_sew_nenena

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-30 21:02:35 መጀመር!

ከሰው ልጅ አእምሮ ውስጥ ሀሳብ አይጠፋም። ስንሄድ ስንቆም ስንቀመጥ... የተለያየ ተግባራትን እየፈፀምን አእምሮአችን ውስጥ የሚመላለስ የተለያየ ሀሳብ አለን። እንድናስብበት ከፈጣሪ በተሰጠን አእምሮአችን ውስጥ የሚፈጠሩ ሀሳቦቻችን #ትልቅ ዋጋና ሀይል አላቸው።

እያንዳንዳችን ዘንድ የሚደርስ አእምሮኣችንን የሚዳስስ የለውጥ ሀሳብ አለ። እንዲህ ቢሆን እንዲህ በሆንኩ እንዲህ በሆነልኝ የምንልበት ርዕሰ #ጉዳይ በቀንና በሌሊት በውስጣችን ይነሳል።

ፈጣሪ መልካምና በጎ ለውጥን በእኛ ላይ ማየት ከመሻቱ የመጣ ድንቅ #ፍላጎት አእምሮአችን ውስጥ በሀሳብ መልክ ያድራል።

መሆን ስለምንፈልገውና መሆን ስላለብን ነገር የሚኖረንን ሀሳብ አካል ለማልበስ የመልካምና የበጎ ሀሳብ ባለቤቱን መታመን መቻል የፍሬያማነት #መሠረት ነው።

እኔኮ ብዙ ጊዜ እያሰብኩ አልሆነልኝም፤ ስንቴ ነው ጀምሬ ያቆምኩት?፤ እንደማይሆንማ እርግጠኛ ነኝ፤ አይ እኔ አልችልም... እያልን ምክንያቶች ከምንደረድር የሚሆንበትንና የሚሳካበትን ዋነኛውን ትልቁን ምክንያት #መመልከት እንጀምር!

- አንተ ለተፈጠርክበት አላማ መኖር አለብህ! ይህ እንዲሆን ደግሞ አንተን #ወደመቻል የሚያመጣህ ፈጣሪ ይረዳሃል...

- አንቺ ለተፈጠርሽበት አላማ መኖር አለብሽ! ይህ እንዲሆን ደግሞ አንቺን #መለወጥ የሚችለው ፈጣሪ አለልሽ...

እስከዛሬ አለመሆኑ፤ እስከዛሬ አለመቻላችን፤ እስከዛሬ መውደቃችን ከህልማችን ከትክክለኛው #መንገድና ከፈጣሪ ሀሳብ ሊለያየን አይገባምና “ትላንቴ በቂ ምክንያት እንዲሆነኝ አልፈቅድም ዛሬን የሰጠኝ ፈጣሪ እንደአዲስ ለመጀመር ከበቂ በላይ ምርጥ ምክንያቴ ነው!” እንበል።

እኛ ለመጀመር እንሰንፍ ይሆናል እንጂ ፈጣሪ እኛን ለማስጀመር ዝግጁ ነው። እኛ ለከበደን፤ ከመክበድም አልፎ ከአቅም በላይ ለሆነብን፤ ከአቅም በላይ ሆኖብንም ለተውነውና ተስፋ ለማናደርግበት ጉዳይ ሁሉ ምንም የማይሳነው መልካሙ ፈጣሪ አቅምና ጉልበት #ድንቅ ተስፋ ሊሆነን የልባችንን በር ያንኳኳል!

መሆን ያለብንን ሆነን እንድናልፍ ለአእምሮአችን የማንቂያ #ደውል የሚያደርሰንን ፈጣሪን እንታመንና ከተከበብንበት እልፍ ምክንያት እንውጣ!

እንደሚይሆን፤ እንደማይቻልና እንደማይሳካ ካመንበት ቀጠና ወደሌላ የእምነት መዳረሻ እንገስግስ... ከፈጣሪጋ የዘመተ እንደሚያሸንፍ አምነን የመሸነፋችን #ምክንያት ከመሆን እንድንቆጠብ አለመቻላችንን ለመለወጥ ወደሚችለው፤ ሁሌም እኛን ከውድቀት ለመታደግ ወደሚፈልገው እንቅረብ!

ለመጀመር ዝግጁ ሁን፤ ለመጀመር ፈቃደኛ ሁኚ፤ የትላንት ሙከራ የዛሬ ጅማሬህ ላይ በጎ ተፅዕኖ ብቻ እንዲኖረው ፍቀድ ከትላንት ስህተትህ መማርን ውደድ... ትላንት እንደጀመርሽው ለመጨረስ ሳይሆን ዛሬ የሚኖርሽ #አዲስ ጅማሬ መሆኑን አውቀሽ በርቺ + ተነሺ።

ጀምሮ የማቆም ምክንያት ወድቆ መቅረት ነውና ልንጋፈጥና ልንታገል ወስነን ስንጀምር ወድቀን ላለመቅረት እንቁረጥ... #ዛሬ ስንነሳ ነገም ወድቀን ላለመቅረት ወስነን ሲሆን የዛሬ መጀመራችን ውጤቱ ያማረ ይሆናል። በመንገዳችን ሁሉ አስጀምሮ ማስጨረስን የሚያውቅበት ፈጣሪ አለና ለመጀመር ስንጀምር ደስ ይበለን። ጀምር! ጀምሪ! እንጀምር...

#እጀምራለሁ!!!

በየአብስራ የተጻፈ

ለተፈጠርንበት አላማ ያኑረን
@sew_mehon_sew_nenena
137 views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 21:01:44
“መጀመር”
በየአብስራ የተጻፈ

>>በየሳምንቱ ሃሙስ ማታ 3:00 መልካም ሃሳቦች ወደእናንተ ይደርሳሉ።

ለተፈጠርንበት አላማ ያኑረን
@sew_mehon_sew_nenena
103 views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 22:00:25 አለመያዝ!...

በመኖር ጀምረን ኖረን የምንደርስበት #መድረሻ የተዘጋጀልን በፈጣሪ የተበጀን የፈጣሪ ስራዎች ነን። ከመድረሻችን ሊያስቀረን ካልሆነም ሊያዘገየን በህይወት መንገዳችን ሁሉ የሚፈታተን መኖሩን በመረዳትም የሰራን ፈጣሪ በእኛ እንዲሰራ ዝግጁ መሆን እንችላለን።

ሲይዝ አያያዝ የሚያውቀው ትክክለኛው ያዢ የሰራን ፈጣሪ ነው። ፈጣሪ የያዘው #ሰው እንደዘገየ፤ እንደከሰረ፤ እንደተጎዳና እንደተሞኘ ሊያስብ አይገባም። በፈጣሪ መያዝ ኪሳራና ጉዳት ጉድለትና ሞኝነት አይደለም።

ዛሬም ነቃ ብለን ማስተዋል አጥርተን መመልከት አለብንና የተያዝንበትን ነገር እንመርምር። ምንድነው የያዘኝ? ምንድነው እንዳልሄድ የሚጎትተኝ? ምንድነው ያሰረኝ? ምንድነው... #መልሱን ለማወቅ ስንፈልግ አለመያዝን ማግኘት እንጀምራለን።

ሊለቀንና ልናስለቅቀው የሚገባውን ሀሳብ ከአእምሮአችን ማራቅ፤ ያልተገባውን ባህሪይ ከእኛነታችን ማላቀቅ፤ ልባችንም እንዲታደስ ልክ ባልሆነ መልኩ የተያዝንበትን መበጠስ፤ ባለመያዝ ለመቀጠል መቁረጥ፤ ልማድ ከሆነ ውሎ ማምለጥ ስለህልምና አላማችን ከልባችን መሆን ታጋይ ትኩረት ሊሰጠው የሚሻ #ጉዳይ ነው።

ባለህበት ስፍራ በሚወራ ወሬ፤ ባለሽበት ቦታ በሚነገር ዜና፤ በደረስክበት ሁሉ በምትሰማውና በምታየው ጉድ፤ በደረስሽበት ሁሉ በሚደርስሽ ነገር... በክፉ #መረጃ ብዛት ልብህ እንዳይዝል! በመጥፎ መረጃ ክምችት አእዕምሮሽ እንዳይደክም!

- ሁሌም ሊይዝህ የተገባ ሲይዝህ መልካም የሆነው ከፈጣሪ የሚላክ #ሃሳብ ነው።
- ሁሌም ሊገዛሽ የተገባ ሲገዛሽም በጎ የሆነው ከፈጣሪ የሚደርስሽ #ሃሳብ ነው።

መልካም በሆነው ስንያዝ ልባችንና አእምሮአችንን በመልካም ሃሳብ የተሞሉ ይሆናሉ። በመልካም ከተሞላን ለክፉ ማስገቢያ #ቦታ እናጣና እንታደላለን፤ በክፉ ላለመያዝ እንበቃለን።

በየአዲስ ቀናችን በየማለዳችን ከመልካም ጉዞ ሊያስቀረን፤ ከመልካም መድረሻችን ሊያዘገየን፤ በመነሻችን የሚገጥመን፤ በመንገዳችን የሚጋረጥብን ሀሳብ ብዙ ነው። ማደራችንን የማይወድ #ከንቱ ያዢ ሁሉ በእንደምን አደርክ/አደርሽ ሰበብ ወደመንገዳችን ሰተት ይላል።

ቀን ሰጪውን ማድመጥ ወደቀን ሰጪው መመለስና ራስን ለቀን ሰጪው መስጠት በእርሱ ሃሳብ መያዝና መገዛት ግን የእያንዳንዱ #ቀን ድላችን፤ የፍፃሜያችንም ማማር ምክንያት ይሆነናል።

ምናልባት የያዘንና የጎተተን #መልካም የመሰለንም ነገር ሊሆን ይችላል። የትላንት ስኬታችንም ቢሆን ወደነገ ከመቀጠል ሊያስረፍደን አይገባም። የዛሬ አምሮትና ምኞታችንም ቢሆን ከመንገድ እንዲያስቀረን አንፍቀድ።

በትክክል ለመጓዝ ከህልማችን ለመድረስ እንነሳ!... እንደማንለወጥ ከምናስብ ይልቅ እንደማንለወጥ እየነገረ የያዘንን ክፉ ሀሳብ ለማስለቀቅ እኛው ለእኛው ያለመያዝ #ዘመቻ እናውጅ። የያዘህን ስታስለቅቅ ያልያዝከውን ወደመያዝ ትገሰግሳለህ፤ የጎተተሽን ስታስለቅቂ የታሰበልሽን ወደማግኘት ትደርሻለሽ። በተፈጠርንበት አላማ መኖር እንችል ዘንድ አንያዝ!

ከተያዝንበት ነገር እንድንላቀቅ ሊረዳን የሚፈልግ የማይረሳ ፈጣሪ እንዳለን አውቀን፤ እንደሚደርስልን አምነን እንዲይዘን እጃችንንም ወደእርሱ #እንዘርጋ!

በየአብስራ የተጻፈ

ለተፈጠርንበት አላማ ያኑረን
@sew_mehon_sew_nenena
157 views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 21:56:15
“አለመያዝ”
በየአብስራ የተጻፈ

>>በየሳምንቱ ሃሙስ ማታ 4:00 መልካም ሃሳቦች ወደእናንተ ይደርሳሉ።

ለተፈጠርንበት አላማ ያኑረን
@sew_mehon_sew_nenena
120 views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 21:15:23 የት ድረስ?

ተገድቦ በተበጀ ዕድሜያችን ስንኖር በእያንዳንዱ ቀናችን ውስጥ የምናደርገው እንቅስቃሴ ብዙ ነው። የምንሮጥለትና የሚያሮጠን፤ የምንታገልለትና የሚያታግለን አላማና ጉዳይ አለ። በብዙ ሁኔታ ብናልፍም በምናልፍበት ሁሉ ስናልፍ ልባችን ውስጥ የሚናፈቅ መድረሻ ይኖራል።

#ጊዜ ባክኖ እንዲቀር ሳይሆን እየተጠቀምንበት እንድንኖር ተችሮናልና በህይወት መንገድ ላይ ሳለን በጊዜ አማካኝነት መጓዛችን ዋጋ አለው። አሁናችንን እንመልከት እያደረግነው ባለው ጉዞ የት ድረስ ለመጓዝ ነው የተነሳነው? የት መድረስ ትፈልጋለህ? የት መድረስ ትፈልጊያለሽ?

በውልደት የጀመረው ጉዟችን በሞት ሲጠናቀቅ የት ደረሰን መገኘት እንዳለብን እንወቅ። መጨረሻው ሲመዘን የማናፍርበትን፤ ነገ ደርሰን በትላንት የማንፀፀትበትን ለማድረግ #ዛሬ በጊዜያችን ተጠቃሚ እንሁንና ጊዜ ለሰጠን ፈጣሪ እንንቃ...

ጅማሬን አለመናቅ ፍፃሜን በተስፋ መጠበቅ ያስችላል። ጅማሬያችን ትንሽ መሆኑን አንይ ፈጣሪ ፍፃሜያችንን #ታላቅ ያደርግልናል። ፈጣሪን አምኖ እንደመጓዝም ታላቅ ስኬት የለምና በእያንዳንዱ ቀን ቀኑን ባሳየን በእርሱ ለመበርታት እንውደድ...

- የት መድረስ አለብኝ?

ሰዎች ድረስ ያሉህ ቦታ አይደለም!... ቤተሰቦችሽ ድረሺ ያሉሽ ስፍራ አይደለም!... ለእኛ #መልካም የሚመኙ ሁሉ እንዲደሰቱ የሚያደርግ የእውነት ለእውነት ኖርን የሚያሰኝ የፈጣሪ ሀሳብ አለና እርሱን ለመረዳት በመሻት ውስጣችን ውስጥ ያሳደረውን መልካም አላማ ከልባችን እናስስ... አናጣውም።

መድረስ ያለብን የታሰበልን ስፍራ ነው። በምድር ለመኖር ተፈጥረን መሮጣችን ካልቀረ ሩጫውን አቋርጠን ድካም ከምናተርፍ መጀመራችንን ለመጨረስ እናርገው!... #ድንቅ አጨራረስ እንድንጨርስ የምሮጠው የት ድረስ እንደሆነ ገብቶን በማስተዋል እንቀጥል...

- የሚገርመው ዛሬም ፈጣሪ መድረስ ያለብህ ትክክለኛው ቦታ ሊያደርስህ #የፍቅር በጀቱን አዘጋጅቷል።

- የሚደንቀው ዛሬም ፈጣሪ መድረስ ያለብሽ ትክክለኛው ስፍራ ሊያደርስሽ #የፍቅር በጀቱን አፅድቋል።

መድረስ ያለብን ትክክለኛ ስፍራ የምንደርስበትም ትክክለኛ #አቅም ፈጣሪ ነው። የፈጣሪ በጀት በቂና ከበቂ በላይ ነውና እንደሚያደርስህ እንደሚያደርስሽ ምንም ጥርጣሬ አያስፈልግም።

ጥረትህን ቀጥል፤ ትግልሽን አታቁሚ... ትንሽ ቢመስልህም፤ ትልቅ የማይሆን ቢመስልሽንኳ ማቆም ፈፅሞ አይገባም፤ መቀጠልህ ትልቅ ነገር እንደሆነ ተረዳ! አለማቆምሽ ትልቅ ነገር እንደሆነ ተገንዘቢ! #እንደገና በሚያቆመው ፈጣሪ ቆመን እንደገና ለመቀጠል መፍቀዳችን ትልቅ ነገር እንደሆነ ይግባን።

የፍቅር በጀት ተለቆልንማ አንዘናጋም። ባለበጀቱን ፈጣሪ እየታዘዝን ከእርሱ ፈቃድ ሳንወጣ በሙሉ ተስፋና እምነት እንነሳ ባለን ጊዜ እንጠቀም... ደስ እያለን ለመንገዳችን የተመጠነ ጥያቄ እናቅርብ #የት_ድረስ?

በየአብስራ የተጻፈ

ለተፈጠርንበት አላማ ያኑረን
@sew_mehon_sew_nenena
217 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 21:14:29
“የት ድረስ?”
በየአብስራ የተጻፈ

>>በየሳምንቱ ሃሙስ ማታ 3:00 መልካም ሃሳቦች ወደእናንተ ይደርሳሉ።

ለተፈጠርንበት አላማ ያኑረን
@sew_mehon_sew_nenena
164 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 21:18:09 ሳናጣ በፊት!
(ያለንን ነገር ሳናጣው በፊት ያለውን ዋጋ እንረዳ።)

እኛ በህይወት ሳለን አለን ብለን ልንጠቅሰው የሚገባ ከፈጣሪ የተሰጠን #ውድ ነገር አለ። በተሰጠን ውድ ነገር ውስጥ ያለውን የፈጣሪን ውድ ሀሳብ መረዳት መቻል ደግሞ ህይወታችንን ያስውብልናል።

የፈጠረን መልካም ነውና ከውልደታችን ጀምሮ በዚህች ብዙ ፈተና ባለባት አለም ስንኖር መኖራችንን እንዳንጠላ የሚያደርገንን እያደረገልን ነው። ምን እንደተደረገልን... ምን እንደተሰጠን ከገባንና ለምን እንደተሰጠን ካስተዋልን መኖራችን #ትርጉም ያገኛል።

ስጦታ ውድ ነው! ርካሽ ቦታ አይሰጠውም... ፈጣሪ የሰጠን ስጦታ ውድነቱ እርግጥ ነው እርሱ ለሰጠን ስጦታ ልንሰጥ የሚገባውን ትክክለኛ ቦታ #መስጠት ይጠበቅብናል... ለተሰጠን ስጦታ በምንሰጠው ቦታ የኛም ህይወት ይወሰናል።

በህይወትህ የመጡ አሁን ላይ አሉኝ የምትላቸው ነገሮች ላይ ያለህን አያያዝ ፈትሽ... በህይወትሽ የተገኙ አሁን ላይ የኔ ናቸው የምትዪቸው ነገሮች ላይ ያለሽን አያያዝ ፈትሺ... ልናጣ የማይገባንን #ያለጊዜው እንድናጣ የሚያደርገን የአያያዛችን ሁኔታ ነው።

ያለንን ነገር ከማጣት በላይ ልቆ ሚጎዳን እያለን ዋጋ ሳንሰጠው ቀርተን #መባከኑ ነው። ስለዚህ ያለንን ነገር ሳናጣው በፊት ያለውን ዋጋ እንረዳ!... ላለን ነገር ተገቢ አያያዝ ይኑረን።

ከተሳሳተ አካሄዳችን፤ ላለን ነገር ትክክለኛ ቦታ ካለመስጠታችን የሚመጣው ኪሳራ ከባድ ፀፀት አለው። ማንምም ደግሞ በኖረው #ኑሮ ቁጭት ውስጥ መውደቅ አይሻም። ራስን ከፀፀት ለመታደግ ያለንን ነገር ሳናጣው በፊት ያለውን ዋጋ ለማወቅ እንፍቀድ።

ባለፉት ጊዜያት የባከኑ ዋጋቸውን ሳንረዳ ያጣናቸው ነገሮች ኖረው ቢሆንኳ አሁን ላይ ፈጣሪ የሰጠን #ጊዜ የተባለው ውዱ ስጦታ ያለውን ዋጋ ተረድተን በፀፀትና በቁጭት ከመባከን ይልቅ ቀሪ ዘመናችንን ለማሳመር ለአጨራረሳችን ጠንቃቃ እንሁን።

ያለን ነገር ያለው ዋጋ ገብቶን መኖር ስንቀጥል መታረም ለሚችሉ ጥፋቶቻችን #አስፈላጊ እርምጃ እንወስዳለን። ያለን እንዳለን የሚገለፀው በትክክለኛ አያያዝና አጠቃቀም ስናቆየው ነውና ያለንን ሳናጣ በፊት ያለውን ዋጋ ለማወቅ እንንቃ!

ባለን ሰአት ከተረዳነው ባለን ነገር ተጠቅመንበት ዛሬያችንን ለእውነተኛ ደስተና እርካታ ነገአችንን ደግሞ ከፀፀት ለዳነ #ህይወት እናበቃለን።

ያለን ነገር ያለው #ዋጋ ገብቶን ስንኖር የምንኖርለት የፈጣሪ አላማ ይኖራል። ያለን ነገር ያለውን ዋጋ ለመረዳት አናርፍድ!

በየአብስራ የተጻፈ

ለተፈጠርንበት አላማ ያኑረን
@sew_mehon_sew_nenena
207 views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 21:15:27
“ሳናጣ በፊት!”
በየአብስራ የተጻፈ

>>በየሳምንቱ ሃሙስ ማታ 3:00 መልካም ሃሳቦች ወደእናንተ ይደርሳሉ።

ለተፈጠርንበት አላማ ያኑረን
@sew_mehon_sew_nenena
156 views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 21:01:04 እንኳንም ትንሳኤ ኖረ!...

ሰው ትላንትን አልፎ ወደነገ መንገድ ላይ በሆነበት ዛሬ በተባለ ቀን ላይ ሆኖ ሳለ የማይካድ እውነት ውስጡ አለ። ፈጣሪ ኑሩ ብሎ በሰጠን እድሜ በሚያሳየን ቀን ውስጥ ሁሉ ተስፋ የተባለ ውድ የሆነውን ስንቅ በየልቦቻችን አኑሯል... መኖራችንም ውስጣችን በሚኖረው ተስፋ ላይ እንደተመረኮዘ እንቀጥላለን...

ትንሽም አልነው ትልቅ ልንንቀው በማንችለው መልኩ ተስፋ የመኖራችን ምክንያት ሆኖ እያኖረን አብሮን ይኖራል። መኖራችን ተስፋ የመኖሩ #ውጤት ሲሆን ተስፋችንም ከፈጣሪ መኖር ይመነጫል...

ያለተስፋ መኖር ኑሮን #ትርጉም አልባ እንዲሆን ያደርገዋል። ስለእኛ የሚያስበውም ፈጣሪ ይህን ስለሚያውቅ ተስፋ ቢስ ሆነን እንድንኖር ለቅፅበትም አይፈቅም።

ተስፋ አትቁረጥ! መባልህ ከሚሰጥህ ተስፋ የላቀ ተስፋ አለህ። ተስፋማ እንዳትቆርጪ መባልሽ ከሚሰጥሽ ተስፋ በላይ ተስፋ አለሽ። ተስፋ አትቁረጡ ከመባላችን በልጦ ያለው የተስፋችን ምንጭ ተስፋን የማይነጥቀን #ፈጣሪ ነው።

ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ ውስጥ አልፈን ወይ በማለፍ ላይ ሆነን ይሆናል... ግን ደግሞ ተስፋ በየትኛውም ሁኔታ የማይረታና የሚያበረታ ብርቱ #ሀይል ነውና ተስፋ ከመቁረጥ ውጪ አማራጭ ባጣንበትም ጊዜ ለልባችን የሚደርስ ጥሪ መኖሩ አይቀርም... ጥሪውም ተስፋ እንድናደርግ የሚያደርግ ነው።

ተስፋ የሚያስደርገንን ማጣታችን ተስፋ ላለማድረግ እንዳይዳርገን #ተስፋ የማይስቆርጠውን በእኛ ላይም ተስፋ ያልቆረጠውን ፈጣሪን ተስፋ አድርገን እንንቀሳቀስ!...

ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታማ ይገጥመናልኮ... ስንት ጊዜስ ተሸንፈን የለ?... ፈጣሪ ግን በተሸናፊዎች ተስፋ አይቆርጥም #አሸናፊ ሊያደርገን ፈልጎ ልባችንን የእርሱ መንገሻ እንድናደርግ ይጠይቀናል...

በሚዝልና በሚደክም በሚታመምና በሚቆስል ልባችን ውስጥ መሆን ለሚሻው ፈጣሪ በምንሰጠው #ፈቃድ በትክክልም የኛ መንገድና የኛ አካሄድ ይስተካከላል... ተስፋ እንደሌለው ሰው እንዳንኖር በሚያደርግ ተስፋ በመሞላት፤ በሚነግስብን መልካም ተፅዕኖ ምክንያት ተስፋ ማድረጋችንን እየወደድን እንኖራለን...

ተስፋ አድራጊ ዛሬው ላይ ማንንም ሳይሆን ነገን የሚያውቀውን ፈጣሪን የሾመ ስለሆነ በማዕበል ተከቦ እንኳ ተረጋግቶ ይኖራል... በስጋት ታጥሮ እንኳ #በሰላም ተኝቶ ይነጋለታል...

ጨለማ ተስፋን ተቃራኒ ነው፤ ተስፋ በፈጠረን እጅ ነው ስንልም #ብርሃን በእጁ አለ ማለታችን ነው። በፈጣሪ እጅ ተይዘን ስንኖር ከተስፋ የራቅንና ከተስፋ የተላቀቅን የመሰለን እለት በተስፋ የሚያስጉዘው ፈጣሪ ዘንድ ብርሃን እንዳለ ለማየት የልቦቻችንን አይኖች እንግለጥ...

- ፈጣሪ እያለ በየት በኩል ጨለማ ይነግስብሃል? ደክመህ ከሆነ ማበርታት የሚያውቅ መልካም ሰሪ አለህኮ...

- ፈጣሪ እያለ እንዴት ሆኖ አበቃ ትያለሽ? አቃተኝ ይሄንንማ አልችለውም የማይል ምንም የማይሳነው ሰሪ አለሽኮ...

ተስፋችንንማ ከደካማው ጉልበታችን ከሚታክት አእምሮአችን አንቀዳም!... ይልቅስ የፈጠረን ፈጣሪጋ ተስፋ አለ! ልዩ ተስፋ! የማይቆረጥና የማይቋረጥ ተስፋ ስለሆነ የተስፋን ምንጭ አንዘነጋም... የተስፋ ምንጫችንን ርቀን ለመድረቅ አንዘናጋም...

+ የኔ ተስፋ አበቃኮ ተቀበረ ስል አንድ ነገር ገባኝ ተስፋ አይሞትም ግን በመቃብር ሊያድር ይገደድ ይሆናል... ምንም ሆነ ምንም እንኳንም ትንሳኤ ኖረ አልኩኝ!

- በህይወት አለሃ? ስለዚህ ልትኖርለት የሚገባውን አላማ ለመኖር በቂና ምርጥ ተስፋ አለህ

- በህይወት አለሻ? ስለዚህ ልትኖሪለት የሚገባሽን አላማ ለመያዝ ድንቅና ልዩ ተስፋ አለሽ

ራሳችንን ለማነሳሳት የምናደርገው ጥረት አይደለም ተስፋ ሞልቶ የሚያስነሳን ፈጣሪ ዛሬም እያኖረን መሆኑ ግን እውነተኛ #አቅም ይሠጠናል!...

- ፈጣሪ የማትወደደውን ከወደደህና አንተን ለፈጠረበት ውድ አላማ ሊያኖርህ ካሻው ለምን ትከለክለዋለህ?...

- ፈጣሪ የማትወደጂውን ከወደደሽና አንቺን ለፈጠረበት ውድ አላማ ሊያኖርሽ ከፈለገ ለምን እሺ አትዪውም?...

ተስፋ እንዳልቆረጠብንና #እድል ሊሰጠን እንደሚሻ በሚጨምርልን የእድሜ ቀን እየነገረን ያለውን ፈጣሪን ተስፋ ከሆንከኝማ በደስታ የምትቀበለኝ አንተንማ በየማለዳው እቀበልሃለሁ እንበለው!...

በማንም ድጋፍ አትነሳ አለዛ ታላቅ አወዳደቅ ትወድቃለህ!... በማንም እገዛ አትቁሚ አለዛ ክፉ ስብራት ትሰበሪያለሽ!... ማደስም መፈወስም በሚችለው ተስፋ አድርጉኝ ብሎ ተስፋ በሰጠን #ፈጣሪ ስንታገዝ ግን ከትላንት የፀለመ ጨለማ እናልፋለን! ከትላንት የባሰ ችግር እንፈታለን!... ከትላንት የከበደ ፈተና በድል እንሻገራለን!...

ከትላንት ይልቅ ተስፋ እያደረግን እንኑርና ፈጣሪን አጥብቀን #ተስፋ እናድርገውና ለመኖር የልቦቻችንን አይኖች እንግለጥ... የማያሳፍር ተስፋ እንደሚያኮራ እናያለን። ተስፋ አለኝ ሊያውም ተስፋዬ የማይቆረጠውና የማይቋረጠው ፈጣሪ ነው በል! በዪ! እንበል!

የሆነ ቀን ተስፋ ሞቶ፤ ካፈር ገብቶ፤ የተቀበረና ያበቃ የመሰለን ቀን ፈጣሪን ለሚያምን ልባችን እንዲህ እንንገረው!
“በመቃብር ተስፋ አደረ፤
እንኳንም #ትንሳኤ ኖረ።”

በየአብስራ የተጻፈ

ለተፈጠርንበት አላማ ያኑረን
@sew_mehon_sew_nenena
207 viewsedited  18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 18:15:28
“እንኳንም ትንሳኤ ኖረ!”
በየአብስራ የተጻፈ

>>በየሳምንቱ ሃሙስ ማታ 3:00 መልካም ሃሳቦች ወደእናንተ ይደርሳሉ።

ለተፈጠርንበት አላማ ያኑረን
@sew_mehon_sew_nenena
159 views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ