Get Mystery Box with random crypto!

#ስንክሳር

የቴሌግራም ቻናል አርማ senksarorthodox — #ስንክሳር
የቴሌግራም ቻናል አርማ senksarorthodox — #ስንክሳር
የሰርጥ አድራሻ: @senksarorthodox
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 738
የሰርጥ መግለጫ

"ፍቅር ያጌብርኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል።ይህ የቴሌግራም ገጽ በየዕለቱ የሚከብሩትን የቅዱሳን ታሪክ(ስንክሳር) የምናነብበትና ጥያቄ የምንጠያየቅበት ነው።
✝️የየዕለቱ መርሐ ግብራት
👉ጠዋት እስከ ፫ ሰአት የዕለቱ ስንክሳርና ወንጌል ይላካል።
👉ማታ ፲፪ ሰአት ከዕለቱ ስንክሳርና ወንጌል የተውጣጡ ጥያቄዎች ይላካሉ።(የጥያቄና መልስ ውድድር)

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-02-18 01:42:10
299 views22:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-18 01:41:49 ††† እንኳን ለጻድቁ አባ አውሎግ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
*
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ አውሎግ አንበሳዊ †††

††† አባ አውሎግ ማለት:-
*ከቀደመው ዘመን ጻድቃን አንዱ::
*እንደ ገዳማውያን ፍፁም ባሕታዊ::
*እንደ ሐዋርያት ብዙ ሃገራትን በስብከተ ወንጌል ያሳመኑ::
*በግብፅና በሶርያ በርሃዎች ለ90 ዓመታት የተጋደሉ ጻድቅና ሐዋርያ ሲሆኑ የሚጉዋዙበትና የሚታዘዛቸው ግሩም አንበሳ ነበር::
*በዚህም አባ አውሎግ "አንበሳዊ" ስትል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትጠራቸዋለች::

አባ አውሎግ ከሚታወቁበት አገልግሎት አንዱ ስብከተ ወንጌል ነው:: ምንም እንኩዋ ገዳማዊ ቅዱስ ቢሆኑም ያላመኑትን ለማሳመን : ያመኑትንም ለማጽናት ተጋድለዋል::

እግዚአብሔር በሰጣቸው አናብስት በአንዱ ላይ ተጭነው (መዝ. 90) : በሌላኛው ላይ እቃቸውን አስቀምጠው በየአኅጉራቱ ከመምህራቸው ቅዱስ አውሎጊን ጋር ይዘዋወሩም ነበር:: የጌታ ቸርነት ሆኖም አናብስቱ የቅዱሳኑን ፈቃድ ሳይነገራቸው ያውቁ ነበር::

ሲርባቸውም ተግተው ይመግቧቸው ነበር:: እንዲያውም አንዴ ቅዱሳኑ እንደራባቸው አንዱ አንበሳ ሲያውቅ ከበርሐ ወደ ገበያ መንገድ ወጥቶ ተመለከተ:: በአህያ ላይ ልጁንና ስንቁን (ዳቦ) ጭኖ የሚሔድ ሽማግሌ ነበርና ዳቦውን አንስቶ ወስዶ ለእነ አባ አውሎግ ሰጣቸው::

ከድንጋጤ የተነሳም ሕጻኑ ሙቶ ነበርና ሽማግሌ አባቱ አዘነ:: አንበሳው ግን ሕጻኑንም ወደ ቅዱሳኑ ወስዶ አስረከበ:: ቅዱሳኑም ከሕብስቱ በመጠናቸው በልተው ቢባርኩት እንዳልተበላ ሆነ:: ሕጻኑንም ከሞት በጸሎታቸው አስነስተው ለአንበሳው ሰጥተውታል::

አንበሳውም ስንቁንና ልጁን ለአረጋዊው ሰጥቶት በደስታ ወደ ሃገሩ ተመልሷል:: ቅዱስ አባ አውሎግና መምህሩ አውሎጊን ከ90 ዓመታት በላይ በዘለቀ ተጋድሏቸው አጋንንትን ያሳፍሩ ዘንድ : ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ንጹሕ መስዋዕት ይሆኑለት ዘንድ በትጋት ኑረዋል::

¤ብዙ ተአምራትን ሠርተው ፈጣሪያቸውን አክብረዋል::
¤እንደ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ባሕር ከፍለዋል::
¤እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሙት አንስተዋል:: ድውያንን ፈውሰዋል::
¤እንደ ቅዱስ ዳንኤል አናብስትን ገዝተዋል::
¤ይህች ቀን ዕለተ ዕረፍታቸው ናት::

††† ቅዱስ በላትያኖስ †††

††† ይህ ቅዱስ ሐዋርያዊ ዻዻስ የቀድሞዋ ሮም ሊቀ ዻዻሳት ሲሆን ቸር : ትጉህና በጐ እረኛ ነበር:: መናፍቃንን ሲያርም : ምዕመናንን ሲመክር : ስለ መንጋው እንቅልፍ አጥቶ ኑሯል:: በፍጻሜውም በዚህች ቀን የሮም ንጉሥ ለ1 ዓመት አሰቃይቶ ገድሎታል:: ዕሴተ ኖሎትን (የእረኝነት ዋጋንም) ከጌታችን ተቀብሏል::

††† አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

††† የካቲት 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ አውሎግ አንበሳዊ
2.አባ አውሎጊን ጻድቅ (የአባ አውሎግ መምሕር)
3.አባ በትራ (የጻድቁ አባ ስልዋኖስ ደቀ መዝሙር)
4.አባ በላትያኖስ ሰማዕት (የሮም ሊቀ ዻዻሳት የነበረ)
5.አባ አብርሃም ኤዺስ ቆዾስ
6.አባ መቃቢስ
7.አባ ኮንቲ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ያሬድ ካህን
2.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
4.ብፁዐን ኢያቄም እና ሐና
5.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ

††† "በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምንም ከኁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንደሆነ ታውቁ ዘንድ ነው::" †††
(ኤፌ. 1:19)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
275 views22:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-12 06:53:51
322 views03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-12 06:53:45
278 views03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-12 06:52:15 † † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን † †

††† እንኩዋን ለአባታችን "አባ ብሶይ ዼጥሮስ" እና "ቅዱስ ዕብሎይ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

††† አክርጵዮስ †††

በዚች ቀን የእስክንድሪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት አክርጵዮስ አረፈ። እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አስረኛ ነው። ይህም አባት እግዚአብሄርን የሚፈራ ንፁህ ቅዱስ ነው ።

በእስክንድርያ አገርም ቄስ ሆኖ የሚያገለግል ነበር ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ከላድያኖስ በአረፈ ጊዜ የእስክንድር አገር ህዝብና ኤጲስቆጶሳቱ መረጡት በወንጌላዊው ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።

ከዚህም በኃላ እንደ ሀዋሪያት መልካም ጉዞን ተጓዘ የእግዚአብሄርን ሀይማኖት ህይወት የሆነ ህጉንም እያስተማረ ቅዱሳት መፅህፍትንም እያነበበላቸውና እያስተማራቸው መንጋዎቹን ይጠብቃቸው ነበር ሁል ጊዜም ይመለከታቸዋል አንድ የብር አላድን ወይም አንድ የወርቅ ዲናርን ጥሪት አላኖረም ከእለት ምግቡ ከቁርና ከሀሩር ስጋውን ከሚሸፈንበት ልብስ በቀር ምንም አላከማቸም።

በዚህም ተጋድሎ አስራ ሁለት አመት ኑሮ ጌታችንንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

+*" ቅዱስ ዕብሎይ "*+

=>አባ ዕብሎይ በቀደመ ሕይወቱ ለ40 ዓመታት በኀጢአት የኖረ: እግዚአብሔር ለንስሃ ሲጠራው "እሺ" ብሎ : ለ40 ዓመታት በንስሃ ሕይወት ተመላልሶ በበርሃ የተጋደለ: እንባው እንደጐርፍ ይፈስ የነበረ: አጋንንትንም ድል የነሳና ለፍሬ: ለትሩፋት የበቃ ቅዱስ አባት ነው:: እግዚአብሔርም ብዙ ቃል ኪዳን ገብቶለታል::

<< ባርያ ሆኖ ያለ ኀጢአት: ጌታ ሆኖ ያለ ምሕረት የለምና ይቅር በለን !! >> (የአባ ዕብሎይ የንስሃ ጸሎት)

+*" አባ ብሶይ (ዼጥሮስ) "*+

=>ብሶይ (ቢሾይ) በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተለመደ
የቅዱሳን ስም ነው:: በተለይ በምድረ ግብ በዚህ ስም
ሰማዕታትም : ጻድቃንም ተጠርተውበታል:: ከእነዚህ
ቅዱሳን (ከገዳማውያኑ) አንዱ የሆነው አባ ብሶይም
(አንዳንዴ አባ ዼጥሮስም ይባላል) የዘመነ ጻድቃን ፍሬ
ነው::

+ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን ቤት ናት:: ያ ማለት ራሳቸውን
ለክርስቶስ የለዩ ሰዎች ይኖሩባታል:: እነዚህ ሰዎች
ከተለያየ ጐዳና እና ማንነት ሊመጡ ይችላሉ:: ቢያንስ ግን
በንስሃ የታጠቡ መሆናቸው ወደ ተቀደሰው አንድነት
እንዲገቡ ትልቅ መሠረት ይሆናቸዋል::

+ቅዱሳንም አንዳንዶቹ ከእናታቸው ማኅጸን ሲመረጡ :
ሌሎቹ ደግሞ ከኃጢአት ሕይወት የተመለሱ ሆነው
ይታያሉ:: ደስ የሚለው ደግሞ በንስሃ ከታጠቡ በሁዋላ
በፍጹም ልባቸው በመጋደላቸው እነሆ በሰማያዊ አክሊል
ተከልለዋል::

+አባ ብሶይ ዼጥሮስም ከኃጢአት ተመልሰው ለቅድስና
ከበቁ ቀደምት አበው አንዱ ነው:: ቅዱሱ ተወልዶ
ባደገባት ምድረ ግብጽ የታወቀ ሽፍታ : ዝሙተኛና ክፋቱ
የተገለጠ ሰው ነበር:: ለብዙ ዘመናት በእንዲህ ካለ ግብሩ
መላቀቅ ባይችል እግዚአብሔር ጥሪውን ላከለት::

+የአምላካችን የጥሪ መንገዱ ብዙ ነውና ለእርሱ ደዌን
ላከለት:: መቼም ወደድንም ጠላንም በሽታ ወደ
እግዚአብሔር የሚያቀርብ ጥሩ ፈሊጥ (አጋጣሚ) ነው::
ዛሬም ቢሆን ዘለን : ዘለን ስንሰበርና የሐኪም መፍትሔ
ሲጠፋ የግዳችን ወደ እግዚአብሔር ቤት (ወደ ጸበሉ)
እንቀርባለንና:: አምላካችን ስለዚህ ጥበቡ ይክበር
ይመስገን::

+ቅዱስ አባት ብሶይም በሽፍትነትና በኃጢአት ኑሮ ሳለ
ለሞት የሚያበቃ ደዌ ደርሶበት የአልጋ ቁራኛ ሆነ::
ኃይሉም ደከመ:: በእንዲህ እያለም በራዕዩ ያየው ነገር
ፍጹም አስደነገጠው::

መላእክት ነፍሱን ወስደው መካነ ኩነኔን ካሳዩት በሁዋላ
አለቀሰ::

+ይልቁን ሌቦችና ዝሙተኞችን ከ4 ሲቆራርጣቸው ስላየ
ፈጽሞ አዘነ : ተጸጸተ:: ፈጣሪውንም ዕድሜ ለንስሃ
እንዲሰጠው ተማጸነ:: ጌታንም "አምላኬ ሆይ! ከበሽታየ
ብታድነኝ : ዳግመኛ አልበድልህም:: ዓለምን ሁሉም ንቄ
አገለግልሃለሁ" ሲል ተማጸነው::

+እግዚአብሔርም ሰምቶት ፈጥኖ ፈወሰው:: አባ ብሶይም
እንደ ቃሉ በፍጹም ልቡ ንስሃ ገብቶ መነነ:: በገዳመ
አስቄጥስ (ግብጽ) ለ38 ዓመታት ሲኖር የላመ የጣመ
በልቶ : ከሞቀ መኝታ ተኝቶ አያውቅም::

+ሰውነቱን ይቀጣት ዘንድም እስከ 30 ቀን ያለ እህል ውሃ
ይጾም ነበር:: በዘመኑ ሁሉም የሴት መልክን አላየም::
ንስሃን የሚወድ ጌታም ጸጋውን አብዝቶለት ብዙ ድርሳናትን
ጽፏል:: የሚገርመው ደግሞ ከትህትናውና ቅድስናው
የተነሳ የእያንዳንዱ ሰው ኃጢአት ተገልጦ ይታየው ነበር::

+ቅዱሱ አባታችን ብሶይ ዼጥሮስ በንስሃና በቅድስና
ሕይወት እንዲህ ተመላልሶ በዚህች ቀን ዐርፎ በገዳሙ
ተቀብሯል:: የድካሙን ዋጋም አድልዎ ከሌለበት :
ከእውነተኛው ፈራጅ ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ተቀብሏል::

=>አምላከ ቅዱሳን ዕድሜ ለንስሃ : ዘመን ለፍስሐ
አይንሳን:: ከክብረ ቅዱሳንም ያካፍለን . . . አሜን !!

=>የካቲት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ዕብሎይ ገዳማዊ
2.ቅዱስ አባ ብሶይ ጻድቅ
3.አባ አክርዽዮስ
4."49" አረጋውያን ሰማዕታት (ፍልሠታቸው)
5.ቅዱስ አሞኒና ሚስቱ ቅድስት ሙስያ (የታላቁ ዕብሎይ ወላጆች)
6.አባ ኖብ ጻድቅ : መነሳንሱ ዘወርቅ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ

=>አምላክ በበረከታቸው ይባርከን::

=>+"+ መቶ በግ ያለው : ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ 'የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል:: +"+ (ሉቃ. 15:3-7)

†ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
†ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር አሜን †
248 views03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ