Get Mystery Box with random crypto!

𝘾𝙔𝙉𝙊𝙎𝙐𝙍𝙀 2𝙠13 𝘽𝘼𝙏𝘾𝙃

የቴሌግራም ቻናል አርማ senjo_squad — 𝘾𝙔𝙉𝙊𝙎𝙐𝙍𝙀 2𝙠13 𝘽𝘼𝙏𝘾𝙃 𝘾
የቴሌግራም ቻናል አርማ senjo_squad — 𝘾𝙔𝙉𝙊𝙎𝙐𝙍𝙀 2𝙠13 𝘽𝘼𝙏𝘾𝙃
የሰርጥ አድራሻ: @senjo_squad
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 227
የሰርጥ መግለጫ

𝔸𝕤𝕡𝕚𝕣𝕖 𝕋𝕠 𝕀𝕟𝕤𝕡𝕚𝕣𝕖 𝔹𝕖𝕗𝕠𝕣𝕖 𝕎𝕖 𝔼𝕩𝕡𝕚𝕣𝕖
"Don’t try to find every answer of life because once you find answers life will change the question paper!"
IG account - cynosurebatch
For any comment - http://telegram.me/Senjo2k13_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-30 13:53:42 Announcement

Original ye 12 result paper selemexa hedachu ke timhrt bet wesedu clearancem cheresu !!!
1.1K viewsedited  10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-28 12:11:20 Announcement

Mekeyeraw web bemestekakelu bechalachihut ftnet hedachu mastekakel tchilalachu
1.6K views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 10:26:38 Ketach balew bot abetutachihun makereb tchilalachu

@tikvahmagbot
1.2K viewsedited  07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-26 09:10:33 Temariwoch ye gibi mircha ena stream choice mastekakel ayichalem bemebalu ye Tikvah Ethiopia bot lay kiretachihun bemasemat mels endigegn tebaberu bemalet brother Amanuel melkt astelalfual.
1.1K viewsedited  06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-25 14:18:31 Announcement

የstream እንዲሁም የሀገር ምርጫ ማስተካከያ ለጊዜው የተዘጋ መሆኑን ልንገልፅ እንወዳለን። ስለዚህም ት/ቤት መሄድ አይጠበቅባችሁም። አዲስ መረጃ ስናገኝ እኛው የምንለቅላቹ ይሆናል።
1.1K views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-23 16:12:56
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት #እንዳያገለግል ተወስኗል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል።

ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ።

ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

ይህ በዲህ እንዳለ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት ይገለፃል።

ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።

1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et

2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et

3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot

4) በ9444 SMS ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

(የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ)

@tikvahethiopia
711 views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-23 16:12:56 የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት መግለጽን ይመለከታል ፦

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር ከቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም ለወንድ 293,865 ሴት 250,703 ድምር 544,568 ተማሪዎች የተሰጠ ሲሆን ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በመጀመሪያው ዙር ሳይፈተኑ ለቀሩ ለወንድ 27,979 ሴት 26,456 ድምር 54,435 ተማሪዎች ደግሞ ከጥር 24-27/2014 ዓ.ም በሁለተኛው ዙር ፈተናው ተሰጥቷል። በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ከተመዘገቡት 617,991 ተማሪዎች ውስጥ ወንድ 321,844 ሴት 277,159 ድምር 599,003 (96.9%) ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ችለዋል።

የፈተና እርማቱ ደህንነታቸው አስተማማኝ በሆኑና ከንክኪ ነጻ በሆኑ የማረሚያ ማሽኖች አስፈላጊው የደህንነት ጥበቃ በፌደራል ፖሊስና በሴኩሪቲ ካሜራዎች ታግዞ በጥንቃቄ ተከናውኗል። ከዚህ በተጨማሪም የፈተናዎች ውጤት በትምህርት ዓይነት፣ በትምህርት ቤትና በተማሪ ደረጃ ሰፊ የውጤት ትንተና በማካሄድ የእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት ውጤት ተገምግሟል።

በዚሁ መሰረት የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል ተወስኗል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል። ነገር ግን በተናጠል የፈተና ደንብ ጥሰት የፈጸሙ 141 ተማሪዎች ላይ ከውጤት መሰረዝ ጀምሮ በየደረጃው የተለያየ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።

ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ። ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።

ስለሆነም ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።
1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et
2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et
3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot - በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባትና Exam Result የሚለውን በመጫን በመልክት መጻፊያው ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት እና የ ምልክት በመጫን መላክና ውጤታቸው ማየት ይችላሉ።
4) በ9444 የ ኤስ ኤም ኤስ (9444 SMS) ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

(የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ)

@tikvahethiopia
406 views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-19 11:56:09
ጥንቃቄ #Grade12+1

የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን ልክ መሆኑ ና portal ላይ መግባቱን ቼክ አድርጉ

http://result.neaea.gov.et/Home/Choice

በተለይ የፊልድ ምርጫችሁን ቼክ አድርጉ። አምና ብዙ ልጆች ሳይፈልጉ #teaching ገብቷል።

Join
@Ethio_Students_Only
@Ethio_Students_Only
494 views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-17 15:11:32
የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይገለፃል ?

በርካታ የ ' ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ' ተማሪዎች ፣ ወላጆች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቼ እንደሚገለፅ መረጃ እንድናጋራቸው ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን ባገኘው መረጃ መሰረት የ12ኛ ክፍል የሁለተኛ ዙር ፈተና እርማት እየተጠናቀቀ ይገኛል።

እስከ የካቲት 15 ድረስ ዘገየ ቢባል እስከ የካቲት 20 ድረስ የውጤት ስራው ተጠናቆ ሊገለፅ እንደሚችል ሰምተናል።

ውጤት ከተገለፀ በኃላ በፍጥነት ወደ ምደባው እንደሚገባ የተገለፀልን ሲሆን በጣም ዘገየ ቢባል እስከ የካቲት 30 ድረስ ተማሪዎች ምደባቸውን እንዲያውቁ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል ተብለናል።

ከምደባው በፊት ግን ቅሬታዎችን ቀድሞ ለመፍታት ይረዳ ዘንድ አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውን በፍጥነት እንዲያስገቡ ተጠይቋል።

ማመልከት የሚችሉት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ፣ መስማት የተሳናቸው እና የማየት ችግር ያለባቸው ተማሪዎች፣ ልዩ ልዩ የጤና ችግር ያለባቸው ተማሪዎች፣ የሚያጠቡ እናት ተማሪዎች ፣ የተመሳሳይ ጾታ መንትዮች ሲሆኑ ዝርዝር መረጃ በዚህ ይገኛል [ https://t.me/TikvahUniversity/2623 ]

በሌላ በኩል ፤ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ስለ ፈተና እርማት ጠይቀናቸው እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልፀውልናል።

በሁለተኛ ዙር ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ከመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ጋር አብሮ እንደሚገለጽ ነግረውናል።

ተማሪዎች እና ወላጆች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እራሳችሁን እንድትጠብቁ መልዕክት እናስተላልፋለን።

@tikvahethiopia
433 views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 10:05:50
እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
መልካም የገና በዓል ለሁላችሁም

@senjo_squad
1.4K views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ