Get Mystery Box with random crypto!

ጥያቄ:- የማህፀን በር 'ቅደመ ካንሰር' ምልክቶችን እንዴት ማወቅ ይቻላል? መልስ :- ሰላም!! | ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል 🔍💊💉

ጥያቄ:- የማህፀን በር 'ቅደመ ካንሰር' ምልክቶችን እንዴት ማወቅ ይቻላል?
መልስ :-
ሰላም!!
የማህፀን በር ካንሰር(cervical cancer) ሁሉት አይነት የደረጃ መገለጫዎች አሉት : ቅደመ ካንሰር ደረጃ እና ከፍተኛ ደረጃ::
ቅደመ ካንሰር ብዙ ጊዜ ምልክት የለውም :: የሚታወቀው ፓፕ ስሜር በሚባል የማሃፀን ምርመራ አይነት ነው:: ብዙ ጊዜ በ20 ዎቹ መጨረሻ እና በ30ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሴቶች ላይ በምርመራ የሚታይ ሲሆን ÷ ከፍተኛ የካንሰርነት ደረጃ ደግሞ በአብዛኛው ከ45- 50ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሴቶች ላይ ከምልክቶች ጋር ይታያል!

#አጋላጭ #ሁኔታዎች
የማህፀን በር ቅደመ ካንሰር ና ካንሰር ደረጃ አጋላጭ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው:-
1. በ'ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ'(HPV 16 &18) መጠቃት:- ይህ ቫይረስ 70% ለምጠጋ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር መንስኤ ሲሆን የምተላለፈውም በልቅ ግብረ ስጋ ግንኙነት ነው::
2. ከአንድ በላይ ሰዎች ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ(በተለያየ ወቅትም ሊሆን ይቻላል)
3. ከሀያ ዓመት እድሜ በታች የሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት
4. በለጋ እድሜ ልጅ መውለድ(ከ20 በታች)
5..በአባላዘር በሽታዎች መያዝ
6. በኤች አይ ቪ ቫይረስ የተጠቁ ከሆነ ተጋላጭነት ይጨምራል
7. ሲጋራ(ወይም ትምባሆ) ማጨስ
አንዳንዴ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን መጠቀም (OCP) ለማህፀን በር ካንሰር የመጋለጥ ዕድል እንደሚጨምር ጥናቶች ያሳያሉ::

#ከ ምልክቶች በጥቂቱ?
1. ለየት ያለ በማህፀን የሚወጣ ፈሳሽ
2. ያለወትሮ ከፍተኛ የሆነ በማህፀን የደም መፍሰስ መታየት
3. ከግብረ ስጋ ግንኙነት በኃላ የሚከሰት የደም መፍሰስ
4.ዳሌ አካባቢ እና የጀርባ ህመም ዋነኞቹ ናቸው::
#ማስታወሻ.1:- የዳሌ ህመም ÷ሽታ የለው የማህፀን ፈሳሽ ÷ ከእምብርት በታች የሆድ ህመም : የማህፀን ኢንፌክሽን (PID) ወይም የአባላዘር በሽታ ምልክት ሊሆን ይቻላል :: ስለዚህ ይህን ምልክቶች ለመለየት በቅርብ ያሉ ሕኪሞች ጋር ሄዶ መታየት ይገባል::
#ማስታወሻ.2.
የማህፀን በር ካንሰር አብዛኛውን ጊዜ #ምንም ምልክት ሳያሳይ በቅደም ካንሰርነት ደረጃ እስከ 10ዓመት ሊቆይ ይቻላል :: አንዳንዴ የሰውነት "በሽታ የመከላከል" አቅም ከተዳከመ ከዚህ ባጠረ ጊዜ ምልክት ያሳያል::

ቅደመ ካንስርን #የማወቂያ #ብቸኛ መንገድ "#ፓፕ ስሜር" የተባለውን ምርመራ ማደረግ ነው::
እድሜቸው ከ21 ዓመት እስከ 65 ዓመት የሆኑ ሴቶች በየ 3 ዓመቱ ይህንን ምርመር ማደረጋቸው "የቅደመ ካንሰር" ምልክት መኖሩን ለማወቅ እንዲሁም ነገሩ ስይወሳሳብ እና አደገኛ ደረጃ ስይደርስ ለማከም ይረዳል::
ምርመራው በብዙ ሆስፒታሎች እንዲህም በአንዳድ የማህፅን ና ፅንስ ሰፔሻሊት ክሊኒኮች ይገኛል::
የዚህ ምርመራ ዋጋ ውድ አይደለም ስለዚህ እድሜያቸው ከ 21 እስከ 65 ዓመት የሆናቸው ሴቶች አገልግሎቱ በሚሰጥበት የጤና ተቋም በመሄድ እንዲመርመሩ ና የጤና ሁኔታቸው እንዲያውቁ #አበረታታለሁ::

መልካም ጊዜ::
ዳንኤል አበበ(MD)(ሲንየር ጠቅላላ ሀኪም)