Get Mystery Box with random crypto!

ስትሮክ ክፍል አንድ ስትሮክ በአንጎል ውስጥ ያለው የደም | ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል 🔍💊💉

ስትሮክ

ክፍል አንድ
ስትሮክ በአንጎል ውስጥ ያለው የደም ዝውውር በሚስተጓጎልበት ወቅት የአንጎል ሴሎች(ሕዋሶች) እንዲሞቱ የሚያደርግ የጤና እክል ነው። ሁለት ዋና ዋና የስትሮክ አይነቶች አሉ። እነርሱም በአንጎል ዉስጥ በደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰትና በደም ቧንቧ መዘጋት ወይም መጥበብ ምክንያት ወደ አንጎል የሚሄድዉን ደም መጠን በመቀነስ የሚከሰቱ ናቸዉ። ሁለቱም የአንጎል ክፍሎች ሥራቸውን በትክክል እንዳያከናዉኑ ወይም እንዲያቆሙ ያደርጉታል። ስትሮክ የሚከሰተው የአንጎላቸን የደም አቅርቦት በሚቀነሱ ወይም በመዘጋቱ ምክንያት ነው። ስትሮክ የድንገተኛ ህክምና ስለሚፈልግ ፈጣን ህክምና መስጠት ወሳኝ ነው። አስቀደም እርምጃ መውሰድ የአንጎል ጉዳትንና ሌሎች ችግሮችን ሊቀንስ ይችላል።

የህመም ምልክቶች
ለመናገር መቸገር እንዲሁም ሌሎች የሚሉትን ለመረዳት መቸገር፦ ግራ መጋባት፣ ቃላት/ድምፅ ማዉጣት መቸገር ወይም ንግግር መረዳትን መቸገር
የፊት፣ ክንድ ወይም እግር ሽባ መሆን ወይም መደንዘዝ፦ በድንገት የመደንዘዝ ስሜት፤ ፊት ፣ ክንድ ወይም እግር ላይ ድክመት ወይም ማንቀሳቀስ መቸገር። ይህ ብዙውን ጊዜ አንድን የሰውነት ክፍል በቀኝ ወይም ግራ ብቻ ምልክቱ ይታያል።
በአንድ ወይም በሁለቱም አይኖች ላይ የማየት ችግር መከሰት
በአንድ ወይም በሁለቱም አይኖች ላይ በድንገት ብዥ የማለት ወይም ጭልም ማለት ሊኖርዎት ይችላል ወይም አንድ ነገር ሁለት ሆኖ የመታየት ችግር ሊኖር ይችላል።
የራስ ምታት፦ ከድንገተኛና ከባድ ራስ ምታት ጋር ተያይዞ ማስታወክ፣ መፍዘዝ ወይም የንቃተ ህሊና መቀነስ ወይም እራስን መሳት የስትሮክን ሊያመለክት ይችላል።
ለመራመድ መቸገር፦ የባላንስ ማጣት፣ እንዲሁም ድንገተኛ ማዞር ወይም ቅንጅት ማጣት (loss oc coordination) ሊኖርብዎ ይችላል።

መንስኤዎች
ለስትሮክ ሁለት ዋና ዋና መንሰኤዎች አሉ እነርሱም የደም ቧንቧ መዘጋት ወይም በደም መርጋት የሚከሰት( ኢስኬሚክ ስትሮክ)ና የደም ቧንቧ መፈንዳት ችግር ምክንያት የሚከሰቱ( ሄሞረጂክ ስትሮክ) ናቸዉ። አንዳንዶች ደግሞ በአንጎል ውስጥ ያለው የደም ፍሰት በጊዜያዊነት ብቻ መስተጓጎል ሊገጥማቸዉ ይችላል። በዚህም ምክንያት የህመም ምልክቶቹ ለአጭር ጊዜ ብቻ ሊታይ የሚችል ሲሆን ይህም ትራንዚየንት ኢስኬሚክ አታክ(TIA) ይባላል።

በደም መርጋት ምክንያት የሚከሰት (Ischemic stroke)
ይህ አይነቱ በጣም የተለመደና በብዛት የሚከሰት የስትሮክ አይነት ነዉ። ይህ የአንጎል የደም ስሮች ሲጠበቡ ወይም ሲዘጉ የሚከሰት ሲሆን ወደ አንጎል የሚሄድን የደም ዝውውርን በእጅጉ እንዲቀንስ ያደርጋል (ischemia) ።
የተዘጉ ወይም የጠበቡ የደም ስሮች የሚከሰቱት በደም ስሮች ውስጥ በሚጠራቀሙ የስብ ክምችቶች፣ በደም መርጋት ወይም በደም ዝውውር ውስጥ በሚጓዙና ከልብ ተነስተዉ በደም ስሮች ዉስጥ ተሰክተዉ በሚቀሩ ሌሎች ነገሮች ምክንያት ነው።


አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ

https://www.facebook.com/sturaelclinic/
https://www.sturaelclinic.com/
9424
+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
https://sturaelclinic@gmail.com