2023-03-10 09:01:28
የፀጉር ቅባት
የትኛውም የፀጉር ቅባት ፣ ከተፈጥሮ ውጪ የፀጉር ርዝመትን አይጨምርም። ነገር ግን፣ እንክብካቤ የጎደለው ፀጉር ጥንካሬውን ስለሚያጣ ከእድሜው በፊት ይሰባበርና የፀጉርን ርዝመት ያሳጥራል።
አንዳንድ ሴቶች፣ ለፀጉራቸው እንክብካቤ፣ ከቅባት ይልቅ ቅቤ መቀባትን ይመርጣሉ። አንዳንድ ሴቶች ደሞ፣ ቅቤ የሚፈጥረውን መጥፎ ጠረን በመጥላት እና የቀለጠው ቅቤ ፊታቸውን ሲነካ ስለማይወዱ፣ ቅቤ ከመቀባት ይልቅ የፀጉር ቅባትን ይመርጣሉ።
አንድ ሰው፣ ውብ የሆነ የፀጉር ገፅታ እንዲኖረው መጀመሪያ የፀጉሩን ተፈጥሮአዊ ባህሪ ማወቅ አለበት።
የፀጉሩን አይነት ባማከለ መልኩ በቂ የሆነ የፀጉር እንክብካቤ ሲኖር እና ፣ፀጉር ልከኛ በሆነ መንገድ የሚዋብ ከሆነ ጥንካሬውን እና ውበቱን እንደጠበቀ መቆየት ይችላል።
በቂ እንክብካቤ የሌለው ፀጉር ፣ ለማስዋብ ሲባል ከልክ ባለፈ መልኩ የሚንገላታ ከሆነ፣ ፀጉሩ በግዜ ሂደት በቀላሉ የሚበላሽ እና በተፈለገው መንገድ ለማስዋብም አስቸጋሪ እየሆነ ይሄዳል።
ፀጉር በተፈጥሮው አንዴ ከተበላሸና ፣ተፈጥሮአዊ ገፅታውን ካጣ በኋላ፣ የተበላሸውን የፀጉር ከመቁረጥ ውጪ፣ ፀጉሩን በቋሚነት ወደነበረበት ገፅታው ለመመለስ የሚያስችል የፀጉር ቅባት የለም።
ነገር ግን፣ የተበላሸው ፀጉር ከተቆረጠ በኋላ፣ ከስር በአዲስ መልክ የሚበቅለውን ፀጉር ተፈጥሮአዊ ገፅታውን ሳይለቅ ለረጅም ግዜ እንዲቆይ የሚረዱ የተለያዩ የፀጉር ቅባቶች አሉ።
አንድ የፀጉር ቅባት፣ ለፀጉር እንክብካቤ ተመራጭ የሚሆነው፣ የፀጉርን ዘለላ በደምብ የማራስ ባህሪ ሲኖረው እና የፀጉሩን ተፈጥሮአዊ ይዘት የሚያጎላ ሆኖ ሲገኝ ነው።
ገበያ ላይ የተለያዩ የፀጉር ቅባት አይነቶች ይገኛሉ፣ ከምርቶች ውስጥ ለአፍሪካዊ ፀጉር ተስመማሚ የሚሆኑት የተፈጥሮ እና የመአድን ዘይት መጠናቸው ከፍ ያሉ ቅባቶች ናቸው።
ገበያ ላይ የፀጉር ዘይቶች ለብቻቸው እንዲሁም ከተለያዩ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ጋር ተቀላቅለው ለተጠቃሚው ይቀርባሉ።
አብዛኛውን ግዜ በተጠቃሚዎች ዘንድ የሚታወቁት፣ የ Olive Oil እና Shea Butter ናቸው። እነዚህ ቅባቶች ሁለቱም ለአፍሪካዊ ፀጉር እንክብካቤ ጠቃሚ ናቸው። በተለይ Shea Butter, ከርዳዳ ፀጉር ላለው ሰው የፀጉርን እርጥበት እና ወዛማ ገፅታን ይጠብቃል።
ከነዚህም ውጪ፣ እንደ Coconut Oil, Jojoba Oil, Argan Oli, እና Tea Tree Oil የመሳሰሉ ለአፍሪካዊ የፀጉር አይነት ተመራጭ የሆኑ ቅባቶችም አሉ።
ስለነዚህ ቅባቶች ጠቀሜታ እና አይነታቸውን በተመለከተ በዩቲዩብ ቻናሌ ላይ ሰፋ ያለ መረጃ አቅርቤያለሁ።
የሚቀጥለውን Link በመጫን መመልከት ትችላላችሁ። አመሰግናለሁ ።
ለህክምና ቀጠሮ ብቻ ይሄን @LEKETERO ወይም @Apointment1
ተጭነው ስም እና ስልክ በማስቀመጥ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ። መልካም ግዜ
46.9K viewsDr. Seife, edited 06:01