Get Mystery Box with random crypto!

' ንባብ ለህይወት ' በደማቅ ስነስርዓት በይፋ ተከፍቷል!! ======================== | ነገረ መፃህፍት 📚📗📓📖

" ንባብ ለህይወት " በደማቅ ስነስርዓት በይፋ ተከፍቷል!!
=================================
ዛሬ በመክፈቻው ላይ መፅሐፎች እንደቆሎ ሲሸጡ ተመልክተናል!!



"ንባብ ለሕይወት" በሚል ርዕስ የመጽሐፍትና የምርምር ተቋማት የተሳተፉበት ዓውደ ርዕይ ዛሬ ከረፋዱ 5:00 ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሐላፊዎች ምሁራን በሙያቸው የተከበሩ ታላላቅ ኢትዮጵያውያን:አንጋፋና ወጣት ደራሲያን: ገጣሚያን ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከፍቷል:: ይህ ኤግዚቢሽን ከሐምሌ 28-ነሐሴ 2 ቀን 2014 ዓ ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይካሄዳል።በዚህ ፕሮግራም ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ አሳታሚዎች ደራሲያንና የምርምር ማዕከላት ተሳትፈውበታል:: በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢ ቡክስ (E-books ) በነጻ ተዘጋጅተዋል።አዳዲስ መጽሐፍት በቅናሽ ይሸጣሉ።ከገበያ የጠፉ ተፈላጊ መጽሐፍት፡ጋዜጦችና መጽሔቶችን የልጆችን የመማሪያና የተረት መጽሐፎች በኢግዚቢሽኑ ላይ ያገኛሉ።

በዚህ ኢግዚቢሽን ላይ ከ50 በላይ የአንጋፋና ወጣት ደራሲያን አዳዲስ መጽሐፍቶች ይመረቃሉ።

ኢግዚቢሽኑ እስከ ነሐሴ 2 ቀን ድረስ የሚቆይ ሲሆን መግቢያው በነፃ ነው::