Get Mystery Box with random crypto!

Ricky Jackson ይባላል። Cleveland, Ohio ነዋሪ ሲሆን ገና በለጋ እድሜው ባልሰራው | ነገረ መፃህፍት 📚📗📓📖

Ricky Jackson ይባላል። Cleveland, Ohio ነዋሪ ሲሆን ገና በለጋ እድሜው ባልሰራው ወንጀል የሞት ፍርድ ተፍርዶበት 39 አመት ከታሰረ በሁዋላ (የሞት ፍርድ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር ካላፀደቁት ወደ እድሜ ልክ ይለወጣል አብዛኛውን ግዜ) ትክክለኛው ወንጀል ፈጻሚ በመገኘቱ ዳጎስ ያለ ካሳ ተከፍሎት (ነዋይ ግዜንና ሞራልን ባይመልስም) ነፃ የተለቀቀ ሰው ነው። ልክ ተለቆ ከእስር ቤት ሲወጣ ያሳሰረውን ሰው አገኘውና ... «ይቅር ብዬሃለው» .... ብሎ አቀፈው።

ቃለ መጠይቅ ላደረጉለት ጋዜጠኞች ደግሞ እንዲ ሲል ተናገረ ....«እስር ቤት ውስጥ ነህ ማለት እስረኛ ነህ ማለት አይደለም»....

☞ ነጻነት ያለው ያላችሁበት ስፍራ ላይ ሳይሆን አይምሯቹ ውስጥ ነው። የቂምና የጥላቻ እስረኛ እንዳትሆኑ ይቅር በሉ!!
ይቅር በሉ፣ መራመድ አታቁሙ ፣ ጉዳታቹ ላይ አትቆዩ! ህይወት ሰፊና ፣ ብዙ ደርዝ ያላት የጉዞ ሃዲድ ናት!!