Get Mystery Box with random crypto!

#አዳምና_ሔዋን_ዛሬ_ደስ_አላቸው!! 'ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ | 7 ቁጥር

#አዳምና_ሔዋን_ዛሬ_ደስ_አላቸው!!

"ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው። በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው። በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው። በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ። አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ፤ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት የተለያየ ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ።"

#ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ