Get Mystery Box with random crypto!

የስነ መለኮት ትምህርት ጀምሬ እርስት አረኩት አይደል? ይቅርታ! እኔ እንጃ፤ እግዚአብሔር በብ | Sapphi

የስነ መለኮት ትምህርት ጀምሬ እርስት አረኩት አይደል? ይቅርታ!

እኔ እንጃ፤ እግዚአብሔር በብዙ ረሀቤን እየመገበ ነው፣ በቃ ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ቃሉ፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሁሉ እየሰማሁ የምሆነውን እያጣሁ ነው።

ብቻ ምን አለፋችሁ፤ እንዴት ያለ ዓለም መሰላችሁ። ደስ ብሎኝ ነው assignment የምሰራው፤ እየወደድኩት ነው ወደ ክፍል የምገባው። ለእስካሁኑ ግን ይቅርታ እየጠየኩ፤ ጌታ ቢፈቅድ ከዚህ በኋላ የተማርኩትን ለማካፈል እሞክራለሁ።

በዚህ በመጨረሻ ዘመን እንድንፀና አደራ እላለሁ፤ ጌታችን መምጣቱ አይቀርም፣ እኛም ወደእርሱ መሄዳችን አይቀሬ ነው። ስለዚህ "መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫውን ጨርሻለሁ፤ ሃይማኖትንም ጠብቄአለሁ። ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ በዚያ ቀን ለእኔ ይሰጠኛል፤" ማለት አንድንችል ቀን ሳለ እንዘጋጅ።

@SapphireAni
Join
@SapphireAni