Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ የጨዋታ ቀን ነው! - «ከባድ ነው፡፡ ሜዳው ጭቃ ነበር፡፡ እንደልብ ለመጫወት የሚከብዱ ሁኔ | የታላቁ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፔጅ✌️❤️💛

ዛሬ የጨዋታ ቀን ነው!

-

«ከባድ ነው፡፡ ሜዳው ጭቃ ነበር፡፡ እንደልብ ለመጫወት የሚከብዱ ሁኔታዎች ነበሩ፡፡ ሆኖም አሸናፊ ለመሆን የቆጠብነው አቅም አልነበረም፡፡ ያሳደርነው እና ያስቀረነው ጉልበት አልነበረንም፡፡ ያለንን ኃይል ሁሉ ተጠቅመን ተጫናቸው፡፡ በተደጋጋሚ የግብ ክልላቸው ጋር መድረስ ቻለን፡፡ የግብ ዕድሎችን መፍጠር ተያያዝን፡፡ ደቂቃዎች ቢነጉዱም የተቃራኒ ቡድን የግብ ክልል ያለማቋረጥ መደብደብ ቀጠልን» ዳዊት መብራቱ (የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋች)

-

ሀምሌ 10 ቀን 1995 ዓ·ም ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ የነበረው የታሪክ ክስተት ላይ ይገኝ ነበር። ለደጋፊው ያ ዋንጫ ብዙ ትርጉም ነበረው። ጨዋታው ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ስለነበር «የዋንጫው ነገር አበቃ፣ አለቀ» ያሉ ብዙዎች ነበሩ። ነገር ግን ዋንጫ አይተው ወደኋላ የማይሉት፣ የማይቻለውን የሚችሉት፣ ታሪክ መስራት የማይሰለቻቸው፣ ሁሌ ለድልና ለስኬት ዘብ የሚቆሙት የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች ይህንን መስማት ፈፅሞ አልፈቀዱም ነበር።

-

ይህ ቀን የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች ከአፍ እስከገደፉ ካምቦሎጆን ሞልተው እስከ መጨረሻ ደቂቃ እምነታቸውን በእነርሱ ላይ ጥለው እየጨፈሩ ለጠበቋቸው ደጋፊዎቻቸው የትዕግስታቸውን ዋጋ የከፈሉበት ቀን ነው።

-

ዛሬ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ·ም ላይ እንገኛለን። ከ19 ዓመታት በኋላ የዛሬ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች እንደቀደሙ ፈረሰኞች ሁሉ የራሳችንን ታሪክ በደማቅ ቀለም ለመፃፍ ቀለማቸውን አዋህደዋል። ብራናቸውን ወጥረዋል። ታሪክ መስራት የማይሰለቻቸው ፈረሰኞች ታሪካቸውን ለመፃፍ የጨዋታውን መጀመር በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

-

ዛሬ አመቱን ሙሉ የነበረውን ውድድር በስኬት፣ በድልና፣ በአሸናፊነት የምንደመድምበት ዕለት ነው። በየአንዳንዱ ጨዋታ የነበረውን ደስታ፣ ሀዘን እና ህመም በስኬት የምናስርበት ቀን ነው።

-

እኛ ቅዱስ ጊዮርጊሳውያን ነን። በፍፁም ተስፋ መቁረጥ አናውቅም። ባህላችንም አይደለም። የለበስነው ማልያ ከተስፋ መቁረጥ የራቀ ነው። ዛሬም 90 ደቂቃ ከልጆቻችን ጎን ሆነን የጀመርነውን እንጨርሳለን። ካምቦሎጆን የሚያንቀጠቅጥ ድጋፍ ሰጥተን እንደ ሁሌው በጋራ ታሪክ እንሰራለን።

-

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲመሰረት መንገዶች አልጋ በአልጋ ሆነውለት አልነበረም። ጊዮርጊስ የህይወት ዋጋ ሳይቀር የተከፈለለት ክለብ ነው። ትላንትም ሆነ ዛሬ ለህልውናው አደጋ የሆኑበትን አንገት እያስደፋ ስሙን በታላቅነት የተከለ ክለብ ነው።

-

ከእግዚአብሔር ጋር ከድል በኋላ እንገናኛለን