Get Mystery Box with random crypto!

የጡዘት መጋረጃ ሲቀደድ ክፍል አንድ ሳሙኤል በለጠ ማስተዋወቂያ የስብስቡ ርዕስ:-ጡዘት የሕትመ | ሳሙኤል በለጠ(ባማ)

የጡዘት መጋረጃ ሲቀደድ
ክፍል አንድ
ሳሙኤል በለጠ

ማስተዋወቂያ

የስብስቡ ርዕስ:-ጡዘት
የሕትመት ዘመን:-2008 ዓ.ም
የግጥም ብዛት:-102 ግጥሞች

ፊዶር ደስቶቮስኪ በየትም አገር የገነነ ራሺያዊ ደራሲ ነው፡፡ ደስቶቮስኪ ከሚታወቅባቸው ስራዎች መካከል “white Nights” አንዱ ነው፡፡ በዚህ መጽሃፉ በፒተርስበንግ ከተማ ባይተዋር ስለሆነ ከስጋው ወደ ነፍሱ ስለሚያይ በምሽቱ የሚደንቅ አንድ ገጸ፟ ባህሪ አለ ዶስቶቭስኪ እንዲህ ጽፏል።

“My history!” I cried in alarm. “My history! But who has told you I have a history? I have no history....”
“Then how have you lived, if you have no history?” she interrupted, laughing.
“Absolutely without any history! I have lived, as they say, keeping myself to myself, that is, utterly alone—alone, entirely alone.[White Night ገጽ-16]

ሰውን 'ሚያህል ብርሃን ታሪኩ ሲያጨልመው ታሪክን 'ሚያህል ታላቅ ነገር ሰው ሳይሰራው ሲቀር ከዚህ የበለጠ 'ሚለበልብ ምን ጸጸት አለ? ገጣሚና ጋዜጠኛ ፋሲል ተካልኝ ይህንን ጉዳይ አብሰልሶሎታል።
“…ሰፊ ሆኖ ተገኝቶ እንደ ጨርቅ ታሪኬ
ተንዘልዝሎ ቀረ አልሆን አለ ልኬ።
ከልደት እስከ ሞት ሲተረክ ሰማሁት
የሕይወት ታሪኬ ላይ ታሪኬን አጣሁት።”
ፋሲል ተካልኝ
[ጡዘት ገጽ-30]

በሕይወት ታሪካችን ታሪካችን ከሌላ እኛ ምንድነን? ማነን? የፍልስፍናው አባት ሶቅራጠስ እንዳለው ነው። "unexamined life is not worth living" (ያልተመረመረ ሕይወት ሊኖር አይገባም!) ዶ/ር በድሎ ዋቅጅራ "ለራስ ወቀሳ" 'ሚል ግጥም አላቸው ከራስ ፀበሉ የተጣላን አንድ 'ራስ የሚወቅሱበት ከእድሜ እድሜ ምንም ቀለም፣ ታሪክ ቢያጡበት እንዲህ ወቀሱት
ለራስ ነፍስ ወቀሳ፣
ላጠራቅም ዕድሜ፣
በራፌን ከርችሜ፣
መስኮቴ ላይ ቆሜ፣
አልድን ወይ አላድን፣
በድን!
[የራስ ምስል ገጽ-44]

ግጥም ሲሰምር እንደዚህ ያለ ውስብስቦችን ይገልጻል ዕውቁ ገጣሚ ቻርለስ ብኮቮስኪ “Poetry is what happens when nothing else can.” ይላል። "ግጥም ምንም መሆን ሳይችል ሲቀር 'ሚሆን('ሚገለጥ) ነው" እንደማለት ነው።

ገጣሚው ጉደኛ ነው ሐሳብ ምልከታ አይነጥፍበትም በቼም ይች ዓለም እንቅብ ሙሉ ሐዘን ነው የደፋችብን ይህም ሐዘን ለማረጋገጫ -nihilism- Absurdism- ሚባሉ 'ርዕዮቶች ፈጥሯል። ፈረንሳዊው ደራሲ አልቤር ከሙ በካሊጉላ መንፈስ "ሰዎች ያለቅሳሉ ምክንያቱን ይህች ዓለም ፍትሃዊ ዐይደለችም" ይላል ፋሲል ደግሞ "ሰበብ" ሲል ተመስጦበታል።
የመጀመሪያ መጨረሻ
እየታወቀው ለሰው እየታየው ለሰው
ሞቱ እየታወሰው
ገና ሲወለድ ነው ቀድሞ 'ሚያለቅሰው።
ፋሲል ተካልኝ
[ጡዘት ገጽ-68]

ለምን? የክፍለ ዘመናችን ታዋቂው ደራሲ Anthony T. Hincks እንዳለው ነው። “Sometimes, I cry other people's tears”.(“አንዳንዴ የሌሎችን ዕንባ አለቅሳለሁ።”) የዓለሙ ፍጽምና ማነስ ሲያስቃስተው እንከተለዋለን።
ገለልተኛ ተመልካች ሳይሆን፥ ተቆርቋሪ ነው፤
በንጽረተ-ዓለሙ አፈጣጠር ምልዓተ ፍጽምና መጉደልና በሰው ኅላዌ የሚንፀባረቀው ሰቆቃ ያብሰለስለዋል? ዕንባን ተማምኖ ወደ ዓለም መጥቶ ማቃሰት ግጥሙ የተሸከመውን ህመም አከረረው።

ገጣሚው ስለ እግዜርና ሰይጣን በጻፈው ግጥም ለመመራመር ይጥራል።[ገጽ-45-46]
ለመኖር አምላክ ወይ ሰይጣን 'ሚል ምርጫ ያስቀምጣል። ያለነዚህ ዓለም ሁሌም ባዶ ነው።
ለገጣሚው ከምናቡና ከንጽጽሩ በዘለል ሐሳቦቹ የግጥሞቹ አጧዥ ናቸው።

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እንዲህ በጀርባ አስተያየት ይላሉ "ግጥምን የተዋጣ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል 'ሐሳብ' የቃላት አመራረጥና አደራደር በመጨረሻም 'ምናባዊነት' እና 'ንጽጽር' ናቸው። የፋሲል የግጥም ስብስቦች፣ ስለባህል፣ ታሪክ፣ ስለፖለቲካ በጠቅላላው የሰው ልጅ የሚገኝበት ሁኔታ በተዋቡ ስንኞች ቀርበዋል።" እውነትም!