Get Mystery Box with random crypto!

የአልቤር ከሙ ወርቃማ አባባሎች (በእኔ የተመረጡና የተተረጎሙ) ሳሙኤል በለጠ አልቤር ከሙ(ከ191 | ሳሙኤል በለጠ(ባማ)

የአልቤር ከሙ ወርቃማ አባባሎች
(በእኔ የተመረጡና የተተረጎሙ)
ሳሙኤል በለጠ

አልቤር ከሙ(ከ1913-1960) በሥነ-ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት የተበረከተለት ትውልደ አልጀሪያዊ ፈረንሳዊ ደራሲና ፀሐፌ ተውኔት ነው።

እንደ የልቦለድ ደራሲ፥ ወግ ፀሐፊ፥ ጋዜጠኛና ፀሐፌ-ተዉኔት ስሙ የገነነ ነዉ። አልቤር ከሙ በሥራዎቹ የሕይወትን ወለፈንድ(the absurdity of life) በስፋት ዳሷል።

ምድር ላይ ብዙም ያልሰነበተው ከሙ ከሆነ ስፍራ በባቡር ለመሳፈር ሲጣደፍ ጓደኛዉ በሚኩና ካላደረስኩህ ብሎት እያሽከረከር ሲጓዝ በሌላ መኪና ይገጫሉ። ጓደኛዉ ሲተርፍ፥ ካሙ ግን በአደጋው ይሞታል። ልክ እንደ ፅሁፎቹ አሟሟቱም ፍልስፍናዉን -የሕይወት ወለፈንድን- ያደምቃል ይላሉ ብዙዎች ከአባባሎቹ ለዛሬ እንቀንጪብ:-

1.በዚህ ሁሉ መኃል መረዳት የቻልኩት በተሸፈነ ድቅድቅ ክረምት ውስጥም የተሸሸገ በጋ በውስጤ ተዳፍኖ መኖሩንና ማግኘቴን ነው::

2.እስከ ዕንባህ የመጨረሻ ጠብታ ጥረስ ኑር

3. ደስተኛ ለመሆን ስለሌሎች ከልክ በላይ መጨነቅ የለብንም።

4.በሁሉም ውብ ልብ ውስጥ አንዳንዴ ኢ-ሰብአዊ የመሆን ነገር አለ።

5.ሰዎች ያለቅሳሉ ምክንያቱም ይች ዓለም ፍትሐዊ አይደለችምና

6.እኔ ያለሁት ስላመጽኩ ነው።

7.ነጻነት የተሻለ የመሆን ዕድል እንጂ ሌላ አይደለም።

8. ልቦ-ለድ በምስል የተገለጸ ፍልስፍና እንጂ ሌላ ዐይደለም

9. በዓለም ላይ ያለው ክፋት ሁል ጊዜ ከድንቁርና የሚመጣ ነው፣ መልካም ህሳቤም ከሌለው የመጥፎ ስሜት ያህል ይጎዳል።

10. የሕይወት ትርጉም ምን መሰለህ(ለሽ) 'ራስህን ከማጥፋት የሚከለክልህ የምታደርገው ማንኛውም ነገር እሱ የሕይወት ትርጉም ነው።

11. በየቀኑ የምትወስነው በጣም አስፈላጊው ውሳኔ 'ራስህን ላለመግደል መወሰን ነው።

12. ሕይወት የሁሉም ምርጫዎችዎ ድምር ውጤት ነው፣ ታዲያ ዛሬ ምን እያደረክ ነው?

13. ደስታና ወለፈን ሁለት የተለያዩ የአንድ ምድር ልጆች ናቸው፣ አይነጣጠሉም።

14. ራሴን ላጠፋ ወይንስ ቡና ልጠጣ? በመጨረሻ አንድ ሰው 'ራሱን ከማጥፋት ከሚያስፈልገው ድፍረት ይልቅ ለመኖር የበለጠ ድፍረት ያስፈልገዋል።

15. ተስፋ 'ኮ የለም እንፈጥረዋለን 'ጂ

16. የወለፈንድ(absurd) ጽንሰ-ሐሳብ አስፈላጊና የመጀመሪያው እውነት ነው።

17. እኔ የምወደው ሥዕሎችህን ሳይሆን ሥዕልህን ነው።