Get Mystery Box with random crypto!

ፀጥታን-ፍለጋ ◦ ◦ ሳሙኤል በለጠ ዝም ብሎ ነገር ፍለጋ የተነሳሁ እንዳይመስልህ ፀጥታ 'ምፈልገው | ሳሙኤል በለጠ(ባማ)

ፀጥታን-ፍለጋ


ሳሙኤል በለጠ

ዝም ብሎ ነገር ፍለጋ የተነሳሁ እንዳይመስልህ ፀጥታ 'ምፈልገው WION የተሰኘ የህንድ ግዙፍ መረጃና የፖለቲካ ትንታኔዎችን የሚያቀርብ ተቋም ከአራት ቀን በፊት "What it means live in a noise world" የሚል መረጃ አጋርቶ ነበር። የዊዎን ታዋቂዋ ጋዜጠኛ ፓልኪ ሻርማ ኡፓድሃይ እንዲህ አለች "እስቲ አካባቢህን ቃኝ ምን ትሰማለህ? በእርግጠኝነት ጩኸት ይህቺ የኛ ዓለም አሁን ላይ ጩኸታም ናት በተቃራኒው ፀጥታ ምቾት የማይሰጠን ነገር ሆኗል።



የድምፅ ብክለት ዓለም አቀፍ ተግዳሮት (Global problem) እየሆነ መጥቷል። የድምፅ ብክለት የልብ ሕመም፣ ደም ግፊት፣ የእንቅልፍ እጦት፣ በጩኸት አካባቢ የሚኖሩ ሕጻናት ለጭንቀት ይዳረጋሉ፤ እንዲሁም በጩኸታማ አካባቢ የሚያድጉ ሕጻናት የማንበብ ባህላቸው አነስተኛ ነው። ለምን በጩኸታማ ዓለም እንኖራለ? ምክንያቱን ዓለም ኢንዱሰትሪ - መር እንቅስቃሴ አብዝታለች" ትላለች ብዙ ጩኸት አለ ብዙ



ምናልባት ጊዜ ፀጥ ካላለ ዓለም ፀጥ የምትል አይመስለኝም አሁን ፀጥታን እየፈለኩ ነው። ቤቴ አጠገብ በሕብረ-ዝማሬ 'ምትዘምር ወፍ ብትኖር እገላታለሁ ምንም ዐይነት ቅኝት ያለው ድምጽ መስማት አልፈልግም 'ፀጥታ' ብቻ አሜሪካዊው የፊልም ዳሪክተር ውዲ አለን እንደኔ ዐይነት ነገር ገጥሞት ነው መሰለኝ "God is silent. Now if only man would shut up." አለ "እግዜር ዝም ብሏል። አሁን ደግሞ ምን አለ ሰው ፀጥ ቢል።" ማለቱ መሰለኝ...



አሁን ፀጥታን ለምን ፈለኩት ትላንት አበባን በትኩረት አይቼ ነው። አበባዋ አበባዋን የፈጠረችው በፀጥታ ጊዜ ነው። መፈጠር መፍጠር ተአምር አይደል? የዕናቴ(የፍሬሕወት) ማሕፀን ጭጭ፣ ፀጥ ያለ ካልሆነ የሕይወት ተአምር እንዴት ይጀምራል? እንዴትም


አሁን ቀኑ በምሽት ክር ተቋጥሯል ሠማዩ ጨፍግጓል፤ ደመናው ቀስ ብሎ ቅርጹን ይለውጣል 'ፀጥ' ሁሉ 'ጭጭ' ብሏል። ፀጥታው በልቤ ማዕዘን ይሰማኛል። ድምጹም የዘላለም መጀመሪያ ነው። ምን አይነት ምስጥር ነው? ፀጥታ 'ምን አይነት ውበት ነው? በፀጥታ ሰበብ ከሸሸሁት መከራ ከምገፋው ሰቆቃ አቆራኛለሁ በእርግጥ እስትንፋስን የመንጠቅ ኃይል አለው እስትንፋሱ ተቀጣጥሎ ወደ ዘላለም ማደጉ አይቀርም! ወይም በሥጋ

በጨለመ፣ በጨገገ፣ ብርሐን በጨለማ ውስጥ ሆኖ ትዝታውን በሚተዝትበት ቅጽበት ፀጥ ስትል(ስትይ) የሆነ ኃይል ይሰማል? ከእግዜር ጋር ለመገናኘት ከፈለክ ከእግዜር ዘንዳ ያለው ፀጥታ ሊኖርህ ይገባል።

አስብ ለምን ጩኸት በዛ ከጩኸት የሚሸሽ ማህበረሰብ እንዴት አጣን? መቼ ነው? ከፀጥታ ጋር የተላለፍነው? ፀጥ ስንልኮ ትናንት፣ ዛሬ፣ ነገ ይሿረባሉ 'ኮ

ከሰው መንጋ እንነጠል
ላንድ አፍታ እንኳ እንገለል
ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል


ይሁን
እኔና ፀጥታ
ሊነጋ ነው መሰል እኔና ፀጥታ ሰጋን፥ ጊዜ ጭጭ ይበል።
አሜን
አሜን
አሜን!