Get Mystery Box with random crypto!

ለምንድነው? ሐ..ዘ..ን..ሽ የረዘመው ለምንድነው? ገጽሽ ጨለማማ ጽጌሬዳ ያረገዘው . . . | ሳሙኤል በለጠ(ባማ)

ለምንድነው?
ሐ..ዘ..ን..ሽ የረዘመው
ለምንድነው?
ገጽሽ ጨለማማ ጽጌሬዳ ያረገዘው
.
.
.
ከሰራ አካልሽ
አንድኳ ደስታ ነጋሪ አልቀረም
ሁሉም 'ርጥብ፥
ሕመሙን ነው 'ሚያቀልም!
.
.
.
እግርሽ አይራመድም፣
እርሙን ቢራመድ
ተስፋሽን ነው!
ሕልምሽን ነው የሚንገዳገድ

እናም! ሂጂ አትበላት፥ አታጣላት ከነብሷ
ድሮን መሸከም ነው መሄድ ማለት ለሷ