Get Mystery Box with random crypto!

ሲ ጀ ም ሩ እሱ ... እንዳሻው የሚተወዉ ፍቅር እንዳለ ያስብ ነበር። ቀን አብራዉ ውላ ሲጨልም | ዥ ን ጉ ር ጉ ር . . .

ሲ ጀ ም ሩ

እሱ ... እንዳሻው የሚተወዉ ፍቅር እንዳለ ያስብ ነበር። ቀን አብራዉ ውላ ሲጨልም "ደና ሁን" ብትለዉ ልቡ ሳይዳምን እንደሚያበቃ...

እሷ ... ከዚህ ሁሉ ህመም ኋላ የምትከፍተዉ የልብ በር እንደሌለ ታስብ ነበር ። ልትከፍተዉ ብትሻ እንኳ ቁልፉ በአለማመን ጥልቅ ዉስጥ እንደወደቀ. . .

ሲ ጀ ም ሩ

እሱ .... እሷን ሊተካ የሚችልበት እልፍ ምክንያት እንዳለ ያስብ ነበር። ይሁን ብሎ ሊወዳት እንደጀመረ

እሷ ... እሱ እስካልከፋ የሷ ልብ ነጭ እርግብ እንደሆነ ታስብ ነበር። ልትጎዳዉ አቅም እንደሌላት

ሲ ጀ ም ሩ

እሱ ... አብሮ መሆን ብቻ ላለመሆን የሚሹት መጣመር ነዉ ብሎ ያምን ነበር። የምርጫ ጉዳይ እንጂ የሚያስር ዉቃቢ እንደሌለዉ

እሷ ... ለልብ ጋሻ ይዘዉ "ማፍቀር" ፤ ከመሟሟት የሚያድን ጥላ ነዉ ብላ ታምን ነበር። ከመድማት የሚታደግ እንጂ ለራስ ለወዳጅ የሚተርፍ ጦር እንዳልሆነ

ይሄ ሁሉ ሀ ሲሉ የመተሩት ስሌት ነዉ። ቀን ዉለዉ ፥ ቀን ቆጥረዉ ሲከርሙ የተረሳቸዉ . . .

ሲ ቋ ጩ ት

እሷ . . . ዘግታ የኖረቸዉ ልብ ብትከፍተዉ ከሚቆስለዉ በላይ እንደቆሰለ ገባት። መክፈት ከዚህ አያብሰዉ እንደነበር ... እርግብ ልብ እንዳልነበራት ... አለማመን ከመክዳት በላይ እንዳጸለማት

እሱ . . . ልቡ ገና መለየትን ሲያስብ ዳምኖ እንደነበር ገባዉ። ችላ ሚባል መጣመር እንደሌለ ... "ሰው" ለክተዉ ሰፋኝ ብለዉ የሚያወልቁት ሸበጥ እንዳልሆነ . . . በለኩ ቁጥር ለሁሉ ህመም እንደሚተዉ


ግን ቋጭተዉትም ፍቅር ምን መልክ እንዳለዉ አልተረዱም። አስልተዉ እንደምያደርሱበት ፣ ተርትረዉ እንደማይሰፉት...

ሰዉ አይደሉ . . .

ፍ ቅ ር ስ "ፍቅር" አይደል . . .






@samuel_dereje