Get Mystery Box with random crypto!

... #ይድረስህ_ብለሀለች_በኑር #ለካ_ብዙ_ቻልኩህ__!! ------------------------ | Sami Habib

... #ይድረስህ_ብለሀለች_በኑር

#ለካ_ብዙ_ቻልኩህ__!!
----------------------------------
ትሆናለህ ብዬ አይቸህ በስስት፡
ህልሜን አጨለምከው ተቀየርክ እንደ እስስት፡
ጠንካራ ነህ ብዬ አምኘ ብቀርብህ፡
በጥርስህ እየሳቅክ አራቅከኝ ከልብህ፡
#እኔ_የዋኋ_ግን__!!
ምንም ሳላደርግህ ልሒድ ብትል ሸኘሁ፡
ይቅርታ ሳትጠይቅ ብትመጣ ተሞኘሁ፡
በመውደድ ታስሬ እየተሰቃየሁ፡
ልገፋህ አልቻልኩም አይንህን እያየሁ፡
~~~
#አንተ_ግን__!!
የለፋሁበትን ንፁህ ሀብቴን በልተህ፡
ከኔ አንደበት በላይ የሰው ወሬ ሰምተህ፡
በውሸት ተሸነፍክ እውነታውን ትተህ፡
ስንት ስንት ነገር ያኔ እንዳልተናገርክ፡
በቃልህ ፅና እንጂ አሁን ለምን አፈርክ!!
------------------------------------------
በቃልህ ታስሬ ሀላልህ ሆኘልህ፡
ላንተ መናገሻ ልቤን ከፍቸልህ፡
በጋለው ፍቅራችን ብዙ እቅዶች ፅፈን፡
ኢንሻ አሏህ ብለን ብዙ ህልም ነድፈን፡
ስንት ችግሮችን ስንት ነገር አልፈን፡
ምን ተሰማህ ዛሬ ስንለይ ተኳርፈን!!?
-------------------------------------------
የህይወትን ወጥመድ ስንት አቀበት ወጥተን፡
ወድጀህ ወደኸኝ ብዙ ነገር ሰርተን፡
በእምነታችን ደምቀን በሀቅ ላይ ፀንተን፡
ስንት ሀዘኖችን አብረን ተሰቃይተን፡
ዛሬ ግን ያን ሁሉ ግሩም ጊዜ ረስተን፡
ወዳጅ መሳይ ጠላት ነገረኛ ሰምተን፡
ሳናስበው ድንገት ቀረን ተለያይተን፡
~
#እንደው_ምን_ተሰማህ..!

ይህንን ስታደርግ እኔ መች ተከፋሁ!!
በል እስኪ ንገረኝ አሁን ምን አጠፋሁ!?
ስንት ስታደርገኝ ስትነክሰኝ መች ሸሸሁ፡
ፍቅር አስገድዶኝ ከቤትህ አመሸሁ፡
ብትለወጥ ብዬ ብዙ ዘመን ታሸሁ
በእውነተኛ ፍቅር ወስኘበት የምር፡
አላህም አስቻለኝ በረታሁ ለታምር፡
~~
ከምላስህ በላይ በተግባር ነገርከኝ፡
ጥለህ እያነሳህ ገድለህ እያከምከኝ፡
አመልህ ሳይጠፋኝ ስንቴ ሸነገልከኝ!?
~~
ከልቤ እንደገባህ ሁሌ እየነገርኩህ፡
ውሸት ቅዠትህን ደጋግሜ ቻልኩህ፡
ላያስችል አይሰጥም በሚል ጠባብ ተስፋ፡
ባንተ ነው ያየሁት ሆድ ካገር ሲሰፋ፡
~~
ስንት እየበደልከኝ እኔ እየታገስኩህ፡
ስትሰድበኝ ፀጥ ስል እያመሰገንኩህ፡
አንተ ስትርቀኝ እኔ እየቀረብኩህ፡
ጥላቻ ስትሰብከኝ እኔ እየወደድኩህ፡
ከአቅሜ በላይ ሆነ አሁን ግን ራኩህ፡
አትረዳም እንጂ ለካ ስንቱን ቻልኩህ!!?
~~
በቃኝ አሁንማ ከልቤ ተሰወርክ፡
ተቀይረህ እንጂ ያኔ እንድህ መች ነበርክ!!
የትዳር ሚስጥሩ አላማና ግቡ ፡
ለኔ መብረቅ ሆኖ ጀምሯል ተግቡ፡
ባለኝ ማንነት ልክ እኔ እየወደድኩህ!!
አብሬ ለመኖር ሁሌ እየነገርኩህ!!
በይሆናል ተስፋ ለካ ብዙ ቻልኩህ!?
~~~~
#አሁን_ግን_በቅቶኛል.....
#የሚለው_ሰው_በዛ...ለምን....!?
~~
http://t.me/Sami_Habib