Get Mystery Box with random crypto!

ማንነትን የማወቅ እና የመረዳት እውነታ የሰው ልጅ በህይወት አካሄዱ አና ጉዞው ላይ ማን የመሆ | መንፈስ ቅዱስ 𝐇𝐎𝐋𝐘 𝐒𝐏𝐈𝐑𝐈𝐓

ማንነትን የማወቅ እና የመረዳት እውነታ
የሰው ልጅ በህይወት አካሄዱ አና ጉዞው ላይ ማን የመሆኑን እውነታ ማወቅ እና መገንዘቡ ወሳኝ ለአንድ አማኝ ወሳኝ ነው።
ብዙ ጊዜ ሰዎች ውስጣቸውን ባዶነት ይሰማቸዋል።ስለ ራሳቸው እራሳቸውን ጠይቀው ምንም አይነት ምላሽን ያጣሉ ። በህይወታቸው ላይ ለውጥን መቀየርን አያዩም። ለዚህም ነው ብዙ ሰዎች እራሳቸውን ፍለጋ ብዙ የሚደክሙት ደስታ የራቀው ህይወት ለመኖር የሚገደዱት ።
እውነቱ ግን ከዚህ በጣም ይለያል
አንድ አማኝ ክርስቶስን ሲያገኝ እና በእርሱም ሲያምን ከዚህ ሁሉ ስሜት እና ሁኔታ ነፃ እንደወጣ ሊያምን ይገባዋል።

“በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።”
ኤፌሶን 2፥6-7
በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነልን ከስልጣናት ሁሉ በላይ በሰማያዊው ስፍራ መቀመጥ ነው። ማንነታችን የክብር ህይወት ነው።ማንነታችን እራሱ ባለቤቱ ክርስቶስ ነው።
ማንነታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንደ አዲስ ታድሷል። ፀጋው ከህይወታችን ላይ ሁሉ የእኔነት መንፈስን መቷል። በእኛ ውስጥ የሚኖረው ባለቤቱ ክርስቶስ ነው።ልንረዳው እና ልናውቀው እሚገባን ትልቁ እውነታ እኛ የክርስቶስ አካል መሆናችንን ነው።

“እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 12፥27
የቅዱሱ የእግዚአብሄር መንፈስ ማደሪያዎች መሆናችንን ልንረዳ ይገባል።በእኛ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ አለ።

“እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤”
ኤፌሶን 1፥13
በመንፈስ ቅዱስ የታተምን እና ተራ አለመሆናችንን መረዳት ወሳኝ ነገር ነው።
ይህን ድንቅ የሆነ ማንነታችንን ባለመረዳታችን ባለማወቃችን የክርስቶስ ፍቅር ተካፋዮች ባለመሆናችን የማይመጥነንን ህይወት ለመኖር እንገደዳለን በተለያዩ ድካም ውስጥ እንወድቃለን
ማንነታችንን ስንረዳ ምን ይሆናል??
እኛ በሀጢያት ላይ እንነግሳለን እንጂ ሀጢያት በእኛ ላይ አይነግስም
ፍፁም የሆነ ደስታ እና እረፍት ይኖረናል
ቅድስናን እምናረገው ልጅነቴን አጣ ይሆናል በሚል ፍራቻ ሳይሆን በእኛ ውስጥ ያለው ቅዱስ የሆነ እና ሀጢያትን እማያቀው ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ ቅድስና ህይወታችን ይሆናል ማደሪያው ንፁ ይሆናል።
ሰይጣንን ሙሉ በሙሉ ድል እንደተነሳ እና እኛም ከክርስቶስ ጋር ጠላትን ድል እንደነሳነው ይገባናል። ሀይሉን ስለተነጠቀ እርሱ በእኛ ላይ አይሰለጥንም።
ማንነታችንን መረዳት እና መገንዘብ በህይወታችን ላይ ለውጥን ያመጣል። ምን ያህል ዋጋ እንዳለን እና ጠቃሚ እንደሆንን ተራ ሰዎች እንዳይደለን እንገነዘባለን።
ተራ አደለንም የክብር አክሊል የሚጠብቀን በክርስቶስ ኢየሱስ ያድንን ክርስቶስ በእኛ ውስጥ የሚኖር የእግዚአብሄር ፅድቆች ነን። ይህን ታላቅ እውነት አውቀን አምነን ልንመላለስ ይገባል።