Get Mystery Box with random crypto!

ማክሰኞ ነሐሴ 24 August 30 የሚጎዱንን መውደድ አንድ ሰው እንዲህ አለ፡ ‹‹ ጠለቶቻችንን | SABBATH SCHOOL(ሰንበት ትምህርት )

ማክሰኞ
ነሐሴ 24
August 30

የሚጎዱንን መውደድ

አንድ ሰው እንዲህ አለ፡ ‹‹ ጠለቶቻችንን መውደድ ማለት፣ ዕንቁው የተደበቀበትን ቆሸሻ መውደድ ማለት አይደለም፣ ይልቅ፣ በቆሻሻው ውስጥ የተደበቀውን እንቁ መውደድ ማለት ነው…እግዚአብሔር እኛን የወደደን እኛ በተፈጥሮ የምንወደድ ስለሆንን አይደለም። ነገር ግን እኛ የምንወደድ የሆንነው እርሱ ስለወደደን ነው። ጠላቶችህን በምታይበት ጊዜ ምን ይታይሃል-በዙሪያው ያለው ቆሻሻ ወይስ በውስጡ ያለው ዕንቁ?



ማቴ 5፡43-48 ያለውን ያንብቡ። የሱስ ጠላቶቻችንን እንድንወዳቸውና እንድንጸልይላቸው ጥሪ እያደረገልን ነው። ክርስቶስ ጠላቶቻችንን መውደድ እንዳለብን ከተፈጥሮ እየሰጠን ያለው ምሳሌ ምንድነው? እርሱ እያስተማረን ያለው ምሳሌ ለምንድነው?



በማቴዎስ 5፡45፣ ክርስቶስ ጠላቶቻችንን እንዴት መቅረብ እንዳለብን ሲነግረን ምናልባትም ትልቅ ችግር ውስጥ ሊከቱን ስለሚችሉ ሰዎች በሰማያት ያለውን አባቱን ምሳሌ ይጠቀማል። የሱስ እንዲህ ይላል፡ - የእርሱ አባት ዝናብንና ፀሐይን ለክፉዎችም ለጻድቃንም እኩል ይልካል፤ እግዚአብሔር ለኃጢአተኞች ዝናብን የሚሰጣቸው ከሆነ፣ እኛ ይልቁንስ እንዴት ልንንከባከባቸው ይገባናል? መሆን እንኳ የሚቻል ቢሆን፣ የሱስ ሁልጊዜ በህይወታችን ችግር ለሚፈጥሩብን ሰዎች ሁሉ ሞቅ ያልን (ፍልቅልቅ) እንድንሆን አይደለም ሊነግረን የፈለገው። በመሰረቱ ጠላቶቻችንን መውደድ ማለት፣ ስለ እነርሱ የሚሰማን ስሜት ሳይሆን ለእነርሱ ጥንቃቄ ለማድረግ በምንፈጽመው የተለየ ድርጊት የሚገለጽ ነው። ክርስቶስ ይህን ንባብ የሚጨርሰው ብዙ ጊዜ ክርክር በሚያስነሳ ሃሳብ ነው ይህም ‹‹ የሰማዩ አባታችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ››(ማቴ 5፡48) በማለት ነው። ነገር ግን ትርጉሙ በንባቡ አውድ ግልጽ ነው። እነዚያ እንደ እግዚአብሔር ፍጹም መሆን የሚፈልጉ ሁሉ፣ እርሱ ለጠላቶቹና ለወዳጆቹ ፍቅሩን እኩል ለሁሉም እንዳሳየ እነርሱም ጠላቶቻቸውን በመውደድ ያሳዩ። በእግዚአብሔር እይታ ፍጹም መሆን ማለት ጠላትን መውደድ እና እግዚአብሄር ብቻ ሊሰጠው የሚችለው የልብ የዋህነት ነው። <<በጉዳት ውስጥ በትዕግስት መጽናት ›› የሚለውን ለየዋህነት የተሰጠውን ትርጉም በሀሳባችን እንደያዝን፤ እግዚአቤሔር ትክክለኛውን የልብ የዋህነት እንዲሰጥህና ጠላቶችህን ለመውደድ ማድረግ ያለብህን ነገሮች ዝርዝር ጻፍ።

@SabbathSchool @TekalignSorato