Get Mystery Box with random crypto!

ረቡዕ ነሐሴ 18 August 24 የሚያሳምን ምስክር በሐዋርያት ስራ መጸሐፍ ውስጥ፣ ምስጋና በሰ | SABBATH SCHOOL(ሰንበት ትምህርት )

ረቡዕ
ነሐሴ 18
August 24

የሚያሳምን ምስክር

በሐዋርያት ስራ መጸሐፍ ውስጥ፣ ምስጋና በሰሚዎቹ ዘንድ በጣም አስገራሚ ተጽዕኖ አድርጎ እናያለን። የሐዋ ሥራ 16 ፡ 16-34 ያለውን ያንብቡ። በከባድ ሁኔታ ከተደበደቡና ከተገረፉ በኋላ ጳውሎስና ሲላስ ወደ እስር ቤት ተጣሉ። ክፉኛ በተደበደቡበት ቁስላቸው ላይ ዘይት የሚያፈስላቸው ማንም አልነበረም። በትልቅ ህመምና እግራቸው በግንድ ተጠርቆ፣ በውስጠኛው ክፍል ተጥለው ነበር። ነገር ግን ሌሎቹ እስረኞች እያዳመጡ ሳለ፣ ጳውሎስና ሲላስ ይዘምሩና ይጸልዩ ነበር። የመሬት መንቀጥቀጡ ከሆነ በኋላ፣ ጳውሎስ እና ሲላስን ጨምሮ ከእስር ቤቱ ማንም አስረኛ አለማምለጡን የእስር ቤቱ ሐላፊ ሲያውቅ፣ ‹‹ በጳውሎስና በሲላስ ፊት እየተንቀጠቀጠ፣ ከእስር ቤቱ ወደ ውጪ አውጥቶአቸው፣ ወዳጆቼ እድን ዘንድ ምን ላድርግ? አላቸው” (ሐዋ 16:29, 30) :: ይህ ሁኔታ የእስር ቤቱን አለቃ በራሱ መዳን ላይ ብቻ እንዲያተኩር ያደረገበት ምክንያት ምንድነው? በሌሎች እስረኞች ለማምለጥ ባለመፈለግ እና በዚህ ሰው እና ቤተሰቡ መለወጥ ላይ የጰውሎስና ስላስ መዝሙርና ጸሎት ያደረገው ተጽዕኖ ምንድነው?



ምስጋና በዙሪያችን ያሉ ሰዎች የህይወት ፍጻሜን በመለወጥ ረገድ ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን ማወቅ በጣም አስገራሚ ነው። ጳውሎስና ሲላስ እንደተለመደው በእስር ቤቱ ጨለማ ውስጥ ሆነው አጉረምርመው ቢሆን ኖሮ፣ በዚያ ምሽት አንድም ሰው ይድናል ብለው ያምናሉ? በስተመጨረሻ የእስር ቤቱ አለቃ ምን እንደሆነ አናውቅም፣ ነገር ግን ጳውሎስ በሌለው አስር ቤት ሆኖ በፊል 1፡ 29፣30 ላይ ‹‹ ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኃልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ እንድትቀበሉ እንጅ በእርስ ልታምኑ ብቻ አይደለም። በእኔ ያያችሁት አሁንም በእኔ እንዳለ የምትሰሙት ያው መጋደል ደርሶባችኃል›› በማለት የጻፋቸውን ቃላት ያስቧቸው። እነርሱ ይህንን መልዕክት በማንበብ የእርሱን ህይወት ካንጸባረቁ በህይወታቸው ደስታን አምጥቶላቸዋል፣ በእርግጠኝነት ለልባቸው ደስታን በማምጣት እንዲዘምሩ አድርጓቸዋል፣ እናም ግድድሮሾች ምንም ያህል ዋጋ የሚያስከፍሉ እንኳ ቢሆን ታማኝ ሆነው እንዲቆሙ አድርጓቸዋል ማለት ነው። ከእርስዎ አንደበት ስንት ሰው ለእግዚአብሔር ለእግዚአብሔር በሚሰጡት በትክክል ይታወቅ፣ ከዚያ እንደሚያሰድር ያያሉ። በሚወጣው የምስጋና ዝማሬ የተነሳ ተማርኳል? በሌሎች ዘንድ እርስዎ ምስጋና ልዩ ትኩረት እንዳለዎት በኋላ ምን ያህል አዎንታዊ ተጽዕኖ

@SabbathSchool @TekalignSorato