2022-01-02 17:43:33
"ሀፍሲ"
ክፍል አስራ ሁለት
ፀሐፊ፦ ኑዕማን ኢድሪስ
እሁድ ጧት
3:00 ሰአት
ሻሸመኔ
... መስጅዱ አከባቢ ወላጆቻቸዉን በሞት ያጡ ህጻናቶች ተሰብስበዋል። ረጂና አስታማሚ ያጡ እድሜያቸዉ የገፉ አዛዉንቶችም ምርኩዛቸዉን ተደግፈዉ በመስጅዱ አጥር ስር ተደርድረዉ ተቀምጠዋል። የሻሸመኔ ወጣቶች ጀመዓ እነ ኡስማን ከመምጣታቸዉ በፊት በከተማዉ እየተዘዋወሩ በያዙት መረጃ መሰረት በሀገሪቱ ብዙ ረጂ ያጡ አረጋዉያን ቢኖሩም የተዘጋጀላቸዉን ስጦታ ለመቀበል የመጡት ግን የተወሰኑት ነበሩ። በህመምናና በተለያዩ ምክንያቶች ያልመጡት ብዙ ናቸዉ።
ሙባረክ ስም እየጠራ ሸኽ አጃኢቡና ኡስማን ለአረጋዉያኖቹ የተዘጋጀዉን እያከፋፈሉ ነበር።
ዴቭ፤ ሀያትና ሳራ ደግሞ በሀፍሲ እየተመሩ ወላጆቻቸዉን ላጡ ህጻናት አልባሳትና የምግብ ዉጤቶችን ይሰጣሉ።
... "ሰዉን መርዳት ለየት የሚያደርገዉ ነገር ከተቀባዩ በላይ ሰጪዉ ነዉ የሚደሰተዉ። ስትሰጡ ፤ ለጋሽ ስትሆኑ የሰጣችሁት ሰዉ በናንተ ምክንያት ፈገግ ብሎ ስታዩት ከየትኛዉም ሰዉ በላይ ደስተኛ የምትሆኑት እናንተ ናችሁ!...." ስራቸዉን አጠናቀዉ ከሻሸመኔ ሙስሊም ወጣቶች ጀመዓ ጋር የምሳ ግበዣ ላይ ሸኽ አጃኢቡ ንግግር እያደረጉ ነዉ። "... ልጆቼ በእርጅና ጊዜያችሁም ይሁን ለአኼራዉ ቤታችሁ ሚጠቅማችሁ በወጣትነት የምትሰሩት ኸይር ስራ ነዉ። ብዙ የተቸገሩ አረጋዉያኖች አሉ፤ የእናንተ የእድሜ እኩዮች አልባሌ ቦታ ነዉ የሚዉሉት። አረጋዉያኖችን ተንከባከቡ፤ ወጣቶችንም ከመጥፎ ነገር ታደጓቸዉ።...." አሉ።
.
.
.
... ከምሳዉ በኃላ ጉዞዉ ተጀምሯል። ሳሪና ሙባረክ ከዴቭ ጋር አብረዉ ሲሄዱ፤ ኡስማን ደግሞ ከሀያት ጋር አብረዉ እየሄዱ ነዉ።
ሀፍሲ ሸኽ አጃኢቡ ለምን እንደፈለጓት ብዙም አላሳሰባትም። ከትናንት ምሽት ጀምሮ ዉስጧ በዴቭ ፍቅር ተንጧል። ለወራቶች ያክል የኔ ይሆናል ብላ እርግጠኛ የነበረችበት ነገር በትናንትዉ ምሽት ንፍስ ላይ እንደተሰጣ የስንዴ ገለባ ላይያዝ ላይሰበሰብ ተበታትኗል። አማላይ የሆነዉ ዉበቷ፤ ብዙ ወንዶች የሚቋምጡለት ቁንጅናዋ ዴቭን ማንበርከክ አልቻለም። በቤተሰቦቿና በጓደኞቿ በኩል የመጡት ወንዶች ሁሉ ተጨምቀዉ አንድ ዴቭን ሆነዉ በጠየቀኝ። "በጣም የምወዳት እሷም ከኔ በላይ የምትወደኝ ሴት አለች!"። ተስፋዋ እንደተሟጠጠ ተሰማት። ልጅ እንዳለዉ ስታስብ ደግሞ ይበልጥ ትሸበራለች። ሸህ አጃኢቡ ዘወር ብለዉ ከተመለከቷት በኃላ ንግግር ለመጀመር ያክል "ምን እያሰብሽ ነዉ ልጄ?" አሏት። እንደመደንገጥ ብላ አይኗን እያርገበገበች "ምን አላሰብኩም ኡስታዝ... ይልቅ ትናንት እፈልግሻለሁ ያሉኝ ለምን ነበር?" ብላ እሳቸዉን መልሳ ጠየቀቻቸዉ። ለማወቅ አልጓጓችም። ማዉራታቸዉ ዴቭን ለደቂቃዎች ቢያስረሳኝ ብላ አስባ ነዉ።
... "ሃዩ" አላት።
"ወይዬ ኡስሚ" ብላ መለሰችለት። ሀያት በተፈጥሮዋ ዝምተኛ ናት። ዝምታዋ ግን ብዙ ነገር አሳጥቷታል። አሁን ላይ ግን በዝምታዋ ምክንያት ኡስማንን ማጣት አልፈለገችም። ለማንም ሳትነግር፤ ለጓደኞቿ ሳታማር በዉስጧ ፍቅሯን አፍና ይዛ ኡስማንን ከአንድ አመት በላይ ወደዋለች። ስሜቷን አዉጥቷ ባትነግረዉም በአይኗቿና በሰዉነት እንቅስቃሴ ገልጻለት ነበር። ነገር ግን ኡስማን ልቡ ከሀፍሲ ጋር ስለሄደ ሀያትን ሊያስተዉላት አልቻለም።
"ትናንት የሆነ ነገር ልትነግሪኝ ፈልገሽ ነበር..." ብሏት እጁን ከመኪያዉ መሪ ላይ ሳያነሳ መልከት አላት። እጆቿን እርስ በርስ እያፋተገቻቸዉ ነበር። አሁንም እንደፈራች ያስታዉቅባል።
"ኡስሚ...." አለች። ድምጸን ዝቅ አድርጋ ብትጠራዉም መልሷን እየተጠባበቀ ስለነበር ሰምቷታል።
"ሃዩቲ ንገሪኝ አትፍሪ!" ብሎ ድፍረት እንዲኖራት አደረገ።
"ኡስሚ .. ከነገርኩህ በኃላ ብትርቀኝስ ብዬ ፈራሁ!" ስትለዉ ኡስማን ልቡ እንደመደንገጥ አለ። መጀመሪያም ከሷ እስኪመጣ እንጅ ከትናንት ምሽት ጀምሮ ጠርጥሯል። ምን እንደሚመልስላት ተጨነቀ። ኡስማን ለሰዎች መጎዳት ምክንያት መሆን አይፈልጎም። ሰዎችን ከመጉትና ከማሳዘን ይልቅ ለራሱ ቢጎዳ ይመርጣል። ቤተሰቦቹም ብዙ ጊዜ ሚወቅሱት በዚ ባህሪዉ ነዉ።
"ሃዩ አንቺንኮ ዛሬ አይደለም ማዉቅሽ እንዴት እርቅሻለሁ?" አላት።
"ኡስሚ እንደ ድፍረት አትቁጠርብኝ"
"ችግር የለም ንገሪኝ!"
"ኡስሚ ዉስጤ ያለዉን ስሜት ቃላት አይገልጹኝም። እነግረሀለሁ እያልኩኝ ስለምፈራህ ብቻ ሳልነግርህ አመት አለፈኝ።..." ኡስማን ይበልጥ ተገረመ። "እኔ ሀፍሲን በስድስት ወር ተስፋ እየቆረጥኩ ነዉ አንቺ አመት ሙሉ ሳትነግሪኝ ብቻሽን አፈቀርሽኝ!" በጣም ደነቀዉ።
"... አፈቅራሀለሁ ኡስሚ" አለችዉ። ስሙን እየደጋገመች ስትጠራዉ እሱም በተደጋጋሚ እየዞረ ሲመለከታት ነበር። ለተወሰኑ ደቂቃዎች ምንም ነገር ሳይመልስላት ዝምታን መረጠ። ሃዩ ደግሞ ስሜቷን አዉጥታ ከነገረችዉ በኃላ ወደሱ ዞራ መልሱን መጠባበቅ ያዘች።
.
.
.
..."ሀፍሲ የኔ ልጅ አንቺ በጣም ቆንጅዬ ነሽ። አላህ (ሱ.ወ) አስዉቦ ፈጥሮሻል። እድሜሽም ቢሆን ሃያን እያለፍሽ ነዉ።...." እያሉ ለመግቢያ ያክል በምክር ቢጤ ጎንተል እያደረጉት ነዉ። ሀፍሲም መኪናዋን እያሽከረከረች ጆሮዋን ጣል አድርጋ እያዳመጠቻቸዉ ነዉ። "... ዉበት እንደሆነ ጠፊ፤ እድሜም ገፊ ነዉ። አሁን የሚጠይቁሽ፤ የሚያባብሉሽ ወንዶች ሁሉ እድሚሽ ሲገፍ፤ ቁንጅናሽ ሲጠፋ አጠገብሽ አይገኙም። እና ልጄ..." ብለዉ ወደ ዋናዉ ጉዳያቸዉ ሊገቡ ነዉ። "...እና ልጄ ኡስማን ወዳንቺ ዘንድ ልኮኝ ነበር።" ሲሏት ሀፍሲ በድንጋጤ የመኪናዋን ፍጥነት መቆጣጠሪያ ፍሬኑን ተረገጠችዉ። መኪናዋ ቀጥ ብላ ነበር የቆመችዉ። ኡስማን እዚ ደረጃ ይደርሳል፤ ሸህ አጃኢቡን ይልክብኛል ብላ አስባ አታዉቅም። "እንደ ወንድሜ ነዉ የማይህ" ካለችዉ በኃላ ተስፋ ቆርጧል። ትቶኛል ብላ ታስብ ነበር።
"ምን ሁነሽ መኪናዉን አቆምሽ?" ብለዉ ጠየቋት። ተረጋግታ ለማሽከርከር እየሞከረች "አይ ምንም!" አለቻቸዉ።
"ነቢ ሰላም አላ
ረሱል ሰላም አላ
ሙሀመድ ነብዬ ሶለላህ አላ
ሙሀመድ ነብዬ ሶለላህ አላ...." ዴቭ የመኪናዉን ቴፕ ድምጽ ለቆታል። በሸህ ሙሀመድ አወል መንዙማ ሙባረክና ሳሪ ከመኪናዉ የኃላ ወንበር ሁነዉ በህብረት እያጨበጨቡ ይቀበላሉ። የሰሩት ስራ አስደስቷቸዋል። ምክንያቱም ከአዲስ አበባ ዉጭ ወደ ክፍለ ሀገር ተጉዘዉ አረጋዉያንንና ወላጆቻቸዉን ያጡ ህጻናት ሲረዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ነዉ። ዴቭ የመኪናዉን መሪ በመሀል እየለቀቀ እንደነሱ ጋር አብሮ ያጨበጭባል።
"ሀዩቲ ይሄን ያክል ጊዜ ሳትነግሪኝ መጎዳት አልነበረብሽም..." አላት። አንድ አመት ሙሉ ሳትነግረዉ ከምትቆይ መጀመሪያ አከባቢ ሀፍሲ ልቡ ዉስጥ ሳትገባ፤ ሳያፈቅር ብትነግረዉ የተሻለ እንደነበር እያሰበ አሁን ምን ብሏት እንደሚለያዩ ማሰላሰል ጀመረ።
"ልነግርህ አስቤ ነበር ግን ፈራሁህ" አለችዉ። ኡስማን ማግባት እንዳለበት ያምናል። ነገር ግን ሸኽ አጃኢቡን ወደ ሀፍሲ ልኳቸዋል። የሀፍሲን መልስ ማወቅ ስላልቻለ ሀያትን ምን ብሎ ይመልስላት፤ ጨነቀዉ። "በድጋሜ ሀፍሲ አልፈልግም ካለች ሀያትን አገባታለሁ!። ፍቃደኛ ከሆነች ግን ሀፍሲን አገባታለሁ።" ብሎ ለራሱ ወሰነ።
https://t.me/ramadanlov
ክፍል አስራ ሶስት ይቀጥላል.........
282 views , 14:43