Get Mystery Box with random crypto!

እሑድ ግንቦት 27 (June 4) በቨርጂኒያ ቅድስት አርሴማ ወቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ክብረ | መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

እሑድ ግንቦት 27 (June 4) በቨርጂኒያ ቅድስት አርሴማ ወቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ክብረ ቅድስት ድንግል ማርያምን አስመልክቶ የተዘጋጀ 2ኛው ታላቅ ጉባኤ
በጉባኤው ላይ፡-
የአምላክ እናት ሥዕሏ በብዙ አበባዎች ታጅቦ ይመጣል።
ሠረገላተ አሚናዳብ ናትና የእመቤታችን ሥዕል እጅግ በደመቀ መልኩ በካህናት በምእመናን ታጅባ በሠረገላ ትገባለች።
ለሕሙማንና ለመጡ ኹሉ በፓርት ሳይድ ከእመቤታችን ሥዕል ላይ የሚፈሰው የተቀደሰ ቅብዕ በጉባኤው ለመጡት በነጻ ይሰጣል፡፡
በእመቤታችን አማላጅነት ከሕመማቸው የተፈወሱ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡
በዓለ ጰራቅሊጦስን አስመልክቶ በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ ትምህርት ይሰጣል፡፡
የተጋበዙ ዘማርያን ዝማሬን ያቀርባሉ።

የእመቤታችን በረከትን በስፋት በሚገኝበት በዚኽ ጉባኤ የእመቤታችን ወዳጆቿ ኹሉ በቨርጂንያ ቅድስት አርሴማ ወቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ከ3:30 PM - 7:30 AM ጀምሮ ይገኛሉና ከአኹኑ ጀምረው ይኽነን መርሐ ግብር ይያዙ።

["ኦ ርኅርኅተ ሕሊና ዘሕገ ልማዳ ምሕረት ለኩሉ ፍጥረት፤ ንሳለማ ንዑ ለሥዕለ ማርያም ቡርክት"]
(ለፍጥረት ኹሉ የሕጓ ልማድ መራራት የኾነች ሕሊናዋ የምትራራ የቡርክት ማርያምን ሥዕል እንሳለማት ዘንድ ኑ) (መልክአ ሥዕል)

አድራሻ 8301 Frye Rd Alexandria, Va 22309