Get Mystery Box with random crypto!

(አስቸኳይ) ክቡራን ሆይ በክረምት ጊዜ በተቋማችን በአንድሮሜዳ ስም ለልጆች ሥልጠና እንሰጣለን በሚ | መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese

(አስቸኳይ) ክቡራን ሆይ በክረምት ጊዜ በተቋማችን በአንድሮሜዳ ስም ለልጆች ሥልጠና እንሰጣለን በሚል በሐሰት በስማችን የሚጠቀሙ ገንዘብ የሚጠይቁ እንዳሉ ሰምተናል። ብዙዎችም እየደወላችሁ ነግራችሁናል።
የአንድሮሜዳ የሥልጠና ተቋማችን ግን የክረምት የአንድሮሜዳ ሥልጠና ምዝገባ አስካሁን ያልጀመርን ሲሆን ምዝገባ የምንጀምረው በሚቀጥሉት ሳምንታት ሲኾን ሥልጠናውም ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ታላላቅ ተመራማሪዎችን ሥልጠናው ላይ የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ታላላቅ ዕውቀቶችንና ዘመናዊውን ሳይንስን የያዙ ትምህርቶችን
ግእዝ፣ ሥነ ፈለክ፣ ቀመረ ፊደል፣ ሥነ ዕፀዋትና በሌሎችም ጥበቦች ባለፈው ዓመት በሰጠንበት "ዓለም ሲኒማ" በሠኔ መጨረሻ ጀምረን ክረምቱን የምንሰጥ ይሆናል።
ይህንንም በሚቀጥሉት ጊዜያት የምንገልጽላችሁ ሲሆን በስማችን ከሚያታልሉ እንድትጠበቁ ስንል መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
(ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ)
(ዶ/ር ጌትነት ፈለቀ)