መዝሙር 103 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን። ² ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ፤ ³ ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥ ⁴ ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥ በምሕረቱና በቸርነቱ የሚከልልሽ፥ ⁵ ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጕልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል። ⁶ እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል። ⁷ ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ፥ ለእስራኤል ልጆችም አደራረጉን። ⁸ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ። ⁹ ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥ ለዘላለምም አይቈጣም። ¹⁰ እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም። ¹¹ ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጠነከረ። ¹² ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፥ እንዲሁ ኃጢአታችንን ከእኛ አራቀ። ¹³ አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤ እግዚአብሔር የምህረት አምላክ ነው @rivivalministry 475 viewsSuperior Anoiting , edited 16:03