Get Mystery Box with random crypto!

ረያን meme & islamic post

የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_meme_and_islamic_post — ረያን meme & islamic post
የቴሌግራም ቻናል አርማ reyan_meme_and_islamic_post — ረያን meme & islamic post
የሰርጥ አድራሻ: @reyan_meme_and_islamic_post
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.29K
የሰርጥ መግለጫ

.
አላማችን አንባቢ ትውልድ መፍጠር ነው
♥ኑ እየተዝናናን እንማማር♥
ያላችሁን ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ አድርሱን👇
@Reyuu_bot
Leave ከማለቶ በፊት ያልተመቾትን ነገር በዚ ያሳውቁን
@Reyuu_bot

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-15 06:53:21
በአንድ ካንፓኒ ውስጥ ተቀጥሮ ይሰራል። ነጭ ደሀ ነው። በሚያገኘው ገቢ የእናቱን የሚስቱንና የልጆቹን ጉሮሮ ይደፍናል። ፍፁም ለጌታው ተገዢ ለአላህ ያደረ ሰው ነው። ዘውትር ስራውን በአግባቡና በእምነት ይከውናል። ሙስሊም እንዲህ ነው ታማኝና ትጉህ! ከዕለታት በአንዱ ቀን ከስራ ገበታው ይቀራል። የካንፓኒው ባለቤት "ክፍያ አንሶት ይሆናልና ነገ ከመጣ ደመወዙን አሳድግለታለሁ" ሲል ይወስናል።

ጨረቃ ለቀን ተረኛዋ ፀሐይ ቦታዋን ለቃለች። ፈጅሩ ወገግ ብሎ ጎህ ቀዷል። ሰራተኛው በጠዋት የስራ ገበታው ላይ ተገኝታል። ገና ከመግባቱ ደመወዙ ከነጭማሪው ሲሰጠው ምንም ሳይደነቅ ለምን ክፍያ እንደተጨመረለት ሳይጠይቅ ስራውን ቀጠለ።

ለተወሰኑ ቀናት እንደበፊቱ ስራውን በአግባብ አከናወነ። በመሐል አንድ ቀን ግን ዳግም ከስራ ገበታው ቀረ። አለቃው በጣም ተቆጣ። የጨመረለትንም ደመወዝ መልሶ ቀነሰ። ስራውን ጨርሶ ክፍያ ሲቀበል የተጨመረለት እንደተቀነሰ አወቀ። አሁንም ግን ምንም አይነት ቃላትን አልተነፈሰም።

በሰራተኛው ሁኔታ የተገረመው አለቃ፦ "ባለፈው ክፍያ ስጨምርልህ ምንም አላልክም ዛሬም ስቀንስብህ ምንም አይነት ጥያቄ አላቀረብክም ለምንድነው?" ብሎ ጠየቀው።
እሱም፦"የመጀመሪያ ጊዜ ስራ የቀረሁት ሚስቴ ወልዳ ነው ያን ቀን ደመወዝ ስትጨምርልኝ ስለጭማሪው ያልጠየቅኩህ የደመወዙ ጭማሪ ያ አዲስ ለተወለደው ህፃን አላህ የመደበለት ሪዝቅ እንደሆነ ስላወቅኩ ነው። ትናንት ስራ የቀረሁት ደግሞ እናቴ ሞታ ነው። ደመወዝ ስትቀንስብኝ ዝም ያልኩት ያ ከዚህ በፊት ትበላው የነበረው የእናቴ ሪዝቅ በሷ መሞት ምክንያት አላህ አቋርጦት እንደሆነ አወቅኩ" ብሎ መለሰለት።

Mahi Mahisho
989 views🅡🅔🅨🅐🅝 ●, 03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ